
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮችን በማንሳት የተወያዩ ሲሆን፣ በቅርቡ በተካሄደው 17ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ በተነሱት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
ሁለቱ ሀገራት በቀጠናው ያለውን መረጋጋት እና ትብብር ለመደገፍ ተስማምተዋል።