ተታላይ ቃል ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም። ከተመቸኝ ቃል መሆን ኣለበት። በቃ። ካልሆነ ተተኪዉን እፈልጋለሁ። በቃ።
በልጅነቴ ኣንድ የቤተሰብን ቀልድ እሰማ ነበር። የጎሳዎች መቀላለድ። እስከዛሬ ድረስ ከጉራግኛ ጋር እንደሚተዋወቁ ኣላዉቅም። ነን ወይም ነበርን ሲሉ ሰምቼ ኣላዉቅም። ገበሬዎች ነን ሲሉ የሰማሁኝ።
የሆረስ ኣንትሮፖሎጂ ጥናት ምን እንደምያወጣ እሱ ነዉ የምያዉቀዉ።
የቤተሰብ ቀልዱ፣ እየተሳሳቁ የሚቀልዱት፣ ወረ እንዳንቆ ሆረ ነቁ ማለት ነዉ።
ከብቶችን የምያረባ ጎሳ ከብቶቹን ሆረ ወይም ጠበል ሲወስድ ኣይቶ ዶሮዎችን የምያረባም ዶሮዎችን ጠበል መዉሰድ ማለት ነዉ።
ቀልድ ነዉ። ያልጀመርኩት። የማልችልበት።
ሆረስን በአካል ኣላዉቀዉም፣ እዚህ ፎረም ላይ በስም እንጂ።
ኣእምሮዬ ዉስጥ ስዬዋለሁ። ከልጅነቱ እስክ እዉቀቱ።
እሱም ኣእምሮዉ ዉስጥ ስሎኛል ብዬ እገምታለሁ።
ከልጅነቱ እስከ እዉቀቱ የሳልኩት ይሀዉ። እሱ የሳለኝም ይሀዉ።
እኔ ከባላገር። እሱ ከከተማ። ይመስኛል።
በእግሮቼ ሄጄ ነዉ አቅም ያገኘሁኝ። አቅም ኣግኝቼ ቡትስ ገዝቼ እግሮቼን ነፃ ካላወጣሁ ሞቼ እገኛለሁ ኣልኩ።
ጠበል ባልወስዳቸዉም ዶሮ ኣርብቼ እንቁላል ሽጬ፣ በጎች ኣርብቼ ሽጬ፣ ድንች፣ ሽንኩርት፣ ካሮት፣ ጥቅል ጎመን፣ ቀይስር ተክዬ ሽጬ፣ መሬት ደቅድቄ ምስር ዘርቼ ሽጬ፣ ሃገር ኣቋርጬ ቡና ነግጄ፣ ሹራብ መስራትን እራሴን አስተምሬ ሰርቼ ሽጬ፣ ዘምባባን ጠላልፌ ባርኔጣ ሰርቼ ሽጬ፣ በኣንድ እጅ ዱላዬን ይዤ፣ በሌላዉ እጄ ኪሴን ጠበቅ ኣድርጌ የሆረስ መደብር ከች ነዋ። ቡትሴን ለመግዛት።
የሆረስ መደብር እንደጉድ ነዉ። ልብስ በየአይነቱ፣ ጫማ በየአይነቱ።
እኔ የምፈልገዉን ቡትስ እያያሁ፣ ዱላዬን ይዤ ጠጋ ብዬ ደና ኖ ጌታዬ እላለሁ። ዱላዬን የጎሪጥ እያየ ደህና ይላል። ወድያዉ በዉስጤ ለካ ደህና ነዉ የሚባለዉ ብዬ ቃሉን ቅልብ ኣድርጌ ያ ቡትስ ጫማ ስንት ኖ ጌታዬ እላለሁ። አስር ብር ነዉ። ቁጥርህ ስንት ነዉ ይለኛል። ኣሁን ደግሞ ለካ ነዉ የሚባለዉ ብዬ ሌላ ቃል ቅልብ ኣደርጋለሁ። በነፃ። የምን ቁጥር ነዉ ጌታዬ እለዋለሁ፣ የቀለብኳትን ቃል መልሼ እየወረወርኩለት።
የእግሮችህ ልክ ማለት ነዉ ይለኛል። ተለክተዉ ለማያዉቁ እግሮች የልክ ቁጥር ይጠይቀኛል። ኣላዉቅም ጌታዬ እለዋለሁ። ካልገዛሁ ሞቼ እገኛለሁ ያልኩትን ሳልገዛ መመለስ ኣልፈልግም።
አቧራ ለበስ እግሮቼን አየር በአየር ግልምጥ ኣድርጎ ይሄ ነዉ የሚሆንህ ብሎ ስያቀብለኝ በፍጥነት የስቀመጥኳትን ባዉንድ ከኪሴ ኣዉጥቼ እሰጠዋለሁ። መልሼ መላልሼ ኣመሰግናለሁ ጌታዬ እያልኩ። እግሮቼ በእሾህ ስንት ቦታ የቆሰሉትን እየነገርኩት። ከኣሁን በኋላ በቃ እያልኩት።
ከፈለከ ሌሎችም ኣሉን ይላኛል። ኣስኮዉን፣ ሎርዱን፣ ጫማ በየአይነቱ እያሳየኝ። ያ የምያምረዉን ለወደፊት ካልገዛሁ ሞቼ እገኛል፣ ለዛሬ ይሄ ነዉ እላለሁ። በዉስጤ አቅምን ኣዉቆ መኖር ታላቅ ችሎታ ነዉ እያልኩ።
ተስማምተን እዛዉ በረንዳ ላይ በቁምጣዬ ቁጭ ብዬ፣ ዱላዬን ከጎኔ ኣድርጌ ኣዲሱን ብርቅ ቡትስ ከእግሮቼ በእጆቼ አዋረ፣ አቧራ የሚባለውን፣ እየጠረኩ ኣጠልቃቸዋለሁ።
ኣጥልቄ ሳልጨርስ ሌላ ገዢ ይመጣ እና ያ የምያምረዉን ጫማ ስንት ነዉ ይለዋል። ሰላሳ ብር ነዉ ይለዋል።
ካዛም ቀንስ እንጂ ነብሴ ይለዋል። ከዛም በቃ ሃያ አምስት ክፈል ይለዋል። እኔ በረንዳዉ ላይ ቁጭ ብዬ የገዛሁትን ቡትስ ኣጥልቄ ሳልጨርስ።
ጆሮዎቼ በሰሙት ቀር ይሉ እና ኣንቴ እለዋለሁ። ኣንተ ወይም አተ ማለት ኣላዉቅም። እኔ የማዉቀዉ ኣንቴ፣ ወገን ማለት ነዉ። ቃሉ ያዉ ኣንድ ቃል ነዉ ብዬ።
ቀር ያሉት ጆሮዎቼ አመሌን ይቀሰቅሱብኛል። ዱላዬ ቅርቤ ነዉ። ቀልድ ኣያዉቁም ከሚባል ሰፈር ነዉ የመጣሁኝ። ያወጡልን ስም ነዉ።
ስንቴ ጌታዬ ያልኩት ቀንስ እንጂ ነብሴ ሲባል እሺ ብሎ ሲቀንስ ለመጀመርያ ግዜ ስሰማ፣ ከገዛሁ በኋላ፣ ኣንቴ ብዬ፣ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዱላዬን ኣናቱ ላይ እርፍ።
ቶሎ ኡ ኡ ጨጨብሳ ሲል እኔ ዱላዬን ኣንገቴ ላይ ኣድርጌ፣ በግራም በቀኝም እጆቼን ዱላዬ ላይ ኣድርጌ ዘገም ዘገም ማለት እጀምራለሁ።
ምንድነዉ ብለዉ ወደ እሱ የሚሮጡት እኔ ዱላዬን ይዤ፣ ቁምጣዬን ለብሼ፣ ቡትሴን ቦጭ ቦጭ እያረኩ፣ ወድያ ወዲህ እያያሁ ዘገም ዘገም ስል ያልፉኛል። እሱ ጨጨብሳ ብሎ ኡ ኡ ሲል የሰማ ዱላዬን እያየ ማን ይጠጋኛል፣ ጨባ ሊሆን?
እኔ ከሄድኩ በኋላ የደረሱለትን ምን እንደምላቸዉ ኣላዉቅም። ሰንቴ ጌታዬ ላለኝ ሳልቀንስ ኣንዴ ነብሴ ላለኝ ስለቀነስኩ ይል ይሆን ብዬ ኣመነታለሁ።
እያዘገምኩ የወንዱሙ ሻይ ቤት ስደርስ ደግሞ ጎራ እላለሁ። ሻይ ቤቱም እንደጉድ ነዉ። ሻይ ከሳጥን የሚቀዳበት። እዛ ቀንስ ዬለም። ሁለት ፉርኖዎች ከኣንድ ብርጭቆ ሻይ ጋር በስሙኒ ተገዝቶ ምሳ የሚባልበት ነዉ። ያን ያህል ድሮ ግዜ ነዉ።
ፉርኖዎቹ ማማራቸዉ። ጉንቱተ ይመስላሉ። ለምን ሁለት ኣድርገዉ እንደሚሸጡ ኣላዉቅም። ዳቦሽ ለምን እንደሚባልም ኣላዉቅም።
በልጅነት ወረ እንዳንቆ ሆረ ነቁ ተብሎ ሲቀለድበት የሰማሁኝ፣ ቀድሞኝ ከተማ ደርሶ ስንቱን እቃ፣ ስንቱን ሳጥን ደርድሮ የጠበቀኝ ይሆን?
እዚህም ፎረም እራሱን ሆረስ ብሎ ሰይሞ ቀድሞ ደርሶ ጠበቀኝ።
ከልጅነት የጀመረ መከራከራችን እስከ ዕዉቀት ቀጥሏል።
ሰዉን ከልጅነቴ ጀምሮ ኣዉቃለሁ። በሁለት እግሮች ከቆመ፣ ሁለት እጆች ያሉት ከሆነ፣ መንቀሳቀስ የሚችል ከሆነ፣ እጆቹ ላይ አምስት፣ አምስት ጣቶች ያሉት ከሆነ፣ ሌላ ሳይንስ ኣያስፈልገዉም፣ ሰዉ መሆን ኣለበት እለዋለሁ።
ይህ ሳይንሳዊ ኣይዴለም ይለኛል። የቆመዉ በሁለቱም ጎኖቹ መተኛት እንደሚችል ማረጋገጥ ያስፈልጋል ይለኛል። አምስት አምስት ጣቶች እጆቹ እና እግሮቹ ላይ መኖራቸዉ በቂ ኣይዴለም ይለኛል። እያንዳንዱ ጣት ላይ ጥፍር መኖራቸዉን በሳይንስ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ይለኛል። እሱ ትዕግስተኛ ሳይንቲስት ነኝ ይላል።
እኔ አመል ኣለብኝ። ዱላዬ ቅርቤ ነዉ። ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ያማዉቀዉን ሰዉ ሳይንስ ብለህ ልታስተምረኝ ነዉ ብዬ ኣሁንም ኣናቱን።
በቅርቡ ቀላል ጥያቄ ጠየኩኝ። ቀላሉን ጥያቄ ከሁሉም ቀድሞ በትክክል መለሰ። በዛ ኣላበቃም። ቀላል ስህተት ጨመረበት። ስህተቱን ኣልፌ የመለሰዉን ቀላል ጥያቄ ትክክል ነህ ኣልኩት።
ተመልሶ መጣ። አመሌ ተነሳብኝ እና ሳይንሳዊ ድፊት ጥምድ ኣደረኩለት። ኣስጠንቅቄ። ቀላል እና ኣጭር ጥያቄ ብዬ። ቋንቋን ከመናገር እና ከመጻፍ የቱ ይቀድማል ብዬ። መልሱን እያወኩኝ።
ያስጠነቀኩትን ኣንቦ የሳይንስ ድፊት ዉስጥ ገብቶ ወዬ፣ ወዬ፣ እወይ፣ እወይ ኣለ። ከዛም የሳይንስ ድፊት ዉስጥ ቆሞ ወዬ ወዬ ያለዉን ስብስብ ኣድርጌ ደህና ዋል ብዬ ከሳይንስ ድፊቱ ለቀኩት።
ሳይንስ እና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ የቀጥላል፣ ይለምልም ብዬ።