ወንጪም እንደዚሁ የብዙ ስመ-ጥር ሰዎች መፍለቂያ ናት፣ ከሁሉም በላይ የእነ ጀግነዉ ሀብተጊዮርጊስ ድነግዴ ና የነ ገረሱ ዱኪ ትዉልድ አከባቢ ናት፣ የምያምር የተፈጥሮ መልከዓ ምድር ያለት ና በዛሬዉ አከላል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አከባቢ ናት።
እኔ አከባቢዉን ለመዘርዘር አይደለም ዛሬ የመጣሁት። አንድ ትልቅ ልዩነት ሰሞኑን ስለተመለከትኩኝ ነዉ፣ አንዱ በቪዲዮ ተቀርዖ ሌላዉ ደግሞ በፊልም መልክ የቀረበ ክዉን ነዉ።
ሳላሌ ሕዝቡ ተሰብስቦ፣ ገነ ለአቅመ-አዳም የልደረሱ ልጆቹን በበሬ ቀንበር ጠምዶ ስለማመጥ አይሁኝ፣ ለሰላም ብሎ ነዉ ይህ ሁሉ የተደረገዉ፣ እግዚዮ ብሎ ስማፃን አየሁኝ። ነገሩ ቀረብ ብዬ ሳየዉ ግን የራሱን ልጆች ነዉ የምለምነዉ፣ የምሰግድላቸዉ። ከራሱ የወጣን አካል በቤቱ መግራት አቅቶት አሁን ወደ መለማመጥ ገባ፣ እግዚዮ ብሎ ይማፃነዋል፣ ያሳዝናል፣ ሕዝቡ ፊዳዉን እያየ ነዉ፣ ወጥቶ ሠርቶ መግባት አልቻልም፣ ንብረት መገንባት አልቻልም፣ ይዘረፋል፣ ይገረፋል፣ ይገደላል። በቁሙ ስቃይ ላይ ወድቆዋል። በራሱ ልጆች እጅ።
ወንጪ ደግሞ (ብያንስ በፊልም ደረጅም ብሆን)፣ ይህ ፊልም እንደምያሳየዉ፣ ፊዳዉን የምያሳየዉን የራሱን ልጅ በራሱ ወንድም ና በወላጅ አባቱ አሳልፎ ለሕግ ስይስረክብ ይታያል፣ እግዚዮ ብሎ መስገዱን ሳይሆን፣ አጥፊዉን አሳልፎ ሥሰጥ ያሳያል። ፍልሙ ምን ያህል ለአከባቢዉ እዉነት ምን ያክል እዉነትነት አለዉ ማወቅ በልችልም አንድ የሰማሁት ታሪክ አለ። ይህም ወደ መጀመሪያ አከባቢ ሕዝቡን ፊዳዉን የምያሳየዉ ይህ እርኩስ ትዉልድ በወንጪ ላይ የተጀመረዉን የገበታ ለአገር የሆነዉን የኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ለማደናቀፍ ሞክሮ የአከባቢዉ ሕዝብ አይሆንም ብሎ ራሱ ምንትፍ አድርጎ ከራሱ ዉስጥ መንጥሮ አሳልፎ በመስጠቱ ነበር ቦኋላ ላይ ፕሮጀክቱ በአግባቡ መጠናቀቅ የቻለዉ ስባል በሚዲያ ላይ ሰምቼአለሁ፣ እንደሱ ከሆነ ደግሞ ይህ ፊልም እዚያ ላይ መሰራቱ የለምክንያት አይደልም ማለት ነዉ።
ሌላዉ በዚህ ረገድ ተመሳሳይ ዉጤት የስገኘ አከባቢ የወለጋ ዞኖች ናቸዉ ስባል ሰምቼአለሁ። አራቱም የወለጋ ዞኖች አሁን ላይ የተሻለ ሰላም አግኝቶ ወደ የተለመደዉ ስራዉ ተመልሶዋል ስባል ሰምቼአለሁ።
ሰላሌ ግን ከወንጪ ና ከወለጋ ትምህርት ወስዶ የራሱን ችግር መቅረፍ አቅቶት አሁንም ሌላ አካል መጥቶ ከችግር እንዲያወጠዉ ይመፀናል፣ ይሰግዳል። ይህ ለምን ይሆናል? ጠላቱ ከሩቅ አለመሆኑን መረዳት አቅቶት ነዉ? አይመስለኝም። የራሱን ልጆች ከመሓሉ መንጥሮ ወደ ሕግ መስጠት አቅቶት ከሌላ አካል ነፃነቱን ይማፀናል።
ትምህርት ይወሰድ እናላለን!
For the case of Selalie refer to the video I shared under the following link.
viewtopic.php?f=2&t=348824