<> በደጉ ዘመን ሁለት የኤርትራ ምግብ ቤቶችን አዘወትር ነበር፥ አንዱ በቅርቡ የፈረሰው ሎምባርዲያ ህንፃ ውስጥ ሲሆን ሌላው ፒያሳ ከባንኮ ዲራማ ጀርባ ነበር። አሮስቶ፣ ከተሌት፣ ፓስታና ሰላጣቸውን ነበር በጣም የምወድላቸው። ከቪንቴጅ ማሽን vintage machine ውስጥ የሚወጣው ካፑችኗቸውም ወደር የለውም ነበር። አንድ የአበሻ ምግብ የሚሰራም አጠር ጠቆር ያለ ኤርትራዊ እዚያው ፒያሳ ነበር፣ ግን ምግቡ ስላልተስማማኝ ከአንዴ ወይንም ከሁለቴ በላይ አልሄድኩም።
<> በኋላ ከአዋቂዎች ስሰማ፣ ወጥና ኤርትራ አብረው አይሄዱም ተባልኩ፣ ከዚያ ወዲህ የአበሻ ምግብ ኤርትራ ምግብ ቤት ውስጥ በልቼ አላውቅም። በኋላም ኢሳያስ አፈወርቂ መጣና፣ እንጀራ የኋላ ቀሮቹ ኢትዮጵያውያኖች ምግብ ነው፣ ከዚህ በኋላ ስፓጌቲ ብሉ ብሎ የሰማሁትን ሃሜታ አረጋገጠልኝ። ታዲያ እንጀራ ባህላቸው ካልሆነ፣ ስፓጌቲ የጣሊያን ከሆነ፣ ፉል (Ful) የግብፅ ከሆነና ህልበት (Asida) የየመን ከሆነ፣ ምንድነው የራሳቸው የሆነው ምግብ? ለምንስ ዞረው ዞረው ወደ ጠሉት እንጀራው ተመልሰው መጡ? ኢትዮጵያን ጠልተዋት ትተዋት ሄደው፣ አሁን ተመልሰው እስር እስሯ እንደሚልከሰከሱትና ER ላይ እንደሚቀላውጡት ማለት ነው?














