የቃል ትርጉም፤
ዉሳቻ = የሴቶች የእንሰት መፋቂያ ደቦ ። የእያንዳንዱ ቤት እንሰት መፋቅ በዉሳቻ (የሴቶች ደቦ) ነው የሚከወነው ። የዚያን ቀን ባለዉሳቻዋ ሴት ሙሉ ድግስ ደግሳ ሴቶች እየበሉ እየጠጡ እየተዘፈነ ነው ሲሰሩ የሚውሉት ። ልክ እንደ ማህበር ዉሳቻ ለባለተራው ይዞራል ። በጉራጌ አብዛኛ ስራ በማህበር ነው የሚሰራው ። ምሳሌ
ከብት ማገጃ የልጆች ማህበር ዎጀ ይባላል (ከብት በተራ ነው የምናግደው)
እንሰት መቆፈሪያ ማህበር ድድቅ ይባላል
እርሻ ማረሻ ያው ደቦ ነው
እንሰት መፋቂያ ዉሳቻ ይባላል
እያለ ይቀጥላል!!!