የዎያኔ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ የኦሊጋርኪ አገዛዝ እንደ ነበር ይደመድማል ። ኦሊጋርኪ ማለት የጥቂቶች አገዛዝ ማለት ነው። ኦሊጎ በግሪክ ጥቂት ማለት ሲሆን አርኪያ መግዛት፣ ማዘዝ ማለት ነው።
የአቢይ አህመድ ባለ 4 ምሰሶ ያገር ማቆሚያ ሞዴል እንደ ገና ገልጾታል
ምሰሶ 1 አልትራ እስትራክቸር፣ የእምነት፣ የሲቪል፣ የሚዲያ፣ የካልቸር ተቋማት
ምሰሶ 2 ሱፐር እስትራክቸር፣ መደመርና የብልጽግና ፓርቲ
ምሰሶ 3 ኢንትራ እስትራክቸር፣ የመንግስት መዋቅሮች፣ አውታሮች፣ ተቋሞች (እስቴት አፓራተስ ና ኢንስቲቲውሽን)
ምሰሶ 4 ኢንፍራ እስትራክቸር ፣ መንገድ፣ የሃይል ፣ የኮሚኒኬሽን ወዘተ ሲስተሞችና ዝርጋታዎች
እዚህ ላይ ትልቅ ጥያቄ መነሳት ያለበት የብልጽግና ፓርቲ ነው ። ፒፒ ፓርቲ ሌሎች ፓርቲዎች እንደ ሌሉ አድርጎ የአንድ ፓርቲ ዲክታቶርነት ያለ ማስመሰሉ ያፍ ወለምታ ወይስ ሌላ ነገር? ደሞ መደመር ፍልስፍና ሳይሆን እስትራተጂ ነው ።
ሌላው የትግሬ ምርጫን የጨረቃ ምርጫ መባሉ ግሩም ስያሜ ነው ። ዎያኔ ጥርነት ከፈለገም ና ተብሏል
የግምገማው ትልቁ ጭብት ይህ ነው፡
በኢትዮጵያ ሁለት ሙሉ በሙሉ ተጻራሪ ስዕሎች፣ እውነታዎች፣ ሁኔታዎች እንዳሉ ነው። አንዱ ይህ የአብይ ስዕል ነው። ሌላው የጎሳ አገዛዝ፣ የኦሮሞ ሄጂሞኒ፣ ያዲስ አበባ ጥያቄ፣ የኦሮሞ ጄኖሳይድ፣ የደቡብ ክልል መፍረስና ቀውስ ባንድ ቃል ልብ ላለ ሰው ሁለት አይነት ኢትዮጵያ ነው የምናየው !!! ትግሉም በዚህ ሁለት ኢትዮፕያዎች መካከል ነው።