Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12902
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

አበሯን መንገድ ላይ አየኋት፣

Post by DefendTheTruth » 19 Oct 2024, 14:43

አበሯን መንገድ ላይ አየኋትና፣ መቼስ የአገሬ ሰዉ ናት ብዬ ሰላም አልኳት፣ ወድህ ወዲያ አይተ አፀፈዉን መለሰች፣ ሰላም አለችኝ። ትንሽ ጊዜ ነበረን ና እንዴት ነዉ ሁሉም ነገር ጥሩ ነዉ አልኳት፣ አዎ ጥሩ ነዉ አለችኝ። ኑሮ ትንሽ ይከብዳል አለችኝ። አይ ብከብድም አገር ቤት ከሉት በላይ አይሆንም አልኳት። አገር ቤት ኑሮ ከበድ ብሎዋል ይባላል አልኳት።

ዘላ ችግሩ እኮ ፖለቲካዉ ነዉ አለችኝ፣ የዘር ፖለቲካ አለች ና ቀጠለች፣ ብዙ አወራች።

አይ፣ ነገሩ ስበዛበት ሕዝቡ ራሱ ፖለቲካዉን ይቀይረዋል ብዬ ንግግሯን መቋጨት መከርኩኝ። ደደብነቷ በግልፅ ይታይ ነበር ና እኔ ደግሞ ከደደቦች ጋር ብዙ የማዉራት ተሰጥዖ የለኝም።

ስለ ዘር ፖለቲካ መዘለፋዱን ቀጠለችበት።

የምለዉ ነገር ጠፋኝ ና የዘር ፖለቲካ ረሓብ አያመጣም፣ ሌላ ነገር ከልሆነ አልኩኝ ብዙም ሳላስብበት፣ የኔ ምኞት ደባሪዉን ንግግር ቶሎ መገላገል ነበርና።

ዘለለች አሁንም ሌላ ነገር ላይ። አብይ አህመድ ዘረኛ ነዉ፣ ሕዝቡን በድሮን እየጨፈጨፈ ነዉ አለችኝ። መጀመሪያ ላይ ትግሬን ነበር፣ አሁን ደግሞ አማራ ላይ እልቅት እየፈፀመ ነዉ አለችኝ።

እርግጠኛ ነሽ ወይ አልኳት፣ ትልቅ ዉንጀላ ነዉና። ይህ ምን የልታወቀ ነገር አለዉ፣ እንኳን እኔ ይቅርና ህፃን ልጅም ያዉቀዋል አለችኝ።


ዉስጤ ላይ ከዚህች ደደብ ጋር መገናኘቴ ና ሰላም ማለቴን ረገምኩኝ። ከምን ደደብ ጋር አጣመረኝ ብዬ፣ ራሴን ረገምኩኝ።

ለወሬ ያህል ብቻ እና ህፃን ልጅ ምን አዉቆ ነዉ ምስክር የምሆነዉ አልኩኝ። ያላዩትን ዝም ብሎ መመስከር ኃጢያት መሰለኝ አልኳት። ነገሩንም ለማሳጠር ብዬ። እኔ ፖለቲካ ማዉራት ብዙም ደስ አይለኝም አልኳት፣ ፖለቲካዉን ማዉራቱን ፈርቼ ሳይሆን ከደደብ ጋር ማዉራቱ ስለደበረኝ።

አጭር ምክር ለመለገስ ሞከርኩኝ። ያላየሽዉን ልክ ቦታዉ ላይ እንደነበር አድርጎ ማዉራት ጥሩ አይመስለኝም አልኳት።

ህፃን ና ሽማግሌዎች እየሞቱ ነዉ፣ የኔም ዘመዶች ሞቶዋል ኣለችኝ። ድሮን ተጠቅሞ ንፁሃንን እየጨረሰ ነዉ አለችኝ። ይሄ ግልፅ ነዉ፣ ቀደም ብሎ ትግሬዎች ላይ ነበር፣ አሁን ደግሞ አማሮች ላይ ነዉ፣ ለነገሩ ኦሮሞዎችም እየሞቱ ነዉ አለችኝ፣ ባለቤት ኦሮሞ ስለሆነ አዉቃለሁ አለችኝ።

የመጨረሻ ለመዝጋት ብዬ፣ እንደምመስለኝ፣ ይህ መንግስት ህፃናትን የመግደል ልዩ ፍቅር ኖሮት ሳይሆን፣ ሕፃናት መኃል ሆኖ ከቶከሰበት፣ ራሱን ለመከላከል ና ወንበዴዉን ለማስወገድ የግድ አፀፋ መመለስ አለበት፣ የሕዝቡንም ደንነት ለመጠበቅ ስል አልኳት፣ አሁንስ ትንሽ መረር ስላለኝ። የልፈለኩትን ተናገርኩ መንገድ ላይ ሳዋራ።

አይ አንተ የአብይ ደጋፊ ነህ ማለት ነዉ አለችኝ፣ እሷም አምርራ። ታዲያ የአብይ ደጋፊ መሆን አጥያት አለዉ እንዴ አልኳት፣ በጥያቄ መልሼ።

ጫፍጫፊ ምናምን ብላ የንኑን አሁንም አሁንም ትደጋግማለች፤ የደደብ ነገር።

አብዪ አህመድን መደገፍ፣ የአገር ግንባታን መደገፍ ነዉ፣ አገር እየገነባ ያለ ሰዉ መሆኑን ነዉ የማዉቀዉ አልኳት። መንገድ ላይ እየዞረ የመጣለትን የማዉራት ጊዜም ያለዉ አይመስለኝም አልኳት ና ቀጠሮዬ ደረሰ ብዬ ቶሎ ተለየኋት፣ ከድብርቱ ለመገላገል ብዬ እንጂ ጊዜ እንኳን ትንሽም ብሆን ነበረኝ።

እንደዚህ አይነት ቀን አያገጥማችዉ፣ ከደደብ ይሰዉራችዉ። ሳለም ዋሉ!