Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6880
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ምሁራን፥ እስቲ ዮሓንስ ለታ ስለኢትዮጵያ ፖለትካ ኣስቦ ያልተፈነገለ ሀሳብ ኣለ?

Post by Naga Tuma » 17 May 2024, 17:29

ዮሓንስ ለታ የትዉልድ ስሙ ነዉ፣ የትግል ስሙ ኣይዴለም። ይህ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተወልዶ ያደገዉ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ንቅናቄ ልጅ እንጂ አባት ኣይዴለም።

የኦሮሞ ንቅናቄ ልጅ ቢሆንም የኦሮሞ ትግል ዉስጥ እንደኖረ ነዉ የሚገባኝ። ማንም ሰዉ ላመነበት በኣግባብ መታገል መከበር ኣለበት።

ይህን ሰዉ በአካል ተገናኝተን ኣንተዋወቅም። ኣልፎ ኣልፎ ሚድያ ዉስጥ ሀሳቡን እሰማለሁ። ኣንድ መጽሓፉን ገዝቼ ኣንብቤኣለሁ።

አሰፋ ጃለታ ፕሮፌሰር ሆኖ ከጻፈዉ ዮሓንስ ለታ ፕሮፌሰር ሳይሆን የጻፈዉን መጽሓፍ ነዉ የበለጠ ተነባቢ ሆኖ ያገኘሁት።

ለመጀመርያ ግዜ ድምጹን ከሰማሁኝ እና አስተሳሰቡን ካነበብኩኝ ግዜ ጀምሮ ያከበርኩኝ ኣሉ፣ የታዘብኩኝም ኣሉ።

እኔ የሚለፋ ሰዉ ለምን ይሳሳታል ኣልልም። ተቀምጦ ከማይሳሳት ተንቀሳቅሶ የሚሳሳት ይሻላል። ባደግንበት አከባቢ ጠባሳ የሌለዉ እግር የሚቀመጥ እግር ነዉ።

እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ ግልጽ የሆኑ ስህተቶች ከታወቁ በኋላ ግልጽ ስህተቶች ነበሩ ማለት ኣለመቻል ነዉ። ግልጽ ስህተት ላይ ስህተት መጨመር የታሪክ ድፍድፍ መተዉ ነዉ።

እስከዚህ ግዜ ድረስ ግልጽ ስህተቶቹን ስህተቶች ነበሩ ሲል ሰምቼ ኣላዉቅም። ብሎ እኔ ያልሰማሁ ከሆነ ያለመስማት ስህተቱ የእኔ ነዉ።

የኢትዮጵያ ምሁራን፣ እስቲ ስለኢትዮጵያ ፖለትካ ያሰበዉ የትኛዉ ነዉ ያልተፈነገለዉ?

የጻፈዉ መጽሓፍ ዉስጥ ኢትዮጵያ መክሰም ኣለባት ሲል ኢትዮጵያ ኣለሁ ኣለች።

ኢትዮጵያ ተወልዶ ኣድጎ ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደራደራለን ብሎ ነበር። እንደዚህ አይነትን የጨቅላ ፖለትካ ክርክር ታዝቤ ነዉ ያለፍኩኝ። ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዛ ዓይነት ክርክርንም ታዝቤኣለሁ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ተወላጅ ዜጋዋን ለእንደዚህ አይነት ጨቅላ የፖለትካ ክርክር ቆሜ ልጠብቅህ የምትል ኣይመስለኝም። ይመስላችኋል?

ካልዘነጋሁ አሜሪካ በተቋቋመች ሁለት መቶኛ ዓመት ላይ የጸደቀዉን የፖለትካ ፕሮግራም ይዞ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተመጣጣኝ የሚባል ያህል ግዜ ቢሸፍትም ከመለስ ዜናዊ ጋር ሸፍተዉ ቁምጣ የለበሱ ባለጎፈሬዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሲታዩ ከእሱ ጋር የሸፈቱት የት እና ምን ያህል እንደታዩ በጥልቀት ኣላዉቅም።

የነበሩት ጥቂቶች፣ በደርግ ሰልጥነዉ የተቀላቀሉትን ጨምሮ፣ ከፖለትካ ተቀናቃኙ ጋር ለመደራደር ወደ በረት ተነድተዉ የግጭት ሰለባ ሆኑ።

ሕወሃት የበላይነት ኣግኝቶ ሰዉ በደጃፉ መደፋት ሆነ። ሰዉ ለትግል ብሎ ከቤቱ ወጥቶ የተደፋበት ቦታ የማይታወቅ ሆነ። በባህልም፣ በታሪክም ተሰምተዉ የማይታወቁትን ሃገር ታዘበ። የጣልያን ወረራ ግዜ ወጣቶች ተነስተዉ ተከብረዉ ሕዝብ ያስከበሩበት ሃገር ሕዝቡ ተዋረደ።

እስርቤት የሚናገረዉ ኦሮምኛ ነዉ እስከመባል ደረሰ።

በዛ፣ መለስ ዜናዊ ያርመዉ ሲባል ያለዕድሜዉ እስከማለፍ ደረሰ።

ለትግሉ ዓላማ የጎሳዎች ማንነት ክልል ይፈተዋል ብሎ ቢከራከር ሲታሰብ እሱን ያፈሩትን ጎሳዎች ብያንስ ወደ ሁለት የጎሳዎች ክልሎች የሚሰነጥቅ ሆነ።

የሃገር ፊደል ኣይመችም ቢባል ሲስተዋል ፊደል ዐን ከሮ ገንጥዬ ዐ እና ር ያላደረኩ ባለ ሀ ግዕዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሳልስ፣ ሃ ራብዕ፣ ሄ ሓምስ፣ ህ ሳድስ፣ ሆ ሳብዕ ነኝ የምትል ሆነ።

አባቱ የተቀበለዉ የካቶሊክ ፕሮቴስታንት ልጅ እንጂ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኣትመቸኝም ቢል ተዋህዶ የፕሮቴስታንት አባት ማርቲን ሉተርን ዕዉቀት ያስቀሰምኩኝ ነኝ የምትል ሆነ።

ይህን ሁሉ ሳላዉቅ ነዉ የጨቅላዎች ፖለትካ ክርክርን ታዝቤ ኣስተዋይነት ይሆናል ብዬ እርስ በእርስ መናቆር እንዲከስም የኢትዮጵያ የባህል ሕዳሴ ያልኩኝ።

ይህ ጥሪ ጠብ ያለ ወይም ያላለ ቢሆን በኣብዛኛዉ በደርግ ግዜ የተገኘ ዕዉቀት ለዚህ እንደባከነ ኣዉቃለሁ። የሃገር ምሩቃንን መንገድ ላይ ያላንከራተተዉ ደርግ የዚህ ዕዉቀት አባትነት ከሁሉ በላይ ያምርብኛል ቢል በሰዉ ቢነፈግ ታሪክ የሚነግፈዉ ኣይመስለኝም።

ለምሳሌ ዮሓንስ ለታ በህይወት ዘመኑ ስንት የካልኩለስ ኮርሶችን እንደወሰደ ፍንጭ ዬለኝም።

ያልተፈነገለ ሳይንስ ኣለዉ እንዳልል ያሳተመዉ የሳይንስ ስራ መኖሩን ኣላዉቅም።

የንን ሁሉ ግዜ ምን ሲታገል ኖረ ቢባል የተነቀፈ ስም በተከበረ ስም እንዲተካ ለፍቻለሁ ይላል። በጀ ብትለዉም በወሬ ወራሪ ነበርኩ የሚል ያስመስለዋል።

ኣፍ እላፊ በጠራራ ጸሓይ፣ በደራ ገበያ ዉስጥ በቅጽበታዊ ዱላ ልክ ሲገባ ልጅ ሆኜ ኣይቻለሁ።

ቦረና የኦሮሞ አባት ኣይዴለም ብለህ መድረክ ላይ ብትጠይቀዉ መመለስ ይተናነቀዉ እና በትክክል ከመለሰ በኋላ ትክክለኛ መልስ መመለሱ ያበሳጨኛል ይላል።

እነዚህ ሁሉ ታሪክ የማይረሳቸዉ ስህተቶች ኣይዴሉም? እላይ እንደጻፍኩኝ ትግል ብሎ የሚንቀሳቀስ ሰዉ ለምን ይሳሳታል ኣይዴለም እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ። ግልጽ ስህተቶች ከታወቁ በኋላ ጨቅላነት መቀጠሉ ነዉ።

ኣስተዋይ የቻልኩትን ለፍቻለሁ፣ ያልሞላ ይሙላ ማለት ይችላል። ቢሆንም የለፋ ልፋትን የምያዉቅ እንጂ ልክፍት የሚሆንበት ኣይዴለም።

እጆችዋን ትዘረጋለች የሚለዉ ትንቢት በማያሻማ ሁኔታ ሲገለጥ የታሪካዊ ሃገር ዜጋ ሃገሩ መክሰም ኣለባት የሚል ትዕቢት የሚከስም ቢሆንም በመሃል ስንቱን እንቁጠር?