
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
nSrspeotdo217lig7i5h8gl6cc10a1t3g2ui8f
h
886g4u7a41
4
8fcl1im31l
·
"የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚጠብቅና ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ አየር ኃይል እየተገነባ ነው"
- ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚጠብቅና ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ አየር ኃይል እየተገነባ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 88ኛ ዓመት በዓል እያከበረ ነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይሉን የዘመናት ውጣ ውረድ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም አፍሪካውያንና እስያውያን አውሮፕላን በማያውቁበት ወቅት ኢትዮጵያ አየር ኃይል አቋቁማ ለተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ስትጠቀም እንደነበር አስታውሰዋል።
አየር ኃይሉ በሀገር ላይ የተቃጡ የወረራ ሙከራዎችን በመመከትም የላቀ ጀብዱ መፈጸሙን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1982 ዓ.ም በአፍሪካ የላቀ ደረጃ ደርሶ እንደነበር ገልጸው፤ ከዚያ በኋላ በተካሄደ የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ምክንያት አየር ሃይል ለውድቀት መዳረጉን አስታውሰዋል።
ለአብነትም፤ የአየር ሃይሉ ብቁ በራሪዎችና ቴክንሺያኖች እንዲበተኑ፣ አውሮፕላኖቹ ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ፣ መሰረተ ልማት እንዳይኖረው መደረጉን ጠቅሰው አየር ሃይል አያስፈልግም እስከሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ተደርሶ ነበር ብለዋል።
ሆኖም የለውጡ መንግሥት መምጣቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የላቀ አየር ሃይል ያስፈልጋታል የሚል አቋም በመያዝ በፖሊሲና በበጀት ስትራቴጂካዊ ለውጥ መደረጉን ገልጸዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን የአየር ክልል የሚያስጠብቁ ሀገር ወዳድ ሙያተኛና አመራር፣ ዘመናዊ ትጥቆች፣ የውግያ መሰረተ ልማት እና ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር መቻሉን ነው ያብራተሩት።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የአየር ክልል በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ 24 ሰዓት በአስትማማኝ ደረጃ እየጠበቀ ይገኛል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያን የሚመጥንና ሀገርና ህዝብን በሰላም በዘላቂነት ማቆየት የሚያስችል ታላቅ አየር ሃይል እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያለችበት ቀጣና ስትራቴጂካዊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች የሚስተናገዱበት ከመሆኑ አኳያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በአስተማማኝ ሁኔታ እናስጠብቃለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በህዝብና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ታላቅ ሀገር መሆኗን ያነሱት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ከዚህ አኳያ ለታላቅ ሀገር የሚመጥን ታላቅ አየር ሃይል እየገነባን ነው ብለዋል።
በተለይም አሁን ዓለም ከአየር ሀይል እስከ ሳይበር የበላይነቱን ለማሳየት እየተሽቀዳደመ በመሆኑ ኢትዮጵያም ያንን ታሳቢ አድርጋ እየሰራች መሆኗን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የላቀ አየር ሀይል ነበራት ያሉት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ በ1960 በኮንጎ ሰላም ማስከበር መሳተፉንም ገልጸዋል።
አየር ሃይሉ በአንድ ወቅት የታንዛኒያን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ ሲጠብቅ እንደነበር በማስታወስ፤ በሱዳንና ደቡብ ሱዳንም የሰላም ማስከበር ትልዕኮን በብቃት መወጣቱን ተናግረዋል።
አየር ሃይል በቀጣናዊና በአህጉራዊ ሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የላቀ ሚና የመወጣት ሚና ይዞ እየሰራ ሲሆን በቅርቡም በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ይህንን የላቀ ሚና ለማጠናከር እየተሰራ ሲሆን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ በሁሉም መስክ ቀዳሚ የሆነ አየር ሃይል እውን እናደርጋለን ነው ያሉት።