Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የግርዝና ሴራ (ስርዓተ ጉራጌ) ምንድን ነው?

Post by Horus » 11 Feb 2024, 02:30

ግርዝና የሚባለው የጉራጌ ስርዓት ዋና ቃሉ ጉርዝ ነው ። የጉራጌ ሕዝብ ሁሉ ለዘመናት የሚመሩበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሴራ (ሴራ ስርዓት ማለት ሲሆን የግዕዝ ቃል ነው) በሁለት ስሞች ይጠራል ፤ የግርዝና ወይም የባሊቅ ስኛት ይባላል። ስኛት ስርዓት ወይም ሲስተም ማለት ነው ። ይህ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ ሕጋዊ ካልቸር ብቸኛው የጉራጌ ብሄር የመሪነት ካልቸር ነው።

ማንኛውም የጉራጌ ጉዳይ ከአንድ ግለሰብ ስህተትና ወንጀል፣ እስከ ባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ፤ ከሁለት ሰዎች ጠብ እስከ ብሄር አቀፍ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ አስተዳደርና የፍርድ አፈጻጸም፣ በአንድ ቃል መንግስታዊ ተግባሮች ሁሉ የሚመሩት በግርዝና (በጉርዝና) እና በባሊቅ ሴራ (ስኛት) ነው።

ጉርዝ ምን ማለት ነው? ባሊቅ ምን ማለት ነው

ጉርዝ በተለይ የክስታኔኛ ቃል ሲሆን መሰረቱ ጥንታዊ ግብጽ ሆኖ ዛሬ በሰፊው የሚታወቀው በሂንዱ ካልቸር ነው ። በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ በሳንስክሪት ጉሩ ማለት አዋቂ፣ አስተማሪ ፣ ቄስ ማለት ነው። በጥንታዊ ግብጽ የጸሃዩ ራ አምልኮ ዘመን የነበሩት የእምነቱ ቄሶች ጉሩ ይባሉ ነበር። ትርጉሙ በሶስቱም ካልቸሮች አንድ ነው ፤ አዋቂ፣ አስተማሪ፣ መሪ፣ የተከበረ ፣ ክቡድ ሰው ማለት ነው።

በጉራጌ የጉርዝ (የግርዝና) ባህል ይህ ስልጣንና ክብር የሚሰጠው እድሜ ጠገብ ሽማግሌ ቢያንስ 60 አመት በላይ የሆነው ዋይዝ አባት ብቻ ነው።

በመላ ጉራጌ ብሄር ውስጥ ያለው ሊላው የጉርዝ ቃል ባሊቅ ይባላል። ባሊቅ እጅግ ጥንታዊ የሴም ቃል ሲሆን በአረሜይክ (ክርስቶስ የተናገረው ቋንቋ) ሞሎክ ይባላል። ትርጉሙም ንጉስ ፣ ጌታ ማለት ነው። በአሲሪያና ዘመናዊ አረሜክ ማሊክ ይባላል። ትርጉሙ ያው ንጉስ፣ ጌታ ማለት ነው ። በአረብኛም በእንብራስጥም ቃሉ ያው ነው ።

ዛሬ ሊቅ ፣ የላቀ፣ ታላቅ፣ ልሂቅ የምንላቸው ቃላቶች ሁሉ ማሊክ፣ ማለቅ፣ ባሊቅ የሚባሉት የጥንት ጽንሶች ናቸው።

ጉርዝ፣ ባሊቅ በአማራኛ ሽማግሌ ማለት ነው።

በጥንታዊ ግሪክና ሮማዊያን ዘመንም አንድ ሰው የአገር መሪ ፣ የሕዝብ መሪ ለመሆን እድሜው ከ60 አመት በላይ መሆን ይጠበቅበት ነበር። የ ጎርቲ ሲስተም ይባል በነበረው የግሪኮች ትራይባል አስተዳደር ተመሳይ የሴኔኬ ስርዓት ነበር ። ዛሬ ሴኔተር (ሴኔቻ) የምንለው ቃል ሲኒየር ወይም ሽማግሌ፣ ባሊቅ፣ ኤልደር ማለት ነው።

የጉራጌ ባሊቅ ወይም ጉርዝና ሴራ ይህን ከመሰለ ጥንታዊ ግንድ የበቀለ ሲሆን በጉራጌ ብሄር ከሽማግሎች ቀድሞ ወጣት አይመራም ። የሽማግሎች ብያኔ፣ ውሳኔ ማኛውም የወጣቶች ቡድን ሊጥስ፣ ሊሽር አይችልም ። በነዚህ ሴናተሮች ጉባኤዎች (ምሳሌ የጆካ እና ጎርደና) የሚወሰኑ ሴራዎች ፣ ስኛቶችና ቅጫዎች የብሄሩ ሕገ መንግስት፣ የወንጀልና ፍትሃ ብሄር ሕግጋትና ቅጣቶች ናቸው ። ቅጫ ማለት ቅጣት ማለት ነው ። ሴራ ሌላ ትርጉሙ ሕግ ማለት ሲሆን ስኛት ሁሉም አይነት የስነ ምግባር መርሆዎችን ያጠቃልላል ።

የዚህ ሁሉ መሪና ያገር አባቶች የጉራጌ ባሊቅ፣ የጉራጌ ጉርዝ፣ የጉራጌ ሽማግሎች ናቸው ። በጉራጌ ብሄር ሽማግሌ ይመራል ያዝዛል፤ ወጣት ይከተላል፣ ይታዘዛል ። ዊዝደም የሚባለው የባሊቆች ብቃት ወዠት፣ በወዠት ይባላል፤ እሱም ማየት ማስተዋል ማለት ነው ። ሕዝብና አገር መሪ ያገር አባት ለወዠት፣ ለዊዝደም የደረሰ ጉርዝ ባሊቅ ብቻ ነው ።
Last edited by Horus on 13 Feb 2024, 14:45, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

Post by Horus » 12 Feb 2024, 00:03

የሰባት ቤት ጉራጌ የጆካ ቅጫ ሴራ

Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

Post by Horus » 12 Feb 2024, 00:15

የክስታኔ ጉራጌ ጎርደና ሴራ

ተመሳሳይ ስርዓቶች በመስቃን ጉራጌ፣ በወለኔ ጉታዘር ፣ በዶቢ፣ ሌላው ቀርቶ በስልቴም አለ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

Post by Horus » 12 Feb 2024, 16:12


Naga Tuma
Member+
Posts: 7311
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

Post by Naga Tuma » 13 Feb 2024, 02:59

Horus wrote:
11 Feb 2024, 02:30
ዛሬ ሴኔተር (ሴኔቻ) የምንለው ቃል ሲኒየር ወይም ሽማግሌ፣ ባሊቅ፣ ኤልደር ማለት ነው።
ሴኔት ሴኔቻ መሆኑን ኣላዉቅም ነበር። ሸነቸ የሚል ቃልን ባዉቅም። ኮረ እና ኮንግረስ የሚባሉ ቃላትን ኣዉቄ የነበረ ቢሆንም።

ቃላትን ማወቅ ደግ ነዉ።

ሸን ማለት አምስት ማለት ነዉ። ካልተሳሳትኩ ሸነቸ ማለት የአምስት ሰዎች ኮሚቴ ወይም ኮሚቲ ማለት ነዉ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የግርዝና ሴራ ምንድን ነው?

Post by Horus » 13 Feb 2024, 14:38

Naga Tuma wrote:
13 Feb 2024, 02:59
Horus wrote:
11 Feb 2024, 02:30
ዛሬ ሴኔተር (ሴኔቻ) የምንለው ቃል ሲኒየር ወይም ሽማግሌ፣ ባሊቅ፣ ኤልደር ማለት ነው።
ሴኔት ሴኔቻ መሆኑን ኣላዉቅም ነበር። ሸነቸ የሚል ቃልን ባዉቅም። ኮረ እና ኮንግረስ የሚባሉ ቃላትን ኣዉቄ የነበረ ቢሆንም።

ቃላትን ማወቅ ደግ ነዉ።

ሸን ማለት አምስት ማለት ነዉ። ካልተሳሳትኩ ሸነቸ ማለት የአምስት ሰዎች ኮሚቴ ወይም ኮሚቲ ማለት ነዉ።
ቃላት ማወቅ ጥሩ ነገር ብቻ ሳይሆን የአንድ ሕዝብ ካልቸር ጂን ምን እንደ ሆነ ማወቅ ማለት ነው ። የሰው ዝርያ ምንነት በጂኑ ይታወቃል፤ የካልቸር ዝርያ ምንነት በቃሉ ነው የሚታወቀው ።

እኔ ኦሮሞኛ ስለማላውቅ ሸኒ (5) ከምን ስረ ቃል እንደ መጣ አላውቅም ።

ከላይ እንዳልኩት ሴኔኬ ፣ ሴኔት የጥንታዊ ግሪክና ሮም ሕግ ና አስተዳደር ስርዓት ነበር ። ሰዎቹም የሽማግሎች Council of Elders (Senators) ነበሩ ። ሴኔት ሽማግሌ ማለት ነው።

በጉራጌ የሕግና አስተዳደር ሴራ የሰነቻዎች ሸንጎ አምስት ከሚል ትርጉም ወይም ቁጥር ጋር ፍጹም አይገናኝም ። ስነቻ ስኛት ማለት ነው ። ስኛት ስርዓት የሚለው የአማርኛ ቃል ነው። ስኛት ስርዓት ማለት እንጂ ሸኒ ወይም የ5 ሰዎች ስብሰባ ማለት አይደለ።

የሰነቸዎች ስብሰባ ሸንጎ ይባላል ። ለተለያየ ጉዳይ የተለያዩ ጉርዳዎች፣ ጎርደናዎች (ጉባኤዎች ) አሉን ። ለምሳሌ ሌላው ስውኘት (ሳቡኘት) ይባላል ። ይህም ያው ስኛት የሚለው ቃል ነው ። ኬርታ ፣ ጉርዳ፣ ጎርደና። ሲምቢታ ወዘተ እያለ እንደ ጉዳዩ ክብደትና አይነት ዳኞቹም ፣ ሽማግልቹም ይለያያሉ ። ጉርዳ ቃል ኪዳን ፣ ግዝት ወይም ከፍተኛ ውሳኔ ማለት ነው ። በሰባት ቤት ጉርዳ ይባላል፤ በክስታኔ ጉርደኛ (ጎርደና) ይባላል።

ስለዚህ ጉራጌ ኬር (ኬይር) የሚለው ፍልስፍና እዝጌር (እግዚአብሄር) የሚለው ሲሆን ሕግ፣ ሰላም፣ ሴራ፣ ስርዓት ማለት ነው። በሙስሊም ፍልስፍና ሸሪአ የሚባለው ነው ። ስለዚህ በእውነተኛ የጉራጌ ስርዓተ ማህበርና አስተዳደር የባሊቆች ውሳኔና ዳኝነት ልክ እንደ መንፈሳዊ ሕግ የሚከበር ነው ። ጉራጌ ቁም በጎርደና አምላክ ካለ አንድ ሰው ይቆማል ።

አንድ ሰው ቢያንስ 60 አመት ሳይሞላው ያገር አባት የሕዝብ መሪ ሊሆን አይችልም፣ አይገባም! በጎረምሳ የሚመራ ሕዝብ የወረራ፣ የጦርነት፣ የአመጽና የሁከት ካልቸር ነው!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42516
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የግርዝና ሴራ (ስርዓተ ጉራጌ) ምንድን ነው?

Post by Horus » 14 Feb 2024, 02:51

በጉራጌ ሽማግሌ ይመራል፣ ወጣት ይከተላል!

Post Reply