ወጣት ሆኜ ስለ አማርኛ ቀልድ ሰምቻለሁ።
ቀልዱ ቋንቋዉ ፍሌክስብል ነዉ የሚል ይመስለኛል።
የማዉቃቸዉ ቋንቋዎች ዉስጥ ያሉትን ተመሳሳይ ቃላትን በብዛት ማስተዋል በቅርቡ አማርኛ ኦሮምኛ ዉስጤ ነዉ የሚል መስሎ ታየኝ። አማርኛ ብቻ ሳይሆን እንግልዘኛም ኦሮምኛ ዉስጤ ነዉ፣ አማርኛም ዉስጤ ነዉ የሚል መስሎ ታየኝ።
ስገምት አማርኛ ትግርኛም ዉስጤ ነዉ የሚል ይመስለኛል።
በቅርቡ ኣዉት የሚለዉ የእንግልዘኛ ቃል ኣዉጥ ከሚል የአማርኛ ቃል ጋር ሲመሳሰልብኝ ጉድ ነዉ ኣስባለኝ። ጉዲ፣ ጉድ፣ ጉድ።
ትላንትና ኣእምሮዬ ዉስጥ መጥቶ እንደ ቀልድ ሲመላለስ የዋለዉ እና መርሳት ያልቻልኩኝ የሃገር ቋንቋን ሰብኛ ማድረግ ይቻል ይሆን ነዉ።
የሰብ ወይም ሕዝባችን ቋንቋ የሆነ። ቆንቆ ሰበ ኬኛ። ቆንቆ ሰበ ኢትዮጵያ።
የሁሉም የሃገር ሕዝብ ወይም ሰብ ቋንቋዎች የጋራ የሆኑ ቃላትን ያካተተ።
ለምሳሌ እፋ እና ይፋ ኣንድ ቃል ናቸዉ።
ሰብኛ የበለጠ መሠረት ያለዉን ቃል መርጦ ይጠቀማል ማለት ነዉ።
ይህ ለምሳሌ ያህል ነዉ።
እኔ የቋንቋም ሆነ የሰብ ወይም ሶሻል ሳይንስ ባለሙያ ኣይዴለሁም።
ቁም ነገሩ የቋንቋ እና ሶሻል ሳይንስ ባለሙያዎች ይህ እንደ ቀልድ የመጣልኝን ሀሳብ እንዴት ያዩታል ነዉ።
ምሳሌዉን በደንብ ብያዩት እፋ ነዉ ማለት ይፋ ነዉ ከማለት ልዩነቱ ምን ያህል ነዉ?
Re: ቀልድ እና ቁም ነገር፥ ሰብኛ
ሌላ ምሳሌ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ እና ትግርኛ ዉስጥ የጋራ የሆነ ቃል ሐቅ ነዉ። ሐቀ፣ ሐቅ፣ ሐቂ እያሉ።
ሶስቱም ኣንዱን ቢጠቀሙ ሰብኛም ያንን የጋራ ቃል ይጠቀማል።
ካልተሳሳትኩ አማርኛ የኩኖ ኣምላክ የነገሰ ዘመን የተፈጠረ ቋንቋ ነዉ። በወታደሮች።
ቋንቋ በወታደሮች ከተፈጠረ ቋንቋዎች በቋንቋ ምሁራን መጠገን እና መዳበር ኣይችልም?
በእኔ አስተያየት አማርኛ ብዙ የተጻፈ ቢሆንም ገና የሚዳበር ነዉ። ኦሮምኛ በሰፊዉ የተጻፈ ባይሆንም የዳበረ ነዉ።
ለምሳሌ ኦሮምኛ ምቹ፣ ሸጎዬ፣ አዶዬ ሲል አማርኛ ዉስጥ አዶዬ መኖሩን ኣላስታዉስም።
ሰብኛ አዶዬን ቢጨምር የቋንቋ ጥቅም እንጂ ችግር ሊኖረዉ ይችላል?