Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum



Horus
Senior Member+
Posts: 40218
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መስቀል፡ ሰዎችን ሕዝብ የሚያደርግ ካልቸር ነው! ማየት ማመን ነው!!

Post by Horus » 27 Sep 2024, 15:13

የሰው ልጅ እንደ ማንኛውም ህያው ፍጡር እንሰሳ ነው። ሰውን ከእንሰሳ ለይቶ ሰብአዊ ያደረገው በሁለት እግር የሚሄድ እንሰሳ ስለሆነ አይደለም፤ በአንድ ካልቸር ውስጥ ስለተወለደና የዚያ የተወለደበትን ማህበረ ሰብ ካልቸር ተምሮ፣ የዚያ ካልቸር ክህሎት፣ ችሎታ ፣ እውቀት ቀስሞ ራስ ቻይና ራስ መር የሰው ልጅ ስለሚሆን ነው።

በሌላ አባባል ካልቸር የአንድ ሕዝብ ሕይወት ክህሎት ነው። ካልቸር የሌላው ሕዝብ ክህሎት አልባ፤ ኢንተለጀንስ የሌለው ፍጡር ነው። የሚያስብ፣ የሚሰራ፣ የሚፈጥር ፣ የሚሻሻል ፣ የሚለወጥ ሰው የሚፈጠረው በካልቸሩ አማካይነት ነው ። በእምነት ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በሌላም መስክ ወደ ፊት የሚራመዱ ሕዝቦች ካልቸር ያላቸው ብቻ ናቸው።

ካልቸር የሌላው ሕዝብ የእንሰሳ መንጋ ነው ። መልካም መስቀል!



Post Reply