Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12906
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

ሌላዉ የዛሬዎቹ ኢትዮጵያኖች በሽታ።

Post by DefendTheTruth » 12 Jul 2024, 16:44

ባለፈዉ እዚህ ፎረም ላይ ኣካፍዬ ነበር፣ በሥሳይ አጌና አንደ ተገለፀዉ ጠቅሼ፣ ብዙ ኢትዮጵያኖች በቅጀት ዉስጥ ነዉ ያሉት ማለቱንና ነገሩ በጣም ትክክል መሆኑን።

ዛሬ ደግሞ በጣም የተስፋፋዉን ና ብዙ ኢትይጵያኖችን እያጠቃ ያለዉ በሽታ የራስን ስህታት የለመቀበል ኣባዜ። የሞራል ዝቅጠት!

እኔ ራሴ ከብዙ ሰዎች ጋር በግሌ ሀሳብ ተለዋዉጬያለሁ፣ አስተያያታችንን ተለዋዉጠናል፣ ክርክር ዉስጥ ገብተናል። በመጨረሻም ነገሮች እያጠሩ መጡ ና የዉሸት መንገድን ኣጋለጠዉ፣ ከእኔ ጋር የተከራከሩት ሰዎች፣ አይ ተሳስተን ነበር፣ አንተ ያልከዉ ሀሳብ ትክክል ነበር አይሉኝም፣ እኔ ደግሞ እገረማለሁ፣ ሰዉ እንዴት ብሆን ነዉ የራሱን ስህተት መቀበል የምያቀተዉ ብዬ እገረማለሁ።

ለከስ ነገሩ የኢትዮጵያኖች እንደምክ በሽት እየሆነ ነዉ። የሞራል ዝቅጠት።

ተሳስቼ ነበር ማለት ትንሽነት ወይም ኣለመወቅ ሳይሆን፣ የሞራል ልዕልና እና እዉቀት ነዉ።

እዚህም ፎረም ላይ ያሉት ጉጠቶች ሥሳሳቱ ስህተታቸዉን ከመቀበል ይልቅ፣ ሄዶ ሌላ ንክ ፈልፍሎ መመለስ ነዉ። የሞራል ዝቅጠት!