Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4615
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ባለሃብቱ የሳሙዬል ታፈሰ ነገር እና አዲስ አበባ ፖሊስ

Post by Abaymado » 29 Dec 2023, 03:55

የሳሙኤል ታፈሰ ነገር አልገባ ብሎኛል፡፡ ብሩን የሚነዛው ለዝና ነው?

አሁን በቅርቡ ለአረጋውያን በግማሽ ቢልዮን ብር ያሰራውን ህንጻ ሲያስጎበኝ ነበር፡፡ ይህን ማስተዋወቅ ያስፈልግ ነበር? ስራው ብቻ ይናገር ነበር እኮ፡፡

ከዛ ደሞ ሌላው የሚገርመው ፖሊስ ጣብያ ማሰራቱ ነው፡፡ ይህ እንዴት ያስኬዳል? ይህን ማሰራት ያለበት መንስት እንጂ ግለሰብ ሊሆን አይችልም፡፡ ኮሚሽኑ ምን እያሰበ ነው ይህን ለግለሰብ የሚሰጠው? ሰውየው የሚያገኘው ጥቅም ይኖራል?
ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ፖሊስ ጣብያዎች ሽንትቤት እንደሚመስሉ ጽፌና መንግስት ራሳቸውን የቻሉ ህንጻዎች ማሰራት አለበት ብዬ ነበር፡፡ በዋና መሃል ከተማ የሚገኘውን ፖሊስ ጣብያ ለዚህ ሰውዬ መልቀቅ ምን ይሉታል?

ባለሃብት ለዚህ አለም ቀውስ ነው ተብሎ በአሜሪካ አገር በህዝብ ይብጠለጠላል፡ ደሃ አገር ደሞ ይሰገድለታል፡፡ በዚህ አካሄድ አገሪቱን ባለሃብት ነኝ የሚል ሁሉ በእጁ ያስገባል ማለት ነው፡፡