ትረካ ያልኩኝ በእንግሊዘኛ ናራቲቭ የሚባለዉን ለማለት ነዉ።
ሃገራዊ ብሔራዊ ማለትም ይቻላል።
ሃገር ለሁሉም ዜጎችዋ ከለላ ናት።
ይህን በጥልቅ ያስተዋሉ ዜጎችዋ ሃገራዊ ትረካቸዉ ወጥ ወይም ኮሄረንት ነዉ። ሃገር የሁላችንም ከለላ ናት ማለት የማይችሉ ዜጎች ሃገራዊ ትረካቸዉ የተዛባ ወይም ኢንኮሄረንት ይሆናል።
ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ሃገራዊ ትረካ ከግዜ ወደ ግዜ ምን ያህል ወጥ ሆኖ ዛሬ ደረሰ? ምን ያህልስ የተዛባ ሆኖ ነበር?
መዛባቱ ከምን ግዜም በተለይ ዘቅጦ የነበረዉ መቼ ነበር?
ይህን ለመገምገም መቶ የማይተዋወቁ ዜጎችን በደንብ የታሰቡበትን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መገመት ይቻል ይሆናል።
አሜሪካኖች ስለ ዐለም ዜና ግድ ዬለሾች ናቸዉ ተብለዉ ቢታሙም ስለ ፕሌጅ ኦፍ አሌጅያንስ እና ናሽናል ኣንተም ወጥ የሆነ ማስተዋል ኣላቸዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
የእኛ ሃገራዊ ትረካዉ እንደዚህ ወጥ የሆኑ እነዚህ ናቸዉ ማለት ያስቸግረኛል።
የህፃንነት ዕድሜዬን ሳልጨርስ እ ኢ አ መስከረም ሁልት፣ አስራ ዘጠኝ ስልሳ ሰባት ጠዋት ያየሁኝን ወይም ያሳየኝን መቼም ኣልረሳም።
በወጣትነት ዕድሜዬ የዛሬ ሰላሳ ሶስት ዓመታት በፊት ጀምሮ መታዘብ የጀመርኩኝም ኣይረሳም።
እ ኢ አ ከስልሳ ሰባቱ ኣብዮት በኋላ የሰማንያ ሶስቱ ስብሰባ ተከሰተ።
በሁለቱ ግዜዎች ሃገር ያስተናገደችዉ ሃገራዊ ትረካዎች የተለያዩ ነበሩ።
የበለጠ ወጥ ወደ ሆነ ነበር ወይስ ወደ መዛባት ነበር ያቀናዉ?
ከዛም ከሃያ ኣንድ ዓመታት በፊት እ ኢ አ ዉሳኔ ዘጠና ስድስት እና በዛ ዉሳኔ ዙርያ የነበረ ንቅናቄ ተከሰተ። ከዛም ምርጫ ዘጠና ሰባት ተከሰተ።
በእኔ ማሰላሰል ምርጫ ዘጠና ሰባት ተያያዥ ቢሆንም ዉሳኔ ዘጠና ስድስት ዙርያ የተከሰተዉ ንቅናቄ ኣሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ላለዉ የፖለትካ ኣቅጣጫ የበለጠ ጉልህ ሚና ያለዉ ይመስላል።
ዉሳኔ ዘጠና ስድስት እና ምርጫ ዘጠና ሰባት አከባቢ ሃገራዊ ትረካ ከምን ግዜም በታች ዘቅጦ የነበረ ይመስለኛል።
ይህ ማሰላሰል እዉነትነት ካለዉ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የሃገራዊ ትረካችን መዛባትን መገምገም ኣስቸጋሪ ነዉ?
ለሃገራዊ ትረካ መዛባት የማይዘነጋ ኣንድ ኣመልካች ነጋሶ ግዳዳ የፍልስፍና ዶክተሬት ይዞ ርዕሰ ብሔር ሆኖ ከሰራ በኋላ ኣንድ ቃለ መጠይቅ ዉስጥ የኣፄ ምኒልክ የአደዋ ዉሎ መከበር ኣለበት ማለት የከበደዉ ነበር።
በዚህ ግዜ የሃገራዊ ትረካችን መዛበት የቀነሰ ቢሆንም የከሰመ ኣይመስልም።
ሃገር የሁሉም ዜጎችዋ ከለላ ናት ማለት እና ይህን ከለላ ሁሉም ዜጎች የመጠበቅ ሀላፊነት ኣለባቸዉ ማለት ምን ያህል ከባድ ነበር? የከለላ ሉዓላዊነት ስር እኩልነት ይስፈን እየተባለ።
Re: ሃገራዊ ትረካችን ባለፉት ሃምሳ ዓመታት
በአከባቢያችን ካህኑ ሞኖቴይዝም ብሎ ከተነሳ ኣሁን ሰላሳ ሶስት ሺህ ዓመታት ኣልፈዋል።
አሜሪካ ስንቱን በድላ ከተቋቋመች ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት ኣልሆናትም።
ይህ ማለት በአስራ ሁለት የብርሃን ሰዓታት ዉስጥ ኣንድ ሰዓት ኣይሞላም ማለት ነዉ።
እንዴት ሆኖ ነዉ ይህን ያህል ረጅም ታሪክ ያለዉ አከባቢ ኣንድ ዘላቂ የመንግስት መዋቅር ኣጥቶ ይህን ያህል አጭር ታሪክ ያለዉ ስንቱን በዳይ ዘላቂ የመንግስት መዋቅር መመስረት የቻለዉ?
መሮዌ ይሁን አክሱም፣ ጎንደር ይሁን አዲስ አበባ ዘላቂ የመንግስት መዋቅር ኖሮዋቸዉ ኣያዉቁም።
ኣሁን ያለዉ የሃገር ሕገ መንግስት የመንግስት ዘላቂነትን ጥያቄ ዉስጥ የምያስገባ ነዉ።
ካህኑ ሞኖቴይዝም ብሎ ከተነሳ ወዲህ መሮዌ መንግስት ነበረ። ዘላቂ ኣልሆነም።
አክሱም መንግስት ነበረ። ዘላቂ ኣልሆነም።
ሸዋ ዉስጥ መንግስት ተቋቋመ። ዘላቂ ኣልሆነም።
ጎንደር ተነስቶ ዘመነ መሳፍንት ኣበቃ ኣለ። ዘላቂ ኣልሆነም።
ኣፄ ምንሊክ ተነስተዉ ያልዘለቀ ቢሆንም አደዋ ዋሉ። በማግስቱ እንግዳ ገብቶ ሌላ ሰበካ ጀመረ።
ኣፄ ሀይለ ስላሴ አንበሳ ተብለዉ ተሹመዉ በአምስት አጭር ዓመታት ግዜ ከሃገር ለመዉጣት ተዳረጉ።
ተመልሰዉ የኣፍርካ ኣንድነት ድርጅትን ለማቋቋም ለፍተዉ በአስር ዓመታት ግዜ ክብር ኣጡ።
ኣብዮት ተብሎ የተንቀሳቀሰች ሃገር ሃያ ዓመታትን ሳታስቆጥር ከዐለም ሃገሮች የድህነት ተርታ ተሰለፈች።
ኣሁን ያለዉ የፌደራል መዋቅር በኣጭር ግዜ ተዋቀረ እና ከአስር ኣጭር ዓመታት በኋላ ለሃገር ቀጣይነት ፈታኝ መሆኑ ተረጋገጠ።
በዚህ ሁሉ ታሪክ ዉስጥ በመሮዌ ይሁን በአክሱም፣ በአንኮበር ይሁን በጎንደር፣ ወይም በአዲስ አበባ ኣንድ ዘላቂነት ያለዉ መንግስት አወቃቀርን መመስረት ለምንድነዉ ያልተቻለዉ?
ይህ ታሪክ የሁላችን ነዉ።