ቅን አስተሳሰብ ያሎት ስለምመስሉን እና ቅን አስተሳሰብ በዚህ ፎረም ላይ በማካፈል ስለምታወቁ፣ እኛም የአቅማችንን ና የመሰለንን ቅን አስተሳሰባችንን (ምልከታችንን) ልናጋረዎ ወደድን፣ ፍቃዶ ሆኖ ከሰሙን።
ኤርትሪያ እደገት የምባል ነገር ያጣችዉ አገሯን ከወረረ ለመጠብቅ ብላ ነዉ ብሎናል፣ ወረረዉም ደግሞ ከሌላ አካል ሳይሆን፣ ከራሱ ከ30 አመት በፊት አገርዎ ነፃ ሆንኩኝ ከምትለዉ አገር ወይም አካል መሆኑን እርሶም አልሸሸጉም፣ የተሳሳትን ነገር ከለ አርሙን በደስታ እንቀበላለን።
አገሮትን ነፃ አዉጥቶ 20 አመት ና ከዚያ በላይ ነፃ ከወጡበት አከል ራሱ መልሶ አገሮዎትን ስጠብቁ ኖሩ ማለት እንዴት ነፃ ወጡ ለማለት ያስደፍራል? ነፃ መዉጣት ራስን ከስጋት ነፃ መድረግን አይጨምርም ማለት ነዉን?
የሆነ ነገር ግልፅ አይደለም እዚህ ላይ።
የለበለዚያ ነፃነቱ ሙሉ ሳይሆን የጎደለ መሆን አለበት፣ እንደ ቅን አስተሳሰባችን።
ይህ ጉድለት መቼ ነዉ የምነሰዉ ና ኤርትሪያ ወደ የተሟላ የእድገት ጎዳኗዋ የምትገበዉ? ለዚያስ ምን ዋስትና አለ? እርሶ ያሉት ዲማርኬሽን ነዉ? እኔ እንደ ቅን አስተሳሰቤ ያ ዋስትና የምሆን አይመስለኝም። ጥርጣሬ አለኝ። የተዘባ ነገር የለ ይመስለኛል። እሱ ከልተስተካከለ የኤርትሪያ ስጋት የምቀጥል ይመስለኛል፣ አሁን ለለፉት የበከኑ 20 አመታት እንቆጫለን፣ ከ20 አመት ቦኋላም እንዲሁ ለለፉት 40 አመታት ብለን እንዳንቆጭ ምን ዋስትና አለን?
እርሶ እንደ አስታዋይ ሰዉ፣ የበሽታዉን ምልክቱን ትቶ ለምንድነዉ መንስዔዉን የማያክሙት? ለእርሶ እዉቀት ይህ ነገር የምከብድ አይመስለንም። ስምፕተሙን ትሪዕት እያደረጉ ከመኖር ጨክኖ መንስዔዉን ፈልጎ መስወገድ የተሻለ ብልህነት ይመስለናል፣ በእኛዉ በኢትዮጵያዊያን የመሓል ና የመስመር ዳኞች ምልከታ ና ጨዋነት። ለስህተታችን አስቀድመን ይቅርታ እየጠየቅን፣ ከስህተታችን እንደምንማር አስቀድመን ቃል እንገባለን።
አንድ የአገሬ ሰዉ አባባል አለ፣ በአፋን ኦሮሞ ነዉ፤
፣ ይላል። ትርጉሙምህን ታኔ ክርስትናን በዳሳ ለመተ ካሳ
የምል ምክር የምመስል አባባል ነዉ።የበዳሳ ክርስትና በዚህ ዙር ስለልተሳካ እንደገና አንሱት
እኔም በበኩሌ እርሶዎ ራሷ ካሉት በመነሳት ስገመግም፣ የኤርትሪያ ነፃነት ጉዳይ የጎደለዉ ነገር እንደለ ይሰማኛል፣ ስለዚህ እንደገና ተመልሶ እንዲያጤኑት በታላቅ ትህትህና እጠያቃለሁ፣ ለእኔ ብሎ ሳይሆን ለራሱ ወንድም ና እህት ለሆነዉ የኤርትሪያ ሕዝብ ወገኔ ስባል።
እስከዚያዉ ድረስ እርሶን ና የተቀረዉን ወንድም ና እህት የኤርትሪያ ሕዝብ (ከሻቦች በስተቀር) ይመቾት እንላለን!