Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Odie
Member+
Posts: 6182
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: Find Pretty Girls in your city for night - Real Women

Post by Odie » 05 Nov 2024, 19:04

ዮሐንስ 1:1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ዮሐንስ 1:2፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

ዮሐንስ 1:3፤ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

ዮሐንስ 1:4፤ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።

ዮሐንስ 1:5፤ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

ዮሐንስ 1:6፤ ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤

ዮሐንስ 1:7፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።

ዮሐንስ 1:8፤ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።

ዮሐንስ 1:9፤ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
ዮሐንስ 1:10፤ በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።

ዮሐንስ 1:11፤ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።

ዮሐንስ 1:12፤ ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

ዮሐንስ 1:13፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

ዮሐንስ 1:14፤ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።

Post Reply