Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12909
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 11 May 2024, 15:31
ነጥቡን የሳትክ ይመስለኛል።
አብቹ ወይም አብችዬ ማለት መብትህ ነዉ፣ በሁለታችዉ መሃል የለዉን ቅርበት ና ፍቅር መግለፅ መብትህ ይመስለኛል፣ ከማንም ሰዉ ጋር ብሆን።
አንድን የአገር መሪን እገልዬ ብሎ መጥራት ግን መስመሩን የሳተ ነዉ። ፕሮቶኮል የምባል ነገር አለ። ፕሮቶኮል የምወጠዉ ለግለሰብ ሳይሆን፣ ለተቋም ነዉ። የአገር መሪነት የተቋም ተቀማጭ ነዉ። በአገሪቷ የመጨረሻዉ የስልጣን እርከን ነዉ። እዛ ቦታ ላይ ቁጭ የለን ሰዉ ተንስተህ አንተ አትልም፣ በኢትዮጵያኖች ወግ መሰረት የክብር ስም አለዉ፣ እርሶ እንላለን፣ የተከበሩ እንላለን፣ ክቡርነቶሆ እንላለን። በመሰሉት የክብር ስም እንጠረዋለን።
የእንድ አገር ፓርላማ ዉስጥ የተቀመጡ ሰዎች የሕዝብ ተወካዮች ናቸዉ፣ ግለሰብነትን ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ተወካይነታቸዉን ተሸክሞ የምሄዱ ሰዎች ናቸዉ፣ ተንስተን አንተ ወይም አንቺ እንላቸዉም፣ ክቡር የምክር ቤት አባል እንላቸዋለን፣ ለሕዝቡ ያለንን ክብር ለመግለፅ ማለት ነዉ።
የእንድን ጠ/ሚንስተርንም ስም በዚሁ አግባብ ነዉ ተንስተን አንተ ወይም አንቺ የማንለዉ፣ በሕዝብ መገናኛ ላይ ወጥተን። በግል ቤቱ ሄደህ አንተ ወይም አንቺ ልትለዉ/ላት ትችላለህ።
መንገዱን የሳትክ ትመስለኛለህ።
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 14887
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 11 May 2024, 17:18
DDT,
አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ ያለቺው አህያ ሆነ እንደ የስዩም ተሾመ ጉዳይ። አወፍራችሁ ቀልባችሁ አድልባችሁ ልትበሉት ነው ማለት ነው። በኦሮሙማ ግምባሩን ላይ የተሳመ መጨረሻ መበላቱ አይቀርም።
-
Naga Tuma
- Member+
- Posts: 6880
- Joined: 24 Apr 2007, 00:27
Post
by Naga Tuma » 12 May 2024, 14:18
DefendTheTruth wrote: ↑11 May 2024, 15:31
ፕሮቶኮል የምባል ነገር አለ። ፕሮቶኮል የምወጠዉ ለግለሰብ ሳይሆን፣ ለተቋም ነዉ። የአገር መሪነት የተቋም ተቀማጭ ነዉ። በአገሪቷ የመጨረሻዉ የስልጣን እርከን ነዉ።
ትክክል። ሰሪ። ስርነ። ስነስርዓት ነዉ።
ይህም ጽንሰ ሀሳብ ነዉ ይህን ጥያቄ ያስጠየቀኝ፥
በኢትዮጵያ ታሪክ ቀጣይ መሪ ቀዳሚ መሪን ኣለማክበር የተጀመረዉ መቼ ነዉ?
እስቲ ስለፕሮቶኮል ከተወራ በምን ፕሮቶኮል ነበር የቀድሞዉ ጠቅላይ ምንስትር መለስ ዜናዊ ቀብረን ወጥተናል ብሎ የነበረዉ?
የእንድ አገር ፓርላማ ዉስጥ የተቀመጡ ሰዎች የሕዝብ ተወካዮች ናቸዉ፣ ግለሰብነትን ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ተወካይነታቸዉን ተሸክሞ የምሄዱ ሰዎች ናቸዉ፣ ተንስተን አንተ ወይም አንቺ እንላቸዉም፣ ክቡር የምክር ቤት አባል እንላቸዋለን፣ ለሕዝቡ ያለንን ክብር ለመግለፅ ማለት ነዉ።
ትክክል። ሰሪ። ስርነ። ስነስርዓት ነዉ። የወከሉት ሕዝብ መወከላቸዉ ተገቢ ነዉ ካለ።
ለመሆኑ ፕሮቶኮል ለሕዝቡ ግራ የምያጋባ ሌላ መጤ ጽንሰ ሀሳብ እንዳይሆን ሕዝብ የምያዉቅ ቃል ወይም ቃላት የሉም?