-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: About Merkato
በመርካቶ “ከደረሰኝ ቁጥጥር ቅጣት” ጋር በተያያዘ “አብዛኞቹ” ሱቆች ተዘግተው መዋላቸውን ነጋዴዎች ተናገሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥር ምክንያት በሻጮች ላይ “ እየተጣለ ያለውን ከፍተኛ ቅጣት የተቃወሙ” ነጋዴዎች በዛሬው ዕለት ሱቆቻቸውን ዘግተው መዋላቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
በትልቁ የገበያ ስፍራ የሚገኙት ዱባይ ተራ፣ ሚሊተሪ ተራ፣ ቦንም ተራ እና አመዴ ማዞሪያ ያሉ ሱቆች “ሙሉ በሙሉ” በሚባል ደረጃ ተዘግተው ከዋሉባቸው አካባቢዎች መካከል መሆናቸውን ነጋዴዎች ገልጸዋል።
ዛሬ ኅዳር 9/2016 ዓ.ም. “አብዛኞቹ” ሱቆች ተዘግተው የዋሉበት መርካቶ፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ አለመረጋጋት ሲታይበት ነበር።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባለሙያዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በገበያ ስፍራው የሚገኙ ነጋዴዎች ለሚሸጧቸው እቃዎች በትክክለኛው ዋጋ ደረሰኝ መቁረጣቸውን እና በሱቆቻቸው ውስጥ የሚገኙ ምርቶች ደረሰኝ ተቆርጦባቸው የተገዙ መሆናቸውን የማረጋገጥ ሥራ ሲያከናውኑ እንደነበር ነጋዴዎቹ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ በመርካቶ አካባቢ የተጀመረው ሥራ “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ” ለማድረግ እንደሆነ ገልጾ ነበር።
ደረሰኝ ሳይቆርጡ የተገኙ ነጋዴዎች “ንብረታቸው ይወረሳል” የሚል ስጋት በነጋዴዎች ዘንድ ተፈጥሮ ነበር። ባለሙያዎች በሚያደርጉት ቁጥጥር፤ ደረሰኝ ሳይቆርጡ የተገኙ ነጋዴዎች “የ100 ሺህ ብር ቅጣት” ሲጣልባቸው እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ስማቸው እንደጠቅስ ያልፈለጉ ለነጋዴዎች ገልጸዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንዲት ነጋዴ፤ “ይህ መረጃ ከተሰማ በኋላ ሰዉ እቃውን [ከሱቆዎች] ማውጣት ጀመረ። ሲጭኑም መንገድ ላይ እየያዟቸው [እቃቸውን] ሲወርሱ ነበር። ስድስት እና 12 ፍሬ እቃ ካለደረሰኝ ሸጠው 100 ሺህ ብር የተቀጡ ልጆች አሉ” ሲሉ ከሰሞኑ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።
ለሸጡት እቃ ደረሰኝ ቢቆርጡም “ትክክለኛው ዋጋ ይህ አይደለም” በሚል ቅጣት የተጣለባቸው ሻጮችም እንዳሉ ሌላ ነጋዴ አስረድተዋል። የቁጥጥር ባለሙያዎቹ በሱቆች ውስጥ የሚገኙ እቃዎች “የተገዙበትን ደረሰኝ ሲጠይቁ” እንደነበርም አክለዋል።
“ሰሞኑን ምንም ዓይነት እቃ ለደንበኛ አይሸጥም። ‘የለም’ ነው የሚባለው። አብዛኛውን መጋዘን ያላቸው ነጋዴዎች እቃቸውን ወደ ቤታቸው አሽሽተዋል” ሲሉ በነጋዴዎች ላይ የተፈጠረውን ስጋት ገልጸዋል።
በአገሪቱ ዋነኛው የጅምላ እና የችርቻሮ ግብይ ቦታ በሆነው መርካቶ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌሎቹም ነጋዴዎች ባለፈው ሳምንት የንግድ ሁኔታውን ተቀዛቅዞ መቆየቱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ሱቆቹ ተዘግተው የዋሉት ነጋዴዎች አባል በሆኑባቸው የቴሌግራም ግሩፖች ላይ “ለአንድ ሳምንት አድማ እንዲመቱ” የሚጠይቅ ፅሁፍ ከተሰራጨ በኋላ መሆኑን አንዲት ነጋዴ ተናግረዋል።
ይህ ሱቆችን የመዝጋት እንቅስቃሴ የተጠራው ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ የበረከተው “ቅጣት እና ንብረት መውረስ ላይ ለውጥ ለማምጣት” በሚል እንደሆነ ነጋዴዋ ጠቅሰዋል።
ሌሎች ሁለት ነጋዴዎች በበኩላቸው ዛሬ ጠዋት ሱቆች መዘጋታቸውን ከተመለከቱ በኋላ እነርሱም በተመሳሳይ መደብሮቻቸውን ዘግተው መዋላቸውን አስረድተዋል።
አንድ ሌላ ነጋዴ፤ በዛሬው ዕለት ሱቆች እንደሚዘጉ “ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ያውቁ የነበሩ” ሻጮች መኖራቸውን አመልክተዋል።
ነጋዴው፤ “ዱባይ ተራ፣ ከይርጋ ኃይሌ እና አመዴ ማዞሪያ ጀምሮ፣ አዳራሽ፣ ጣቃ ተራ፣ አራተኛ” የሚባሉት አካባቢዎች እንዲሁም “አዲስ አድማስ እና ንጋት ብርሃን ህንጻዎች” ላይ ሱቆች መዘጋታቸውን ገልጸዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌሎች ነጋዴዎች ደግሞ ከዱባይ ተራ በተጨማሪ ሚሊተሪ ተራ እና ቦንብ ተራ የሚገኙ መደብሮችም ተዘግተው መዋላቸውን ጠቅሰዋል።
ድር ተራ በተባለው አካባቢ የሚገኙ መደብሮች ደግሞ “ግማሾቹ ሲዘጉ ቀሪዎቹ ሱቃቸውን ገርበብ አድርገው ከፍተው እቃ ግን እየሸጡ አይደለም” ተብሏል። ይሁንና ሸማ ተራ አካባቢ የሚገኙ “ምድር ላይ ያሉ” ሱቆች መከፈታቸውን አንድ ነጋዴ ገልጸዋል።
ቢቢሲ፤ በመርካቶ የሚገኙት ሱቆችን መዘጋት በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ እና ገቢዎች ቢሮዎች መረጃ ለማግኘት ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።
መርካቶ የሚገኝበት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ በማኅራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በመርካቶ “መደበኛ የግብይት እንቅስቃሴ” እየተደረገ መሆኑን የሚገልፅ ፅሁፍ ከፎቶዎች ጋር አጋርቷል።

DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12902
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Re: About Merkato
Revelations,
how on earth are you still losing that much energy and time for someone who is only a mere shepherd?
Can you deny that the man is like any shepherd in the country, here a proof. Picture says more than 1000 words, they say. We have a leader from the people, for the people in Ethiopia, finally.
With regard to Merkato's whining, well there should be an effort to be exerted (pain to be endured) to transform a highly corrupt society in to a modern and law-abiding one. There is no free lunch, dude.
Did the whining stop Piassa's transformation? NO! Did it stop that of Kazanchis, Arat Killo, Meskel Square and many more places?
NO!
So, why expect any different outcome in this case, unless your are truly a dumb like the guy of Ankuro Media?