<> ጌቶቻቸው በሰሩላቸው ከተማ ማጌጡ ባልከፋ፣ ግን ሌላ አፍሪካውያኖች በራሳቸው ጉልበትና ዕውቀት የሰሯቸውን ከተሞች መናቅ፣ የባርነትን ቀምበር በፈቃደኝነት አንገት ላይ ማጥለቅ ማለት ነው። ያ ሳያንሳቸው ቀላዋጮቹ፣ በፍጥነት ኳላ ላምፖርና ሲንጋፖርን እንሆናለን ብለው “ምስኪኗንና ኋላ ቀሯን” ኢትዮጵያችንን አንጓጠጧት። የረሱት ነገር ግን፣ በራሳቸው አንድም የሰሩት ነገር አለመኖሩ ነው። ዛሬ ታዲያ፣ ሲጋፖርን በበረሃ ተንፏቀው ብቻ ነው የሚደርሱባት፣ ኢትዮጵያንም ጦሙን እንዳደረ ቡችላ በ ER መስኮት ቁልጭ ቁልጭ እያሉ ብቻ ነው የሚያዩዋት። ቀላዋጭ!













