ጃ-war እይነገረን ያለው፤፟
1. የአብይ አገዛዝ (ኦህዴድ-ብልጽግና) ከተገረሰሰ ሥልጣን ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ዕጅ ሊወጣ ይችላል። ያ ከመሆኑ በፊት ጫና በመፍጠር አሁን ሀገሪቱ ላይ የተፈጠረውን የሕዝብ ብሶትና ቁጣ የተወሰኑ የፖለቲካ ማሻሻያዎች በማድረግ አስተንፍሰን ኦህዴድ-ብልጽግና እንዲቀጥል እናድርገው እያለ ነው ማለት ነው። ወይም
2. የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ቢፈልግ እንኳን በትህነግ ጊዜ እንዳደረገው ኦህዴድ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ሆኖ የኦሮሞ ወጣቶችን/ ቄሮዎችን/ ለሕዝባዊ አመጽ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ዕድል አሁን ላይ የለኝም ብሎ ያስባል ማለት ነው።
ያ ካልሆነ "ሀገሪቱ በታሪኳ አይታ በማታውቀው መንገድ አደጋ ላይ ነች። ወደ መበታተንም እየሄደች ነው። እነ አብይም ሰው የማይሰሙ ዕብሪተኞች ሆነዋል። " ብለህ ከደመደምክ በኋላ "የመንግስት ለውጥ ለማድረግ አይደለም የምንቀሳቀሰው" ማለት በፍጹም አይገናኙም።
Please wait, video is loading...