በመጀመርያው ማለትም ከ0፡00 - 2፡18 ደቂቃ ባለው የአብይ አህመድ የወለጋ መርዛም ንግግር ትርጉም እንዲህ ይላል፡-
"የኦሮሞ ህዝብ ለ100 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ያሳለፈውን ጭቆናና መከራ ራሱ ያውቀዋል፡፡ እሱን ለእናንተ ለመንገር ወደዚህ አልመጣሁም፣ አልነግራችሁም፡፡ ነገር ግን ለእናንተ ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው፡፡ ነገር ግን ከአጠገቤ ላሉት እንግዶች /በዋነኝነት ለተመስገን ጥሩነህ እና ለአገኘሁ ተሻገር ማለቱ ነው፡፡ / እንዲገባቸው ደጋግሜ እንግራቸዋለሁ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በገዛ አገሩ በማንነቱ፣ ተሸማቆ፣ በቋንቋው እንዳይናገር ተክልክሎ በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንዲኖር ተፍርዶበት ቆይቷል፡፡ እሱም አልበቃ ብሎ ለስደት፣ ለመከራ እና ለሰቆቃ ተዳርጎ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ኦርሞ ነጻ ወጧል፡፡ አትጠራጠሩ ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ተመልሷል፡፡ ከአሁን በኋላ ያለው የልማት ጥያቄ ነው፡፡ ዘመኑ ደግሞ የሰላም እና የዲሞክራሲ ስለሆነ የልማት ጥያቄያችሁን ለመመልስ መንግስታችን እየሰራ ነው፡፡"
ከላይ ያለው የአብይ አህመድ የወለጋ ንግግር ሲጠቃለል "ኦሮሞ ሆይ አማራ ዳግም ሊገዛህ እየመጣብህ ስለሆነ ታጠቅና ተነስ" የሚል ነው፡፡
ሁለተኛውና ከ2፡20 - 3፡55 ደቂቃ ያለው የአብይ አህመድ የወለጋ መርዛም ንግግር ትርጉ የሚከተለው፡፡
"ወገኖቼ በጠላት አጀንዳ አትታለሉ፣ ልምከራችሁ፡፡ ከጠላታችሁ ጋር እያወራችሁ፣ እየመከራችሁ ሳለ እኛ ኦሮሞዎች እርስ በርሳችን ግን አንደማመጥም፡፡ ይህ የእርስ በርስ አለመደማመጥ የኦሮሞ ህዝብ የረጅም ግዜ ችግር ነው፡፡ በታሪክም ቢሆን አሳልፎ ለጠላት የሰጠን ይህ አለመደማመጥ እና አንድነት ሳይኖረን ቀርቶ ነው፡፡ ስንጠላለፍ ከርመን፡፡ ከጠላት ጋር ውይይት ማድረግ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ ስህተት ተምረን በአንድነት እንቁምና ጠላቶቻችን እንመክት፡፡"
በዚህ የአብይ አህመድ ንግግር ጠላት ተብሎ የተፈረጀውና በተደጋጋሚ ጠላት እየተባለ የተነገረው የአማራ ህዝብ ነው!!
Please wait, video is loading...