Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40405
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አንድ የፖለቲካ ስርዓት የጸና ነው ወይስ አይደለም ለማለት መኖር ያለባቸው ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

Post by Horus » 29 Mar 2024, 22:32

13 ነባራዊ (ኦብጀክቲቭ) መለኪያዎች እነሆ፤
1
ስርዓቱ ፕሉራሊስት ወይም ብዝሃዊ መሆን አለበት። የጥቅሞችን ልዩነት የሚገነዘብ የልዩነት አንድነት አንድነት መሆን አለበት፤ ማለትም ልዩነቶች ያቀፈ አንድነት ሳይሆን አንድ የሆኑ ልዩነቶች ሲሆን ነው። አንድነት በሚመስል ስርዓት ውስጥ ልዩነቶች ማራመድ ሳይሆን ልዩነቶችን እንዳሉ አውቆ በአንድነት ስርዓት ውስት መደራጀት ማለት ነው።
2
የስርዓቱ መሰረት ግለሰቦች መሆን አለባቸው። ማለትም ከቡድኖች በተለይም ከጎሳ ቡድኖች ይልቅ ግለሰቦች ሉአላዊና፣ የበላይና ወሳኝ መሆን አለባቸው።
3
የተወሰኑ ሕዝቡን የሚወክሉ ተቋማት ካሉ ያልተወከሉትን ለመጨመር ፈቃደኛና ክፍት መሆን አለባቸው። መስፋት የሚችሉ ሆነው በየግዜው ያልተወከለው ክፍል እየተነሳ አዲስ ነጻ ተቋም የማይፈጥርበትና ያሉትን የማያርስበት ስርዓት መሆን አለበት ።
4
የህብረተሰቡ ኤልቶች ልሂቃን ወይም የገዥ ክፍሎች ሌላውን የሚያካፍሉ መሆን አለባቸው። የአንድ ኃይማኖት፣ የአንድ ጎሳ፣ የአንድ ልማድ ወገኖች ብቻ መሆን የለባቸውም።
5
በቁጥር 2 ከተጠቀሰው ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ውስጥ ሰፊ ወይም በቂ መሃል ሰፋሪ መደብ (ሚድል ክላስ) ወይም የከበርቴ ክፍል የሆነ የሲቪል ኃይል መኖር አለበት ።
6
ያለው የመንግስት ጸባይ ወይም ባህርይ ወይም አይነት ሴኩላር ኢኃይማኖታዊ ማለትም ዘመናዊ የሲቪል መንግስት በኃይማኖት ላይ ያልተመሰረተ መሆን አለበት ።
7
ስርዓቱ (መንግስቱ) የተወሰኑ የጥቅም ግጭቶችን እንደ ጤነኛ ነገር ተቀብሎ ለማስተናገድ ተቋማትን ማዘጋጀት አለበት፤ እነዚህ ተቋማት በሃብታምና ድሆች መሃል ፣ በባህሎች መሃል፣ በቋንቋዎች መሃል የሚነሱ የጥቅም ግጭቶችን የሚያካትት መሆን አለበጥ
8
በስርዓቱ ውስጥ ያለው የኃብት ልዩነት ሰማይና ምድር መሆን የለበትም። በጣም ሃብታም ጥቂቶች እና በጣም ድሃ ብዙዎች የተከፋፈለ ስርዓት አይረጋም፤ ለምሳሌ ስራ አጥነት 40% የደረሰበት መንግስት ። የኃብት ልዩነት በሰፋበት ስርዓት የፖለቲካ እኩልነት ሊኖር አይችልም።
9
የኢኮኖሚ እድገት ወይም ብልጽግና በረጅሙም ቢሆን መኖር አለበት ።
10
ሕብረተሰብ እራሱን ከወረራ የሚጠብቅበት ሰራዊትና ዲፕሎማሲ እንዲኖረው ያስፈልጋል ፤ነገር ግን የጦር ሰራዊቱን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና ከመፈንቅለ መንግስት መቆጣጠር የሚችል መንግስት መሆን አለበት ።
11
በስርዓቱ ውስጥ በግላዊ ሕይወትም ሆነ ማሕበራዊ ሕይወይ የሲቪል ነጻነቶች መኖር አለባቸው።
12
በስርዓቱ ውስጥ የፖለቲክስ ውይይትና ሙግት ባህል ማለትም በአማራጭ ፖሊሲዎች ማሻሻያዎች ላይ የመፋጨት ባህል መኖር አለበት ።
13
የገዥው ክፍል መሪዎች የፖለቲካ ፈቃድ ወይም መሻት ማለትም በዴሞክራሲና ፍትህ የሚያምኑ መሆን አለባቸው ።

እነዚህ 13 ሁኔታዎ ወይም አብዛኛዎቹን የሚያካትት መንግስት ብቻ ነው የተረጋጋ ወይም እስቴብል አስተዳደር የሚባለው ። በዚህ መለኪያ መሰረት የአቢይ አህመድ ኦሮሞች መንግስት አንዱንም እንኳ ሙሉ በሙል አያሟላም ። ለምሳሌ ቁጥር 10ን ብንመለከት የተወሰነ መከላከያ ቢኖረውም ዲፕሎማሲ የለውም ።

በነዚህ 13 መለኪያ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ ያልተረጋጋ አነስቴብል መንግስት ነው።

ሆረስ ዐይነ ብርሃን
May 19, 1995