Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Misraq
Senior Member
Posts: 16750
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Misraq » 23 Feb 2024, 12:30

ሆሩስ የታሪክ አዋቂ ነኝ ብሎ እንዴት ይህንን የመሰለ ግድፈት ይፈጽማል

1) ቱርክ በ11ኛውና 12ኛው ክፍለ ዘመን ገንና አልወጣችም፥፥
ኦቶማን ቱርክ ወሳኝ የሆነውን ከባይዛንታይን ኤምፓየር የተረከበችው May 29, 1453 naw

፪) ላሊበላ ዳግማዊት ኢየሩሳሌምን ለመገንባት የተገደደው Western በክሩሴደሮችና በሳላህአዲን (Kurdistan ሃይሎች) መካከለኛው ምስራቅ በወደቀ ግዜ ነው፥፥ የምእራባውያን መንግስታት ኦሮቶዶክሳውያንንም ይዘርፉና ያሰቃዩ ስለነበር የኢትዮጵያ ነገስታት ኢየሩሳሌምን ነጻ የማወጣት ጥሪ ስላልተቀበሉ ሳላህ-አዲን ዴር ሱልጣንን ለኢትዮጵያውያን ሰጥቶ እስከ ቅርብ ግዜ የኛ ነበር፥፥ ቱርክ እዛ የደረሰው ከ400 መቶ አመት በህዋላ ነው

Horus wrote:
22 Feb 2024, 02:15
የዛሬ 1000 አመት የኦቶማን ኢምፓየር ኢየሩሳሌን ተቆጣጥሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማትን ሁሉ ሲወስድ ታላቋ ኢትዮጵያ አዲሲቱን ኢየሩሳሌም በላሊበላ ትገነባ ነበር !!! ቱርኮች ኢትዮጵያ ምን እንደ ሆነች ያውቃሉ ! የዛሬ 600 አመት የአዳሉ መሃምድ ግራኝን እየረዱ የክርስትና መጽሃፍ ሲያቃጥሉ የገዳማቱን ወርቅ ሲዘርፉ ኢትዮጵያ ምን እንደ ሆነች ያውቃሉ !! ኢትዮጵያ ሺ ግዜ ብትቀጥን ሁሌም ጠጅ ነች ። የዘመናችን ቱርኮች ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ !ይህን የማያውቅ የሕዝቦቹ ማፈሪያ የሆነው መንገድ የጠፋው ሹክሻክ ጸረ ኢትዮጵያ ቆርቆሮ ለቃሚ ብቻ ነው!

Last edited by Misraq on 23 Feb 2024, 15:20, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 40425
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Horus » 23 Feb 2024, 14:44

ምስራቅ
እኔ አሁን ብዙ አስፈላጊ ነገሮች ላይ ስለ ተጠመድኩኝ ይህን ይጎዮሽ ውስጥ አልገባም ። የኦፊሴሉ የኦቶማ ኢምፓየር 1299 እስከ 1922 ነው ። ከ1299 ለብዙ ዘመን ያኢሳል ካሊፊቶች በመስፋፋት ለ1299 የቱርክ መነሳት መስረት ሆነዋል ። ዝርዝር ነገር ለምን ዛጉዊዎች አዲስ ኢየሩሳሌም ፈለጉ የሚል የምትነግረን ካለ ነገረን ። የእኔ ዋና ነጥብ ቱርክ ግራኝን ደግፋ ከኢትዮጵያ ጋር የፕሮክሲ ጦርነት አድርጋለች በ1525። ይህ የመጨረሻ ሃሳቤ ስለሆነ መልስህን አልጠብቅም።
https://en.wikipedia.org/wiki/Ottoman_Empire

Misraq
Senior Member
Posts: 16750
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Misraq » 23 Feb 2024, 15:16

ወንድማችን ሆረስ

ኦቶማን ቱርክ ኢየሩሳሌምን የያዘው በ 1516 ነው፥፥ በዚህ ግዜ የዛገዌ ዳይናስቲ አልነበረም፥፥ የዛግ ዌ ዳይናስቲ ያበቃለት በ1270 ነው:: አንተ የዛሬ 1000 ሺህ አመት ስትል ኢየሩሳሌም በቱርክ የወደቀቸው በ 1024 ነው እያልከን ነው:: so your margin of error is 500 years. Will you stand corrected? or will you abscond as you said on your last reply.

Horus
Senior Member+
Posts: 40425
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Horus » 23 Feb 2024, 15:47

My final last time !!!!!!!

ኢየሩሳሌም መቼ ነው በስላሞች መያዝ የጀመረችው?

"638
The Islamic history of Jerusalem begins with the conquest of the city by Caliph Umar in 635 (or 638). Umar had been one of the prophet Muhammad's closest companions and served as his second successor (khalifa) after Abu Bakr."

በቃ ኦቶማን ይህ የእስላም ክሊፌቶች መስፋፋት ነው የተረከበት ! እንደ ደብተራ ፔዳንቲክ አትሁን ፣በቅ ይህን ታሪክ ከሌሎች ተከራከር ! የኔ ነጥብ ቱርክና የግራኝ ወረራ እንጂ የኢስላሚክ መስፋፋት ታሪክ አይደልም ። ወእ ሌላ አርስት ሂድ

Naga Tuma
Member+
Posts: 6888
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Naga Tuma » 23 Feb 2024, 16:00

ምስራቅ፥

እናስተምረዉ ያልከዉን ኣይቼ ርዕሱ ስቦኝ ከፈትኩኝ።

ነጥብህን ኣንብቤ ገረምከኝ፣ እንደገና።

እስቲ ሆረስ ኣንተ እንዳልከዉ ተሳሳተ እንበል።

ስህተት ነዉ ያልከዉ የታሪክ ዕዉቀቱን የምታዉቀዉን የኢትዮጵያ ምሁር የታሪክ ABCD ልናስተምረዉ ያስፈልጋል የምያስብል ስህተት ነዉ?

እኔ ስለታሪክ ከሆረስ የተለየ ግንዛቤ ያለኝ በኣንድ ቀላል ነገር ግን ቁልፍ የሆነ ታሪክ ላይ ነዉ።

ብሉይ ኪዳን ዉስጥ ስለተጻፈ የጥንት አስተያየት ነዉ። ለእኔ ተቀባይነት ዬለዉም። ለእሱ ተቀባይነት እንዳለዉ እስከዛሬ ኣላዉቅም። መልሼ መላልሼ ብጠይቀዉ እስከዛሬ ኣልመለሰም።

ከዓመታት በፊት ነዉ ስለ ስለጥንቱ አስተያየት ኣንብቤ ሙሴን ዘ ሞስት ወንትድ ማን ኢን ኣፍርካ ያልኩኝ።

ከዛ በኋላ ነዉ የስግመንድ ፍሪዩድን ስለሙሴ ፎረንሲክ ታሪክ ያነበብኩኝ።

ስለምን እንደጻፍኩ ገባህ ወይስ ስለዚህ ሀ ብለህ መማር የምያስፈልግህ ነህ?

ኣለማስተዋልን ሰዉ ስንት ግዜ መበጣጠስ ኣለበት?
Misraq wrote:
23 Feb 2024, 12:30
ሆሩስ የታሪክ አዋቂ ነኝ ብሎ እንዴት ይህንን የመሰለ ግድፈት ይፈጽማል

1) ቱርክ በ11ኛውና 12ኛው ክፍለ ዘመን ገንና አልወጣችም፥፥
ኦቶማን ቱርክ ወሳኝ የሆነውን ከባይዛንታይን ኤምፓየር የተረከበችው May 29, 1453 naw

፪) ላሊበላ ዳግማዊት ኢየሩሳሌምን ለመገንባት የተገደደው Western በክሩሴደሮችና በሳላህአዲን (Kurdistan ሃይሎች) መካከለኛው ምስራቅ በወደቀ ግዜ ነው፥፥ የምእራባውያን መንግስታት ኦሮቶዶክሳውያንንም ይዘርፉና ያሰቃዩ ስለነበር የኢትዮጵያ ነገስታት ኢየሩሳሌምን ነጻ የማወጣት ጥሪ ስላልተቀበሉ ሳላህ-አዲን ዴር ሱልጣንን ለኢትዮጵያውያን ሰጥቶ እስከ ቅርብ ግዜ የኛ ነበር፥፥ ቱርክ እዛ የደረሰው ከ400 መቶ አመት በህዋላ ነው

Horus wrote:
22 Feb 2024, 02:15
የዛሬ 1000 አመት የኦቶማን ኢምፓየር ኢየሩሳሌን ተቆጣጥሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማትን ሁሉ ሲወስድ ታላቋ ኢትዮጵያ አዲሲቱን ኢየሩሳሌም በላሊበላ ትገነባ ነበር !!! ቱርኮች ኢትዮጵያ ምን እንደ ሆነች ያውቃሉ ! የዛሬ 600 አመት የአዳሉ መሃምድ ግራኝን እየረዱ የክርስትና መጽሃፍ ሲያቃጥሉ የገዳማቱን ወርቅ ሲዘርፉ ኢትዮጵያ ምን እንደ ሆነች ያውቃሉ !! ኢትዮጵያ ሺ ግዜ ብትቀጥን ሁሌም ጠጅ ነች ። የዘመናችን ቱርኮች ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ !ይህን የማያውቅ የሕዝቦቹ ማፈሪያ የሆነው መንገድ የጠፋው ሹክሻክ ጸረ ኢትዮጵያ ቆርቆሮ ለቃሚ ብቻ ነው!

Misraq
Senior Member
Posts: 16750
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ወንድማችን ሆረስን የታሪክ ABCD ልናስተምረው ያስፈልጋል

Post by Misraq » 23 Feb 2024, 16:09

Naga Tuma,

ወደ የት እንደምትወስደኝ አውቃለሁ እሱም ሙሴ.... ሞሰስ.... ሙሳ..... ከዛም.... ሞሲሳ ብለህ ሙሴን ኬኛ ልትለው እንደሆነ ግልጽ ነው

ወንድማችን ሆረስ,

ቱርክ islamic ብትሆንም አረብዊት ግን አይደለችም፥፥ State እና Religion መለየት እንዳቃተህ ያሳያል፥፥ በሰባተኛው ክፍለዘመን የነበሩት የአረብ ካሊፋቶችና ቱርኮች እንድ ናቸው ማለት የሮማን ኤምፓየርና አሜሪካ አንድ ናቸው ማለት ነው፥፥ አይዞህ መማማር ያለ ነው ስለዚህ ስናስተምርህ እሺ በል

Post Reply