Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6852
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ህዳሴ፥ ዱላ፣ ሲቄ፣ ሞዓ፣ ሞዐተ፣ ፍርድ ቤት፣ እስር ቤት

Post by Naga Tuma » 07 Oct 2024, 15:17

ዱላ፣ ሲቄ፣ ሞዓ፣ ሞዐተ፣ ፍርድ ቤት፣ እና እስር ቤት የሚጋሩት ኣንድ ቁምነገር ምንድነዉ ቢባል ፍትሕ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ፍትሕን መሻት በኣብዛኛዉ የሚከሰተዉ በሁለት ግለሰቦች መካካል በሚነሳ ኣለመግባባት ነዉ።

የሁለት ግለሰቦች ክርክር ትልቅ ኣፍራሽ ሊሆን ይችላል። የሁለት ግለሰቦች መስማማት ብዙ የሚገነባ ሊሆን ይችላል።

ጥንት ግዜ ፍትሕ መስጫ በዱላ የተጀመረ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ዱኤል ተብሎ ሰነበተ ማለት ይቻላል።

ሴቶች የማህበረሰብ መሪ የነበሩ ግዜ የበላይነት ነበራቸዉ።

ወንዶች ኣምጸዉ ተቀየረ እና ሞዓ ሆኑ፣ የሴቶችን መብት ሳይነፍጉ።

ሲቄ ቀጭን ቢሆንም ያዉ ዱላ ነዉ። ሴት መብት እንዳላት ማሳያ ምልክት። ስጦታዉ ብታገባትም የመብቷን ማሳያ ምልክት ይሀዉ ተብሎ ያሳዩታል።

ሞዐተ እመቤቶች ስሞታቸዉን አደባባይ ኣዉጥተዉ ተሰምቶ ማሸነፍያቸዉ ነዉ።

የሞዐተ ቀን እመቤቶች ተሰብስበዉ ብሶታቸዉን ስያሰሙ አባወራዎች ከርቀት ሆነዉ ያዳምጣሉ ኣሉ። ሰዉ መንገዳቸዉ ፊት ኣይቆምም። ኣንድ መንገዳቸዉ ላይ የቆመ ሰዉ እሱ ብቻ ደፍሮ ቆመ የተባለን ኣስታዉሳለሁ።

ይህ የዱላ፣ ሲቄ፣ ሞዓ፣ እና ሞዐተ መጣጥፌ የሰማሁኝ እና የገባኝ ያህል ነዉ። ስለዚህ ባህል ጥልቀት ከእኔ የበለጠ ማብራራት የሚችሉ እንዳሉ እርግጠኛ ነኝ።

እዚህ የእኔ አላማ ከኢትዮጵያ ህዳሴ ጋር ምን ኣያያዘዉ ነዉ።

የዐቅሜን ያህል የለፋሁበት ነዉ።

ከጥንት ግዜ ጀምሮ እየዳበረ የመጣዉ የሕዝባችንን ባህል መርሳት ሳይሆን እያጠኑ የበለጠ ማዳበር ያሻል ለማለት ነዉ። የህዳሴ ጽንሰ ሀሳብ በኣጭሩ ይሄ ነዉ።

ለህዳሴ ተመጣጣኝ የኦሮምኛ ቃልን ስፈልግ አዴሱን ኣስታወስኩኝ እና የህዳሴ ወይም የአዲስ ቃል መሠረት ምንድነዉ ኣልኩኝ።

አዲን ኣስታወስኩኝ እና አዲስ ከሀዳስ የመጣ መስሎኝ ስለነበር ሊሆን ኣይችልም ኣልኩኝ። ወድያዉ ሀዲን ኣስታወስኩኝ።

አዲ፣ አዲስ፤ ሀዲ፣ ሀዳስ።

እኔ የቋንቋ ጥናት ባለሙያ ኣይዴለሁም።

እንደዚህ ተመሳሳይ ቃላትን ሳስተዉል የተመሳሳይነታቸዉን ምክንያት እጠይቃለሁ፣ እፈልጋለሁ።

አዲ ወይም ሀዲን ሳስታዉስ ሌላ ጥያቄ ኣስጠየቀኝ። ካልተሳሳትኩ የሀይማኖት አባቶች ነጭ ጨርቅ ኣናታቸዉ ላይ ያደርጋሉ።

ነጭ ልብስ በባህል የምያመለክተዉ ኣለ? ንፅህናን ኣመልካች ነዉ? ኣዲስነትን ኣመልካች ነዉ? ከሆነ የአዲስ ወይም ሀዳስ ቃል መሠረት አዲ ወይም ሀዲ ሊሆን ይችላል?

ይህም ኬኘ ወይም የኛ ልትል ነዉ በሉኝ እንጂ።

አይዴለም። መልሱን ሳይኖረኝ ነዉ ጥያቄ የምጠይቀዉ። ከሆነ ሌላ ምዕራፍ ኣስጀማሪ ይሆናል።

ህዳሴ አዴሱ ከሆነ፣ የአዲስ መሠረቱ አዲ ከሆነ አዲስ አበባ አዴሳ አባቦ መሆኑ ነዉ ወይ ያስብላል። በሁለት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ኣንድ ትርጉም ያለዉ የከተማ ስም። ለኬኘ፣ የኛ ክርክር ፍትሕ መሆን የሚችል።

ወደ ፍትሕ ርዕስ የሚመልሰን። ክርክር ተፈታ ተብሎ ፍትሕ የሚባል። ተፈታ፣ ፈታ፣ ፉተኤም ኣንድ መሠረት ያላቸዉ ኣይዴለም?

ዘመናዊ ፍርድ ቤት ዉስጥ ተስተካክሎ የተቆረጠ ዱላን ጋቭል እያሉ መረጃ እና ማስረጃን በማመዛዘን ፍትሕ መስጫ ሆነ።

የጨመሩበት እስር ቤትን ነዉ። ካልተሳሳትኩ በባህል ያልነበረ።

ይህ ሁሉ ለህዳሴ በቂ ብሬይንስቶርሚንግ መሆን ይችላል። ኣይችልም?

ይህን ርዕስ እመለስበታለሁ።