Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Abiy's call for peace is positive but he has to take swift & concrete actions on the ground!

Post by Axumezana » 03 Feb 2025, 16:55

Abiy has to do the following in an immediate effect!

- Change his slow death/ divide & rule strategy ( he has implemented over the last two years) to stabilization, rehabilitation and empowerment of Tigray as per the Constitution.
- Recognize & respect TPLF as his grand father party
- Reinstate Tigray territorial integrity & facilitate the return of displaced Tigrayans .
- Work with TPLF to restructure and restaff the Tigray Temporary government. Tigray should be led by a person who has been accepted/approved by both TPLF and the Ethiopian government
- Genuine Political Dialogue with TPLF & establishment of tactical alliance with TPLF to defend Ethiopia from foreign invaders like Egypt backed Eritrea or Somalia.The tactical alliance could be upgraded to strategic alliance and integration within the next 5 to 10 years.
- Election in Tigray within a year for Tigray people to have their elected government .
- Fund the rapid reconstruction of Tigray


የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለትግራይ ህዝብ በተለይ ለትግራይ ሊሂቃን ያቀረቡት ጥሪ

+++++++++++++

ጥር26/2017(ጋዜጣ+)፡- በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለጽኩት፡ የትግራይ መሬትና ህዝብ የስልጣኔ መነሻ፣ የሃገረ መንግስት ዋልታና ጋሻ ናቸው። የትግራይ መሬትም የመንግስት አስተዳደር፣ የአስተዳደር ስርዓት እና የሀገር እሴቶች መፍለቂያና ማቀቢያ ነው። የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን በመፍጠር እና በመንከባከብ ውስጥ ያለው ሚና ጥልቅ መሆኑን ፀሃይ የሞቀ ሓቅ ነው። የትግራይ ህዝብ በማይፋቅና በማይደበዝዝ ቀለም የተፃፈ ደማቅ ታሪክ ያለው ህዝብ ብቻ አይደለም፣ ከምንም በላይ ደግሞ የአገሩ ወዳጅ፣ የሰላምና የብልጽግና ወዳጅ የሥራ ወዳጅ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሓቅ ነው። ትግራይ ብዙ ሊቃውንት ምሁራንን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ህዝባቸውንና አገራቸውን የሚጠቅሙ የሀገር ሽማግሌዎችን አፍርታለች።

የትግራይ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የመንግስትን ምንነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ሃገረ መንግስት የመሰረተ ነው ። ይህ ብቻ ሳይሆን ሃገረ መንግስቱ አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅትም ቢሆን ከባድ ዋጋ እየከፈለ ሃገረ መንግስቱን ያቀበ ህዝብ ነው።

በለዚህም ነው ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን ለሀገሩና ሉዓላዊነቱ ክብር ሲል ከድርቡሽ፣ ከግብፅ እና ከጣሊያን፣ በኋላም ከምዕራብ ወይም ከምስራቅ እንዲሁም ከሰሜን ወራሪ ሃይሎች ጋር ተዋግቶ ለሃገሩ ሉኣላዊነት መስዋእትነት የከፈለው። በተጨማሪም ለዴሞክራሲ፣ ለሰላምና ለልማት ዋጋ ከሌሎች ወንድማማች ብሔሮች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ልማትና እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

ሌላው የትግራይ ህዝብ መለያ ባህሪ የሀገር ፍቅር ነው።ልክ የትግራይ መሬት የኢትዮጵያ መሰረት እና ማዕከል ሆኖ እንዳገለገለ ሁሉ የትግራይ ህዝብ ልብም በአገር ፍቅር ስሜት የተሞላ መሆኑን የታሪክ ማስረጃዎች በመጥቀስ ለማረጋገጥ መሞከር "ለቀባሪ ማርዳት" ነው ።

የትግራይ ህዝብ ሃገሩን በሰላሟም ሆነ በችግር ጊዜ ኪዳኑን ሳይክድ ዋጋ እየከፈለ የአባቶቹን አደራ ጠብቋል።

በተለያዩ ዘመናት ማእከላዊ መንግስት እንቅፋት ሲገጥመው ሀገሪቱን በማዳን እና ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

ከአክሱማዊ መንግሥት ውድቀት በኋላ የተፈጠረውን ክፍተት በመዝጋት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ክፍተቶችን በማስተካከል ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። አገራዊ አንድነትን በማረጋገጥ ረገድም ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

የትግራይ ህዝብ ታታሪና ስራ ወዳድ ነው። የትግራይ ህዝብ ኮረብታ ላይ ወጥቶ ያለማል፣ ድንጋይ ሰንጥቆና ፈልፍሎ የሚገነባ ህዝብ ነው ። ይህንን ግልጽ እና የታወቀ እውነታ ለማሳየት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገኝም። የትግራይ ህዝብ ትንሽ ሰላም በነበረበት ወቅት በንግድ፣ በግብርና፣ በህንፃ፣ በኪነጥበብ፣ በቴክኖሎጂ መስክ ያከናወኗቸው ተግባራት መንገደኞች የሚገነዘቡት ሃቅ ነው። ከዚህም በላይ በፈተናዎች ውስጥ የማይናወጥ በመንፈስ የጠነከረ ሕዝብ ነው።

እንደ አለመታደል ሆኖ ግን በተለይ ባለፉት መቶ አመታት በተለያዩ አጋጣሚዎችና ምክንያቶች በተለይም ከማእከላዊ መንግስት ጋር ባለው ግጭት የትግራይ መሬት የጦር አውድማ ሆኗል፤ የትግራይ ህዝብም የጦርነት መጠቀሚያ ሆኗል። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መነሳት ያለበት ጥያቄ የትግራይ ህዝብ ባለፉት መቶ አመታት ጦርነት ምን አይነት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፀጥታዊ ጥቅሞች አገኘ ፣ምንስ ከሰረ ? ብለህ መጠየቅና ማሰላሰል ይገባል ።

በዚህ ጊዜ አንድ አስተዋይ የትግራይ ሊሂቅ ትግራይና ህዝቦቿ ከጦርነቱ ያገኙት ወይስ ያጡት ጥቅም ይበዛል ብሎ መጠየቅና መልስ ማግኘት አለበት። ሌላው ሊነሳ የሚገባው ጦርነት ብቸኛው አማራጭ ነበር ወይ? ሌላ መፍትሄ አልነበረውም? የሚለው ጥያቄ ነው። እና ከአሁን በኋላ ጦርነት እንዳይነሳ ለመከላከል ምን ማድረግ ይሻላል ? የሚል ጥያቄውን መጠየቅ እና መልሱን ማግኘት አስፈላጊ ነው።

በጣም የሚያሳዝነው የትግራይ ህዝብ የትላንት ቁስሉን ሳያገግም አሁንም ሰላምና መረጋጋት አግኝቶ ሰርቶ እንዳይገባና እንዳይለማ በጦርነት ወሬ ፍርሃት ሽብር እየኖረ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን አደጋ እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ተረጋግቶ መወያየት ያለበት ጉዳይ መሆኑ ከጠቢብ የተሰወረ አይደለም።

ስለዚህ የትግራይ ተወላጆች በፖለቲካ፣ በቢዝነስ፣ በፀጥታ ፣ በአካዳሚክ እና በሚዲያ እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ምሁራን የትግራይ ህዝብ እስካሁን የተከፈለው ዋጋ ይበቃዋል ፣ ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም ብላችሁ መጀመሪያ በውስጣችሁ ያለው ልዩነት በሰላም በውይይትና በመረዳዳት የትግራይ ህዝብ አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ጉዳያችሁ እንድትጨርሱ እጠይቃለሁ።

ቀጥሎ ከፌደራል መንግስትና ከሌሎች ሃይሎች ጋር ያላችሁን አለመግባባት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንድትሆኑ ጥሪ ኣቀርባለሁ ።

በፌዴራል መንግሥት በኩል በሁሉም ጉዳዮች ላይ መወያየት፣ የሃሳብ ልዩነቶችን እንደ የአመለካከት ልዩነት ወስዶ ግን በተግባባንባቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተስማምተን እንድንሠራ የሚያደርግ ሁኔታ እንዳለ በመገንዘብ ህዝብን ከስጋት እናቶች እንቅልፍ ከማጣት፣ወጣቶች ከመሰደት ማዳን ላይ እንድትሰሩ ከሁሉም በላይ ግን ህዝብዐወደ ልማትና ማገገም እንዳመለስ አብረን እንድንሰራ በድጋሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

ሰላምና መረጋጋት ለትግራይ ህዝብ
ጥላቻና ጦርነት ይበቃል

! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
==================================================================================================================