ሳታፍር The territorial map of Tigray (old spelling “Tigre”) የሚል ጽሑፍ ይዘህ መጠህ ሰው ታጭበረብራለህ። TIGRE ትግረ ኤርትራ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ህዝብ መጠሪያ ነው፡ ቋንቋው ደግሞ ከትግርኛም ከኣማርኛም ይልቅ ለግዕዝ የቀረበ። (አራት ሚልየን ነጥቦች) አሁን ሂድና እዛው ያመጣሀው ካርታ ላይ ትግራይ የሚል ስም ፈልግ።
Meleket wrote: ↑03 Aug 2024, 02:45ከታላቁ ኤርትራዊ ድምጻዊ በረኸት መንግስተኣብ ትንሽ ግጥምና ዜማ ቢጤ ተውሰን እስቲ እናንጐራጉር
Axumezana ንMeleket ዝጸመቕካዮ ዕረ
መሪሩካ ዶ ሓቅነት ምስ ሰዓረ
ሰታትዮ እምበር ናበይ ድሕርድሕሬ ናበይ ድሕር ድሕሬ!![]()
እውነት ሁሌም ጣፋጭ ነች፤ ላልተቀበላት ሰው ግን ልክ እንደ ሓሞት መራራ ነች! ብለናል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።Meleket wrote: ↑02 Aug 2024, 10:28Axumezana wrote: ↑02 Aug 2024, 09:09ግራ የተጋባኸው ደብተራ መለከት፥ እስቲ ኤርትራ የምትላትን አገር እዚህ ጥንታዊ ማፕ ላይ ፈልገህ አሳዬኝ፤ ብቻ የትግራይ እካል ነበረች ብለህ መራራ እውነቱን እንዳትጎነጭ!
https://www.google.com/url?sa=t&source= ... zuqZOvOxFg
ኣዬ ወዳጃችን Axumezana ከመሰረቱ እውነት ከሆነ መራራ ሊሆን ኣይችልም እውነት ሁሌም ጣፋጭ ነች። እውነት ካልጣፈጠችህ እውነቱን አልተቀበልክም ማለት ነው።
ኤርትራ በዬትኛው ሂሳብ ነው የትግራይ አካል የምትሆነው። እንደ እናንተ ኣባባል ጥንት የምትሉት የኣክሱም ዘመነ መንግሥትን ነው። ያኔ ኤርትራ የትግራይ ነበረች ነው ልትለን የምትፈልገው? ትንሽ ሰው ይታዘበኛል አትልም? የኢትዮጵያ ነበረች ብትል እንኳን ይሻልህ ነበር። ነገር ግን ያኔም አሁንም ለወደፊትም ኤርትራ ኤርትራ እንጂ ትግራይ ሆና ኣታውቅም ብንልህ ቅር ኣይበልህ።
ያኔ በአክሱም ዘመን “ዓሰብ” የትግራይ ክልል ነበረች ልትለን ነው? ያኔ በኣኽሱም ዘመን ዳህላክ የትግራይ ነበረች ልትለን ነው? አዬ ወዳጃችን እኛ እኮ እያል ያለነው ታሪካችን ቅድመ ኣዅሱም ነው። ምስክራችንም የመጠራ የቆሓይቶ የኣዱሊስ የኣስመራ የናቅፋ የዳዕሮ ጳውሎስ የሰምበል የማይተመናይ ገና ያልተበረበሩት በሺዎች የሚቆጠሩት መሰል ስልጣኔን የሚገልጹት “ዑናዎቻች” ናቸው። ያኔ እነዚህ ሁሉ የትግራይ ነበሩ በለና።![]()
ትግራይን እኮ ከኤርትራ ኣገር ያቀኑ ዘንድ በላክናቸው አንዳንድ ኣካላቶቻችን ኣማካኝነት የቆረቆርናት ነች። ዓድዋን ማን ነው እንዴ የቆረቆራት እስቲ ለማተብህ ብለህ መስክር ወይም የመንበረ ሰላማን “ሊቃዉንት” ጠይቅ ወዳጃችን። የጸዓዘጋው ራስ ዓንደሃይማኖት ይባላሉ የዓድዋ ቆርቋሪ!![]()
ኣንተ የ19ኛውን ምእተ ዓመት የጀርመኖች ካርታ ኣቅርበህ ኤርትራን አሳዩኝ ትለናለህ? እስቲ ኣንተው እዛው ካርታ ላይ ኢትዮጵያንና ትግራይን ኣሳየን “ትግረ”ን አላልንህም። ትግረ የኛ የኤርትራዉያን ብቸኛ ይዞታ መሆኑ አትዘንጋ። እስቲ ትግራይ ውስጥ ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በ”ትግረ” ቋንቋ የሚያወሩ ዜጎች ኣሏችሁን? አንዴም አስመራን ራስ ኣሉላ ናቸው የቆረቆሯትም ብለሀናል፡ ምን ዬማትለው አለህ።![]()
እስቲ ግዜ ካገኘህ Travels of Jesuit in Ethiopia የሚል መጽሃፍ ላይ የሰፈረውን ታሪካዊ ካርታ ተመልክተህ ተመለስ። "The Abissine Empire as it now is and the true source of Nile" በሚል ርእስ ስር ታገኘዋለህ። ዓንሰባ ጋሽና ባርካ የተሰኙት የኤርትራ ወንዞች የት እንደተመደቡ ፍንትው ብሎ ይታይሃል። መረብና ኣዋሳኙ ደጋማ ክፍልም TIGRE ተብሎ ተጠቅሷል ትግራይ ዬለ ኢትዮጵያ ዬለ። አስመራንም እዛ ካርታ ላይ ፍንትው ብላ ታገኛታለህ፡ ቅን ልብ ካለህ ቢለናል እኛ ኩሩዎቹና ቀብራሮቹ እንዲሁም ትሑቶቹ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
ያንተው ምንጭ እንዲህ ይለናል The territorial map of Tigray (old spelling “Tigre”) ። ኣቤት ኣለማፈር ኤርትራ ውስጥ Tigre “ትግረ” የሚባል ለግዕዝ ይቀረበ ብሔር የሌለ ይመስል። ትግራይ ድሮ ትግረ ይባል ነበር ሊለን ይቃጠዋል። በል ማንም ቀጠናችንን በቅጡ ያልረገጠና ያልመረመረ “ተመራማሪ” የጣፈውን እያመጣህ ኣታጭበርብር።
ትምህርቱ ደህና ነው ኣይደል እየገባህ ነው?
![]()