Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7334
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቡትስ፣ ቦቴ፣ ቡቲክ፣ ቦኬ

Post by Naga Tuma » 31 Dec 2023, 14:29

ከልጅነት እስከ ወጣትነት ኢትዮጵያን ኣይቻለሁ። ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ብዙ አከባቢዎቹን።

እኔ የማስታዉሰዉ ያየሁኝ አከባቢዎች ሁሉ የሰዉ ልጆች እግሮች ቢቆጠሩ ጫማችን ካደረጉት ይልቅ ያላደረጉት እጅግ ይበዛሉ።

ኣሁን ሁሉም ኣልፎላቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁሉም እግሮች፣ በረ ባሶም ቢሆን፣ ጫማ ማድረግ ችለዉ ከሆነ ኣላዉቅም።

ወጣት ሆኜ ስንት እግሮች በእሾሆች በሚቆስሉበት እና በጭቃ በሚቆሽሹበት ሃገር ቡትስ ጫማ ተንቆ ሲዘለፍ ሰምቻለሁ። ስለ ቡትስ አሰራር ኣንድ ፎርሙላ ተማር ቢባሉ ከባድ ነዉ በሚሉ።

በከብት እርባታ ከኣፈሪካ በጣም የምትታወቅ ሃገር ዉስጥ እግሮች ክጭቃ እና እሾህ ጋር ሲታገሉ ይኖራሉ፣ ይኖሩ ነበር።

ቆዳን ፍቆ ጫማ መስራት መቻል ከባድ ነዉ? ጉራን ዉልቅ ኣድርጎ ማን ፋቂ ይባላልን መርሳት ከተቻለ።

ስለ ቡትስ ኢትዮጵያ ዉስጥ በወጣትነቴ የሰማሁትን የልጅ ፌዝ ታዝቤኣለሁ።

ያ ፌዝ እዚህ ፎረም ላይ ሲደገም ኣንብቤ የበለጠ ታዝቤኣለሁ። ሲሉ ሰምታ ይባላል ብዬ።

ያልተማረዉ ስላልተማረ ነዉ ይባላል። ተማረ የተባለ እንደዚህ አይነት ፌዝ የምናዉቃት ኢትዮጵያ ዉስጥ ምንድነዉ ብሎ መጠየቅ ካልቻለ ምን ይባላል?

በቡትስ ያፌዙት ቦቴ ማለት፣ ቡቲክ ማለት፣ ቦኬ ማለት ህልማቸዉ እንደሆነ ኣዉቃለሁ።

ቡትስ፣ ቦቴ፣ ቡቲክ፣ ቦኬ ሁላቸዉም ኢትዮጵያ ዉስጥ የተፈጠሩ ኣይመስለኝም። ሁላቸዉንም ኢትቶጵያ ዉስጥ መፍጠር የልተቻለ ኣይመስለኝም።

ሁላቸዉም የተፈጠሩበት ሃገሮች ተከብረዉ ኣድገዉ እያደጉ ያሉ ናቸዉ።

ኢትዮጵያ ቡትስ ብሎ የምያፌዝ ኣሜሪካ ቋ ቋ የሚለዉን ቡትስ እያንቋቋች ኣንዷ ኣድርጋ ብታልፍ ፈዞ የምያይ ነዉ። እዛ ፌዝ፣ ኣሜሪካ ደርሶ ያፌዙበትን ኣይቶ መፍዘዝ።

በትክክል ካስታወስኩ ጃፓን ስለ አረት ነገሮች አፈ ታሪክ ኣላቸዉ ኣሉ። አፈር፣ አየር፣ እሳት፣ እና ዉሃ። አምስተኛዉ ስፍራም ኣለ።

ወጣት ሆኜ ሁለት ተመሳስይ ልበወለዶችን ኣስታዉሳሉ። ሁለቱም በጣም ለም አከባቢዎችን በኣእምሮ ዉስጥ ይቀርጻሉ። ተመሳሳይ የፍቅር ታሪክ ኣለባቸዉ።

ኣንዱ ለም እና ጫካ የበዛበትን መቱ አከባቢ ያስተዋዉቃል። ፍቅረኞች ከአዲስ አበባ ሄደዉ ያዩት።

ሌላኛዉ ከእንግልዘኛ የተተረጎመ በእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ድንበር አከባቢ የነበረን ለም እና ጫካ ያለበትን ያስተዋዉቃል። የፈረንሳይ ጉብል የእንግሊዝ ኮረዳን ወዶ ጫካ ዉስጥ በፈረሱ ሄዶ ጫካ ዉስጥ ኣስሮ ኮረዳዋን ሲጎበኝ። ኣሁን ደሴቷን እያስታወስኩ ያ ስፍራ የት እንደሆነ እራሴን እጠይቃለሁ። እግሮቹ ላይ ቡትስ ኣድርጎ ነበር ፈረሱን ሲጋልብ የነበረዉ ቢባል ኣይደንቀኝም።

ኣሁን ጥያቄዉ እንግሊዝ ሃገር ቋ ቋ የሚለዉ ቡትስ አይነትን ጨምሮ በትልቅ ወጪ ተገዝቶ ሲደረግ ስሙ ራሱ ከዉጪ በመጣ ጫማ ላይ ፌዝ ምንድነዉ? ብዙ ኢትዮጵያዊያን ርካሹን ቡትስም ኣጥተዉ በእግሮቻቸዉ በሚሄዱበት ሃገር።

በኢትዮጵያ ኣብዮት ዋዜማ ላይ በኢኮኖሚዋ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጋር ተመጣጣኝ ደረጃ ላይ ነበረች የተባለች ጃፓን እንዴት ነዉ በአለም ላይ ወደ ሁለተኛ መጥቃ የነበረች ግዜ ኢትቶጵያ ዉስጥ ስንቶች ባዶ እግሮቻቸዉን እየኖሩ አፈር ገፍተዉ ቡትስን እንኳን መግዛት የቻሉት ለፌዝ የሆኑት?

ካዛም የበለጠ ተማረ የሚባለዉ የቡትስን አሰራር መማር፣ ማሻሻል፣ እና ማስፋፋት ያስፈልጋል እንጂ የልጅ ፌዝን ማስፋፋት ኣያስፈልግም ማለት ኣይችልም? ቡትስ ብሎ እያፌዘ ቦቴ፣ ቡቲክ፣ ቦኬ ብሎ እያወደሰ።

የኢትዮጵያ ወጣትንስ መቼ ነዉ አፈር፣ አየር፣ እሳት፣ እና ዉሃ ማለት እየቻልክ ወደ እንግሊዝ ስደት ከማሰብ አፈር፣ አየር፣ እሳት፣ እና ዉሃ ብለህ ወደ ለሟ መቱ ሂድ ብሎ ማስተማር የሚቻለዉ? ኩራትን ዉልቅ፣ ቡትስን ጥልቅ ማድረግ ስትችል ነዉ ብሎ ማስተማር ሲቻል ጭምር ነዉ።