Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

“አላማ የለሹ የ ኦህዴድ ሰራዊት መጨረሻው ከደርግ ሰራዊት በባሰ ሁኔታ ማለቅና መበተን ነው” ሸለቃ ማሞ

Post by Za-Ilmaknun » 12 Jun 2024, 18:58

በ ሲኖ ትራክ አናቱ ላይ የነዳበትን የትህነግ ጉጀሌ አቅፎ ፣ ከ መአት ያዳነውን አማራ እየፈጀ ያለው የ ኦህዴድ ሰራዊት፣ በቅርቡ ከነግሳንግሱ ውርደት ተከናንቦ እንዲጠፋ በ አለቆቹ ተፈርዶበታል፣፣

ከየጉዳንጉዱ እያፈሰ በየማሰልጠኛው ባጎረው ምናምንቴ ሁላ ፅኑ አላማ ታጥቆ በጀግንነት የሚዋጋውን የ አማራ ህዝብ አሸንፋለሁ ብሎ የሚቅበዘበዘው ኦህዴድ ከ በ አንድ አመት ጦርነት ያለውን ሁሉ እያጣ ነው፣፣


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: “አላማ የለሹ የ ኦህዴድ ሰራዊት መጨረሻው ከደርግ ሰራዊት በባሰ ሁኔታ ማለቅና መበተን ነው” ሸለቃ ማሞ

Post by Za-Ilmaknun » 12 Jun 2024, 19:18

በ ዘጠኝ አቅጣጫ እልቆ መሳፍርት አራዊት ያሰማራው ኦህዴድ፣ በ አምስት በኩል የተሰማራው ተበልቶበት ሌላውም መውጫ መግቢያው ጠፍየቶ እየተወቀጠልህ ነው!! 💪🏼 ፋኖ በስሙ ጀግንነት አለ! ድል አለ!!


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: “አላማ የለሹ የ ኦህዴድ ሰራዊት መጨረሻው ከደርግ ሰራዊት በባሰ ሁኔታ ማለቅና መበተን ነው” ሸለቃ ማሞ

Post by Za-Ilmaknun » 13 Jun 2024, 12:57

“በኦፕሬሽኑ ላይ ኦፕሬሽን ተሰራበት!” ሲል ገልጾታል ፕሮፌሰር ፋኖ ኢያሱ አባተ፡፡ በበኮሎኔል ጃዋር ዲካ የተመራው ኦፕሬሽን በአማራ ፋኖ ፍርክስክሱ ወጣ! በዘጠኝ አቅጣጫ የገባው የብልጽግና ሰራዊት ዘመቻ በአማራ ፋኖ አሸናፊነት ተደመደመ፡፡ :mrgreen:

የአማራ ፋኖ በጎንደር ም/ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ፕሮፌሰር ኢያሱ አባተ እንዳስታወቀው የአማራ ህዝብ ልጅ የሆነው የፋኖ ሰራዊት በአገዛዙ ላይ አስደማሚ ድል ተቀዳጅቷል፡፡ የአገዛዙን “ዞኑን እናጸዳለን” በሚል የተከፈተ ዘመቻ በመመከቱ ሂደት የአማራ ፋኖ በጎጃም አካል የሆነው በኢንጂኔር ማንችሎት እሱባለው የሚመራው ሰራዊት ከፍተኛ ተጋድሎ ፈጽሟል፡፡

የአገዛዙ ሰራዊት በሌሊት እንቅስቃሴ አደረገ፡፡ ከባህር ዳር በጭስ አባይ በኩል ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ሀይል ነው ሲያንቀሳቅስ ያመሸ፤ ያደረው፡፡ በጠዋት ደግሞ የግና ጭርቆስና ወደ ሜጮ አንጦ በረሀ አድርጎ ወደ ወፍ አርግፍ መገንጠያ ላይ ንግስተ አዜብ ተራራ የኢንጂኔር ማንችሎት እና የሻለቃ ጸዳሉ ሀይል ጋር ከፍተኛ የሆነ ግጥሚያ ተደረገ፡፡ በዚህም ጠላት ሙትና ምርኮኛ ሆኖ አመራር ጭምር ተመትቶበት እስከምሽት ድረስ ማንሳት ያልቻለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ይሄ ሀይል ወደ ወፍ አርግፍ እንቅስቃሴ በማድረግ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦርን ከበባ ለማድረግ ሞከረ፡፡ ከሀሙሲት አንበሳሜ አርብ ገበያ የመጣው ሀይል ደግሞ የተወሰነው ወደ ገላውዴዎስ መስመር፤ የተወሰነው ደግሞ ወደ ማክሰኚት ወፍ አርግፍ አቅጣጫ ጉዞ አደረገ፡፡ ከደብረታቦር በማህደረ ማርያም ልጫ፡፡ ከእስቴ በሁለቱም አቅጣጫ፡፡ በድሮው የባህር ዳር መስመር በፒስታው በኩል እንቅስቃሴ አድርጎ ግንድ አጠመም ላይ ያኛውን ሀል መጠበቅ ጀመረ፡፡ በአስፋልቱ ጉዞ ያደረገው ደግሞ በጅብ አስራ፤ በቀጭን ሜዳ ጅባ ስራ፤ ቀጭን ሜዳ ከአንዳቤት ከመጣው ሀይል ጋር በመገናኜት ጅባስራ ግንድ አጠመም፡፡ አሁንም በተመሳሳይ ከአንዳቤት በበቅሎ ፍለጋ የወጣው ሀይል በቅሎ ፍለጋ አንዳቤት ከአንደኛዋ ሻለቃ ጋር ከገጠመ በኋላ የሚመታው ተመትቶ የተረፈው ጉዞውን ቀጠለ፡፡

የሚቀጥለው ጉዞአቸውሳና ወደሚባለው የደራ ወረዳ አንደኛው ቀበሌ ነበር፡፡ እዚህ ቤት ከሜጄር ጀኔራል ተወርዋሪ ክፍለጦር ጋር በተደጋጋሚ ገጥመው ብዙ ጊዜ ተመትተዋል፡፡ እዚህ ላይ አገዛዙ ወደ ዘጠኝ ጊዜ ማጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡ ያንን ቦታ አስፍቶ በመያዝ ነበር ጉዞ ለማድረግ የተሞከረው፡፡ ከወፍ አርግፍም የተንቀሳቀሰው ከእስቴ፣ ከአንዳቤት፣ ከደብረታቦር፣ ከአንበሳሜም ያለፈው ሀይል ሙሉ ወደ ደዘጠኝ አቅጣጫ ነው ከበባ ለማድረግ ሞክሮ የነበረው፡፡

ይሄ ሀይል በከፍተኛ ሁኔታ ነው የተቀለበሰው እና አሁን ሁሉም ሀይል ወደ ሶስት አቅጣጫ ብቻ የመሰብሰብ ሁኔታ ይታይበታል፡፡ በዘጠኝ አቅጣጫ ነበር ለማስፋት የሞከረው፡፡ እኛም ከዚያ በላይ የምናውቀው ጓዳ ጎድጓዳ ቀበሌ በመሆኑ በማስፋት፣ በመቁረጥ፣ እየሳቡ በመምታ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበብና ታክትኪ በተሞላበት ሁኔታ ነው ጥቃት ስናደርግ የዋልነው፡፡ በዚህም ንግስት አዜብ ተራራ ላይ የነበረው ከግና ጭርቆስ ወደ ወፍ አርግፍ እና ሜጮ መገንጠያ አካባቢ የነበረው የእነ አርበኛ ጸዳሉ እና ኢንጂኔር ማንችሎት ሀይል ያደረሰው ጥቃት ጠላትን ቅስሙን ሰብሮታል፡፡

በተመሳሳይ የአንዳቤት ብርጌድ ደግሞ የወረዳዋን ከተማ ወለሽን ሙሉ በሙሉ ነው ተቆጣጥሮ የነበረው፤ ይሄም ጠላት ይዞታውን በማስፋት ወደ ቀበሌዎች ለመውረድ እና ዞኑን አጸዳለሁ ባለበት ሰአት ወረዳ ሲነጠቅ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥ ውስጥ ነው ገብቶ የነበረው፡፡ በዚህም ከባድ መሳሪያ ማለትም ብሬል እና ዲሽቃ ተኳሾች ጭምር ናቸው የተደመሰሱበት፡፡ ብዙ የነፍስ ወከፍ መሳሪያም ተገኝቷል አንዳቤት ከተማ ላይ፡፡

መካነ ኢየሱስ ከተማ ላይ የነበረው ሙሉ ውጊያ ደግሞ በሻለቃ ብርቃየሁ የሚመራው ጦርና በእነ ሻለቃ ቆራጡ እንዲሁም ክፍለጦር አዛዦች በሚመራ የተጠና ኦፐሬሽን ወደ ልጫ ገላውዴዎስ በማቅናት ከሜጄር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ጋር ተገናኝቷል፡፡ ከዚህም በኋላ በበቅሎ ፍለጋ፣ ጅባስራ ማርያም አድርጎ እስቴ ከተማን ተቆጣጥሯል፡፡ ሙሉው መካነ ኢየሱስ ከተማ በዚህ ሁኔታ በፋኖ እጅ ወድቋል፡፡ ከሰሞኑ ንጹሀን ላይ ጭፍጨፋ ተፈጽሞ ስለነበር ፋኖው ህዝቡን እያበረታታ ነው የዋለው፡፡

ማህደረማርያምም ላይ እስከ ሰባት ሰአት ድረስ ውጊያ አድርገናል፡፡ ስለዚህ እኛ ጠላት ካሰበው ሶስት አራት እርምጃ ቀድመን እይሄድን ዞኑን አጸዳለሁ እያለ በዘጠኝ አቅጣጫ የገባውን ወራሪ የብልጽግና ሰራዊት ህልሙን አክሽፈን በአሸናፊነት ወጥተናል፡፡ ይህ ኦፐሬሽን በኮሎኔል ጃዋር ዲካ የሚመራ ሲሆን ከፍተኛ እቅድ የተደረገበት ነበር፡፡ እቅዱም “ዞኑን አጽድተን እናስረክባለን” የሚል ነበር፡፡ “ዞኑን አጽድተን ትግሉን እናጠናቅቃለን” በሚል መንፈስ ነው የጀመሩት፡፡ እኛ ግን በኦፕሬሽኑ ላይ ኦፕሬሽን ሰራንበት፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ከአንዳቤት አንድ የቆሰለ ፋኖ፤ ከሜጄር ጀኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ደግሞ ሙሉ ደፈጣ ተደርጎባቸው ስለነበር ቆሚሳ ላይ አንድ ሲሰዋብን አንድ ቆስሏል፡፡ የአገዛዙ ሰራዊት ግን ብዙ ሙትና ቁስለኛ ስለነበረው በመኪና ነበር እየጫነ ሲያመላልስ የነበረው፡፡

https://mereja.com/amharic/v2/966159

Post Reply