Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6847
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ነዉር የማታዉቅ ወይም የረሳች አዲስ አበባ ክፍል የማን ናት?

Post by Naga Tuma » 26 Oct 2024, 18:55

በዚህ ሳምንት የህንድ ሰዉ መንገድ ላይ ኣጋጠመኝ። ከየት ነህ ብሎ ቢጠይቀኝ ባህላችን ባደረግነዉ ኮራ ማለት አፌን ሞልቼ ከኢትዮጵያ ነኝ ኣልኩት።

ቁጭት ባለሰለሰዉ ዐይነት ድምጹን ዝቅ ኣድርጎ አዲስ አበባ ዉስጥ ዋለቴ እና ስልኬን ከክሴ ወሰዱብኝ ኣለኝ።

ኮራ ያልኩኝ በቅጽበት ኣፍሬ ኣዝናለሁ ኣልኩት።

ኣዉጫጭኝ ባህል የነበረባት ኢትዮጵያ ሌብነት ነዉር መሆኑ አዲስ አበባ ዉስጥ እንዴት ተረሳ? ወይስ ነዉር መሆኑን የማያዉቅ ኢትዮጵያዊ ኣለ?

እጅ የሌላ ሰዉ ኪስ ሲገባ ቅጣት ግንባርን ብያገኘዉ እናት ምን ትላለች? አባት ምን ይላል?