Re: Horus, tell us more about this lovely ክስታኔ tradition
Lovetarik,
የምታይው ባህል በክስታኔ ጉራጌ ጋብቻ ሂደት 3ኛው እስቴፕ ነው ። የባህሉ (የበዓሉ) ስም ቸግ ይባላል። ፍጸማ (ወይም ፍጽምጽም) ማለት ነው። ቸግ ከተደረገ በኋላ ሰርግ አይፈርስም ። በሁለተኛው እስቴፕ የሴት ወላጆች ልጃቸውን ለመስጠት ከፈቀዱ በኋላ የቸግ መፈጸሚያ ቀን ተጥሎ የሴት ወላጆች ይህን ግዙፍ ድግስ ይደግሳሉ ። ሙሽሮቹ እዚህ ውስጥ አይገኙም። ይህ የሁለቱ ቤተ ሰቦች መተሳሰሪያ ባህል ነው ።
የወንድ ወገኖች ጥሎሽ፣ ስጥታዎች ለሴት አባት፣ ለሴት እናት ፣ ለልጅቷ የሚሰጥ እንቁዎች ይዘው ሴቷ ቤት ይገኛሉ ። በቁጥር 2 የተላኩት ሽማግልችም ይገኛሉ ። የወንድ ወገኖች ጋቢ ቡሉኮ ሌላም ሌላ እንደ ሃብታምነታቸው ለሴት ወላጆች ያለብሳሉ። የሴት እናት ይህ የሚታየውን ዉፋ ቅኔ (raw [deleted]) ዋና ዋና በሚባሉት እንግዶች አናት ላይ አስቀምጣ በሻሽ ታስራለች ።
ከፍተኛው የአክብሮት ምልክትና መግለጫ ነው ። ቡሉኮ ከማልበስ በላይ ያለው አክብሮት መስጫ ማለት ነው። የድሮ ሰዎች ለብዙ ነገር ቅቤ በራሳቸው ላይ ተደርጎ በሻሽ ታስሮ እዚያ ላይ ባርሜጣ ያደርጉ ነበር ። አጼ ምኒልክ ሁሉ ያን ያደርጉ ነበር ።
ንጹህ ቅቤ በዚህ መልክ የመጣው ክርስቶስ ከሚለው እምነት ነው ። ክርስቶስ ማለት የተቀባ ፣ የተመረጠ፣ ክቡር ፣ ቅዱስ ማለት ነው! ቅብዓ ቅዱስ እንደ ምንለው ማለት ነው ። መቀባት መሾም ነው። የባህሉ ስር ያ ነው ። ደሞም በባህላችን ጋብቻ በጣም የተከበረ ነገር ነው። በዚህ በቸግ ቀን የተወሰነ ነገር በእግዚአብሄር ዳኝነት የተፈጸመ ነው ተብሎ ነው የሚወሰደው ። የሴቷ አባት ልጄ ልጃችሁ እንድትሆን ሰጣችኋለሁ ፤ ለዚህም ዳኛዬ እግዚአብሄር ነው ብሎ ነው የሚናገረው። የወንዱ እናትም ልጃችሁ የራሴ ሴት ልጅ አድርጌያታለሁ ትላለች ። በእውነትም ደሞ ምሽራ ለአማቷ እንደ ልጇ ነው የምትሆነው ። ለምሳሌ የምሽራዋ ባል ቢሞትና የምሽራዋ እድሜ በጣም ካልገፋ አንድ አመት ካዘነች በኋላ ባል ማግባት ከፈለገች አማቷ የሟቹ ባል እናት ልክ እንደ ሴት ልጇ ደግሳ ትድራታለች ።
አንድ አላዋቂ ከተሜ ግን ቅቤ መቀባትን ተጸይፎ ባህል ሲያበላሽ ይታያል !
ይህን ነው ቸግ (ፍጥምጥም) የሚመስለው ።
viewtopic.php?f=2&t=338005&p=1453980#p1453980