በስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ ባለው የፀጥታ ችግር የተነሳ፣ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በአንድ ክፍለ ጦር እየተጠበቀ እንዲያመርት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት፣ የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ናቸው፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን የ2016 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት፣ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነበር፡፡
የከሰም የስኳር ፕሮጀክትም ቆሞ ለሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ ከስኳር ልማት ፈንድ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው፣ በተመሳሳይ ኦሞ አንድና አርጆ ደዴሳ ከሌሎች ፋብሪካዎች በሚገኝ ገቢ ወጪያቸው እየተሸፈነ ነው ብለዋል፡፡
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካም በ2015 ዓ.ም. በፀጥታ ምክንያት ማምረት ባለመቻሉ፣ ከሌሎች አራትና አምስት ፋብሪካዎች ከተገኘ ገቢ ወጪው ሲሸፍን እንደነበር ገልጸው፣ በፀጥታ ምክንያት ስኳር የማያመርቱ ፕሮጀክቶች፣ እንዲሁም ማምረት ጀምረው ካቆሙት መካከል ከሰም፣ ተንዳሆ፣ አርጆና መሰል ፋብሪካዎች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል፡፡
ነባር ከሚባሉት ፋብሪካዎች መካከል ወንጂ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ሦስትና ፊንጫ የተሻሉ የሚባሉና ጥሩ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ አሁንም ትልቁ ችግራቸው ፀጥታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ፊንጫ ከ19 ሺሕ ሔክታር ወደ 11 ሺሕ ሔክታር መውረዱን፣ አብዛኞቹ ማሽኖች መቃጠላቸውንና አርጆ ከቁጥጥር ውጪ የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ጥረት መመለሱን አስረድተዋል፡፡
ከመተሐራ ፋብሪካ 4,800 ሔክታር መሬት አገዳ መጥፋቱን አስታውቀው፣ ፋብሪካዎች የፀጥታ ችግሮች ካልተቀረፈላቸው የተሻለ ስም የነበረው የስኳር ምርት ስሙን ብቻ ይዞ ይቀራል ብለዋል፡፡ ‹‹በመሆኑም ከቋሚ ኮሚቴው ትልቅ ዕገዛ እንፈልጋለን፤›› ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ መንግሥት የፀጥታ ችግሩን ካላስተካከለ የስኳር ችግርን መፍታት አይችልም ብለዋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/124778/
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4487
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4487
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ እንደገለጹት:- የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በአንድ ክፍለ ጦር እየተጠበቀ እንዲያመርት ተደረገ :)
"የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተቋማቸውን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ኅዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርቡ፣ ‹‹የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ ሌባ፣ ሽፍታና ወንበዴ ማፅዳት አይደለም፡፡ ሚሊሻ ምን ይሠራል? ከዚያ ካለፈ ፌዴራል ፖሊስ የት ይሄዳል? ይህንን አስተሳሰብ ካላስተካከልነው በየመንደሩ ያለውን የሌባ እንቅስቃሴ መከላከያ መጥቶ ያፅዳ የሚል ፍላጎት እየሰፋ ከሄደ፣ ሠራዊቱ ሥራውን ማከናወን አይችልም፤›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ የአገር ሉዓላዊነት ማስጠበቅና ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መመከትና ማስቀረት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፣ ‹‹ጠንካራ የመከላከያ ሠራዊት መገንባት አለብን እንጂ፣ የሠራዊቱ ተግባር በየመንደሩ ያለን ሌባ ማሳደድ ባለመሆኑ ይህ መሠረታዊ ችግር መስተካከል አለበት፤›› በማለት ለቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቢያ አቅርበው ነበር፡፡"

ሚኒስትሩ አክለውም የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ የአገር ሉዓላዊነት ማስጠበቅና ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መመከትና ማስቀረት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፣ ‹‹ጠንካራ የመከላከያ ሠራዊት መገንባት አለብን እንጂ፣ የሠራዊቱ ተግባር በየመንደሩ ያለን ሌባ ማሳደድ ባለመሆኑ ይህ መሠረታዊ ችግር መስተካከል አለበት፤›› በማለት ለቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቢያ አቅርበው ነበር፡፡"