Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC- የትግራይ ከተሞች ነዋሪዎችን በፍርሃት እያራደ ያለው የእገታ እና የዘረፋ መበራከት

Post by Za-Ilmaknun » 14 Jun 2024, 19:06

ትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አልታወጀባትም፤ በርካታ ሰዎች ግን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በኋላ ከቤታቸው ከመውጣት ራሳቸውን ያቅባሉ።

ለደኅንነታቸው የሚሰጉ ነዋሪዎች ጎረቤቶቻቸው በስለት እና በጦር መሳርያ ጥቃት ሲደርስባቸው እና ሲዘረፉ ቢያዩ፣ አልያም የድረሱልኝ ጥሪ ቢሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለትን ይመርጣሉ።

ለዚህ ታሪክ ሲባል ቢቢሲ ያነጋገራቸው በርካታ ሰዎች በክልሉ እያጋጠመ ያለው በሕጻናት እና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው እገታ፣ በሌሎች ላይ በሚደርሰው ጥቃት እና ሞት በፍርሃት ውስጥ እየኖሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሽረ፣ በዓዲ ዳዕሮ እና ሸራሮ ከተሞች ዝርፊያ እና እገታ ይፈጸማል። የፋሲካ ጾም አካባቢ በሸራሮ አንድ ሰው ከቤቱ ታግቶ ሲወሰድ አይቻለሁ። እስከ አሁን የገባበት አይታወቅም። በሽረ ከተማም መኪና ይዘው በመጡ ግለሰቦች የታገተ ሰው አለ። ሆኖም እነዚህን አጣርቶ መረጃ የሚሰጥ አካል ስለሌለ፣ ሰው በምን ምክንያት ዒላማ እየሆነ እንዳለ አይታወቅም።”

ተማሪ ማኅሌት እንደጠፋች ወደ ቤተሰቦችዋ ስልክ ተደውሎ መታገቷንና እንድትፈታ “ሦስት ሚሊዮን ብር” እንዲከፍሉ እንደተነገራቸው በወቅቱ ቤተሰቦቿ ለቢቢሲ ተናግረው ነበረ።

የአድዋ ከተማ ፀጥታ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ገብረ ዮሐንስ ባለፉት ሳምንታት በክልሉ ለሚገኙ የሚዲያ ተቋማት በሰጡት ቃል፣ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቢኖሩም በተማሪ ማኅሌት ጉዳይ ግን እስከ አሁን መረጃ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል።

የተማሪዋ መታገት እና የደረሰችበት አለመታወቅ፣ ከአድዋ ከተማ በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የአክሱም ከተማ ላይ ቀላል የማይባል ስጋት ማሳደሩን የከተማዋ ኗሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገርም በከተማዋ ማጅራት በመምታት የሚፈጸሙ ዝርፊያዎች መበራከታቸውንም ጠቅሰው፣ በሳምንት ቢያንስ ሁለት ሰው ጥቃት እንደሚፈጸምበት ያስረዳሉ።

“ከ12 ሰዓት ጀምሮ በነጻነት መንቀሳቀስ አይቻልም፤ ጠዋት ተነስቶ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድም አይታሰብም። ገንዘብ ይዞ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እጅግ ከባድ ነው። ያለው አማራጭ የአስቸኳይ ጊዜ እንደታወጀበት አካባቢ በጊዜ ወደ ቤት መግባት ነው” ሲሉ የከተማዋ ኗሪ የሆኑት መምህር ሙሉ ተጠምቀ ገልጸዋል።

ይህም ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች እያስከተለ ነው የሚሉት መምህር ሙሉ፣ በተለይ በክልሉ እያጋጠመ ያለው የሰዎች መታገት እና ገንዘብ መጠየቅ ሥነ ልቦናዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆናቸውን ያስረዳሉ።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cldd9ny9l7ro

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: BBC- የትግራይ ከተሞች ነዋሪዎችን በፍርሃት እያራደ ያለው የእገታ እና የዘረፋ መበራከት

Post by Za-Ilmaknun » 14 Jun 2024, 19:14

ከትንሽ እስከ ትልቅ የክልሉን ሀብት የሚዘርፍ፣ የክልሉ የጦር አዛዦች፣ ባለሃብቶች እና ግለሰቦችን የያዘ፤ በጥቅም የተሳሰረ መደብ” መኖሩ ችግሮቹ በሕብረተሰቡ ላይ እንዲንጸባረቁ እያደረገ ነው ይላሉ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ የመንግሥት ቅርጽ እንዳይኖረው እየታገለው ነው፤ በኢትዮጵያ የተጠያቂነት የሚቀርብባቸው ግለሰቦች እዚያ ነው ያሉት። . . . ቁጥሩ ትንሽ የማይባል የታጠቀ ኃይል በተለያዩ አካባቢዎች ተበትኗል፤ ለ30 ዓመታት በኢትዮጵያ ያዳበረውን የዝርፍያ ተሞክሮ የያዘ ኃይል ትግራይ ነው ያረፈው” ሲሉ ችግሩ ሥር የሰደደ መሆኑን ያስረዳሉ።

Post Reply