Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
kebena05
Member
Posts: 3122
Joined: 10 Nov 2019, 14:58

የአስመራ "የኮሪዶር ልማት"

Post by kebena05 » 19 Aug 2024, 08:09

ጋሽ ሆሮር

ታሪካዊ ቅርሶችንና ሕንፃዎችን እያፈረሱ፣ ሚሊዮኖችን ለዘመናት ከነበሩበት ቀያቸው በግድ እያፈናቀሉ ለጥቂቶች ባለግዜዎችና "ባለሃብቶች" መሬታቸውን በመሸጥ፣ የአካባቢውን ስያሜ በመቀየር፣ በስመ የኮሪዶር ልማት ስንቱን እያስለቀሱ ለጥቂቶች ሲባል ዛሬ እንደ ካዛንችስ ቡናቤቶች በተለያዩ መብራቶች ከተማውን አሸብርቀው እንደነ ሽማግሌው ሆሮር አይነቱ፤ ከተማዋን ይኸም እይዋት አሸብርቃለች ይሉናል።

የአስመራ ውበቷ በግዚያዊና ዘላቂነት በሌለው መንገዶች በማሽብረቋ ሳይሆን፤ ቅርሶቿን ጠብቃ፣ ነዋሪዎቿን ሳታፈናቅል ታሪካቸውንና ትዝታዎቻቸውን በመጠበቋ ደስተኛ ነዋሪዎቿን በማፍራቷ ነው።

Please wait, video is loading...