Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ፣ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎችም አካባቢዎች ታስረው ይገኛሉ

Post by Za-Ilmaknun » 13 Feb 2024, 13:54

የፕሪቶሪያው ስምምነት ‘ነፃ ያላወጣቸው’ የትግራይ ተወላጆች የመከላከያ ሠራዊት አባላት

ቢቢሲ ያነጋገራቸው በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ፣ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎችም አካባቢዎች ታስረው እንደሚገኙ ይናገራሉ።እነዚህ የትግራይ ተወላጆች ከአምስት ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው እና በከባድ ወንጀል ከተፈረደባቸው ሲቪሎች ጋር ተደባልቀው በተለያዩ እስር ቤቶች እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ይናገራሉ። በአገሪቱ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ እነዚህ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በበኩላቸው “አገር እያገለገልን ተከዳን” በማለት እንደሚያዝኑ ጨምረው ያስረዳሉ። የፌደራል መንግሥት ከ 5,000 የማያንሱ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት እና የፀጥታ አባላት የትግራይ ተወላጆች በመላ አገሪቱ ታስረው እንደሚገኙ መረጃ አንዳላቸው ይገልጻሉ

https://www.bbc.com/amharic/articles/cx7l08ql7x4o