አያያዙን፥ አይተው ጭብጦውን ቀሙት፤
ስብሰባው ሲሰልቅ ጡጦውንም ደገሙት
መምራቱን ባይችል ስልኩንም ዘጉበት
መናገር፥ እንዳይችል መንግስቱ ሲፈርስበት
ሃሎ አሜሪካ ሃሎ ደቡብ አፍሪካ
መልስ አልተገኘም ደብርፄ ቢያንዃዃ
ስልጣኑን ነጥቀው ሰጡት ለወዲ ረዳ
ደብርፄ ተንቀዋለለ በአውላላ ሜዳ
ስብሰባ አበዛ ቢወግጡት እምቦጭ
አለቀ ዘመኑ ገፉት ወደ ውጭ
መንገድ ነው ብሎ እርሱ የሄደበት
አየሁት፥ ባህር፥ ገብቶ ሲንቦራጨቅበት
ወይ ወደፊት አይሄድ አይመለስ፥ ኻላ
ደብርፄ ግራ ገባው በብልጦች ተበላ
ስዬ ጌታቸውን ይዞ በሞግዚትነት
ይገባኛል አለ ትግራይን መግዛት
ከፋፍሎም ቢሆን ባአውራጃነት
የአብይ አሽከር ብንሆንስ ምን አለበት
ግሪን ሌጋሳውንም እንዘምርለት
የድሃ ቤት አፍርሰን እንደስለት
ማእድ ማጋራትም እንዳይቀርበት