Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ኢትዮጵያ፡ ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም!

Post by kibramlak » 16 Feb 2022, 17:12

Horus wrote:
16 Feb 2022, 13:29

ስለዚህ የያንዳንዱ የፖለቲካ ተዋኛን ሆነ (አንተንም ጨምሮ) የፖለቲካ ቡድን መቆሚያ፣ ሚና፣ ህሳቤ፣ መለኪያው በነዚህ አራት ቅራኔዎች ዳይናሚክስ አማካይነት ነው ። ኮንሺየስነስ ማለት ንቃተ ስሜት ማለት ነው ። አንድ ግለሰብ ፖለቲካ ወስጥ የሚካፈልበት ሞቲቬሽን አራት ናቸው፤ (1) ስልጣን ወይም ሃይል ለማግኘት፣ ማን ምን ማድረግ ምን ማግኘት እንዳለበት ለመወሰን (2) ገንዘብ፣ ሃብት ወይም መሬት ለመቆጣጠር፣ (3) ዘነኛ ለመሆን፣ ለመታወቅ፣ ለመወደድ፣ (4) ለመከበር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ማንነትቱ እና ዲግኒቲውን ለማረጋገጥ ነው ። ከዚህ ውጭ ሌላ ገፊ ሞቲቬሽን የለም ። አንተም አንድን የፖለትካ አቋም የያዝከው፣ ሌላውም የራሱን የፖለቲካ አቋም የያዘው ለዚህ አላማ ነው ።
Horus,

እላይ የጠቀስካቸው 4 የፖለቲካ ሞቲቬሽን ላብዛኛወች ፔለቲካን መተዳደሪይያ ላደረጉ ሰወች ይሆናል እላለሁ፣፣ ነገር ግን ለ የኔ ቢጤ ላምዳ ለሆነ ሰው ከዚህ በፊት እላይ የቀስኳቸው ሶስት የመንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶች ሲቃወሱ የተቃውሞ ምንጭ ይሆናሉ እላለሁ፣፣ ታድያ ሁሉም የሚያጠነጥነው የፍትሀዊነት ችግር ሲስተዋል ነው፣፣ ኢፍትሀዊ ክስተቶችን ለመቃወም ፖለቲከኛ የግድ መሆን አያስፈልግም፣፣ ስለዚህ በሶስቱ መሰረታዊ የመንግስት አገልግሎቶችን በኢፍትሀዊ መመዘኛ እንደሚከተለው ማየት እንችላለን፣-

፩) የኢኮኖሚ ኢፍትሀዊነት፣- አንዱ በልቶ ሌላው ሲራብ (ሌላም ምሳሌ መጨመር ይቻላል) ወይም አዱ ሲደጎም ሌላው ሲረሳ
፪) የደህንነት ኢፍትሀዊነት፣- ለአንዱ ከለላ ለሌላው ስጋት ስንሆንበት ፣ እንደ ጥሩ ምሳሌ የ መንግስት ነን ባይ ፖሊሶች አውዳሚ ቄሮወችን ትተው ሰላማዊ ህዝብን ሲደበድቡ ስታይ (በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው)
፫) የፍርድ ኢፍትሀዊነት፣- ፍርድ ሲዛባ (የእስክንድርያ እና የነጃዋርን መታሰርና መፈታትን አነፃፅር) ፣ የተፈናቃይ እና የአፈናቃዮችን ጉዳይም አነፃፅር ከፍትህ አንፃር

በነገራችን ላይ፣ እኔ ጎሰኝነትን የማጠቃልለው በኡፍትሀዊነት ነው፣፣ በጎሰኝነት የኡኮኖሚ፣ የደህንነት እና የፍርድ ኢፍትሀዊነት ታገኝበታለህ፣፣ ይህ ኢፍታዊነት ነበር ትህነግን ያባረራት፣ አሁንም ተረኞች ጋ የተፈጠረው ተቃርኖ ጎሰኝነት ባመጣው ኢፍትህዊነት እንጅ ትግሪ ወይም ኦሮሞ ተብለው እንደፍጡር በመሰየማቸው አደለም፣፣ ምክንያቱም የዜጋ ፖለቲካ ቢመጣም ትግሬም ሆነ ኦሮሞ ማንነቱን አይቀይርም፣፣ በጎስ ምክንያት ግን ኢፍታዊነት የተላበሰ ጥቅማጥቅም አያገኝም (በአንፃራዊ ማለቴ ነው)

Horus
Senior Member+
Posts: 42630
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢትዮጵያ፡ ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም!

Post by Horus » 16 Feb 2022, 18:13

Kibramlak,
አሁን ውይይቱ ከአንቲፍራጂሊቲ ወደ ፍትህ መጥፋት ሂዷል፤ ያ ሌላ አለም ነው። አንድ የገዥ ቡድን ስልጣን ሲይዝ እና ስልጣኑን ተግባሪ ማድረጊያ የአመጽ መሳሪያዎች ሲገነባ፣ ሲቆጣጠር ለማሰርና ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ሁሉን ነገር ለመወሰን ነው ። ማን ምን ማድረግ ወይ አለማድረግ ይችላል? ማ ምን ማግኘት አለበት የለበትም? ወዘተርፈ! አንድ ሕዝብ በሕግ ሳይሆን በሰዎች እስከ ተገዛ ድረስ ያነሳሃቸው የኢኮኖሚ፣ የሶሻል እና የፖለቲካ ፍትህ ሊያገኙ ፈጽሞ አይችሉም ። አልፎ አልፎ እንደ ሃብተ ጎርጊስ አባ መላ አይነት በትክክል የሚፈርዱ ግለሰቦች ካልሆኑ በስተቀር! እናም እኒህ ያልካቸው ፍትሆች በጎሳ ስርዓት ስር ፈጽሞ ፈጽሞ አይሟሉም። ይህም የሚሆነው ግለሰቡ ሉዓላዊ መብቱና ሃይሉ ተቀምቶ ለጎሳ መስፍን ወይም ለጎሳ የቢሮ ከበርቴ የተሰጠ ስለሆነ ነው ። የኢትዮጵያ ግለሰብ ዜጋ ዲስኢምፓወረድ የሆነ ስልጣኑ የተሰለበ፣ የተኮላሸ ስለሆነ ነው ። ያም የሆነው በጎሳ ነጋዴ የዘር መሳፍንቶች ብቻ አይደለም ፣ እራሱ ግለሰቡ እራሱ ተፈጥሮአዊና ሶሺያላዊ የማይገሰስ መብቱን የሚያውቅበት ንቃተ ስሜት ወይም ኮንሺየስነስ እድገት ስላልደረሰ ነው። ጎሳ የሚለው ጽንሰ ሃሳብ እንደ ፖለቲካ ፋክት ተቀብሎ በዚያ ዙሪያ የሚደራጅ ግለሰብ ሉዓላዊ ስብዕና እድገት ላይ የደረሰ አይደለም ። እዚያ እንዲደርስም የራሱ የጎሳ መሳፍንቶቹ አይፈልጉም! ሳይንሱ ይህ ነው ። ይህ እንዲሆን ሰዎች በጎሳ የዳቦ ስማቸው ሳይሆን በስብዕና ልዕልናችው መደራጀታቸውና በሰው ሳይሆን በሕግ መገዛታቸው የግድ ይላል! ኬር

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ኢትዮጵያ፡ ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም!

Post by sarcasm » 04 Dec 2023, 17:42

The secrete of Ethiopian progress by ሆረስ ልበ ብርሃን

ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም? If this is not the epic war sermon, what is?
Horus wrote:
24 Dec 2021, 14:13
ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ ድረስ ሳይፈተሽ በጥሬው የተዋጠውን እምነት በማፍረስ ላይ ነች ። ይህ ጥሬ እምነት ሰላም ከሌለ እድገት ብልጽግና የለም የሚለው ልማድ ነው ። ይህ ልማድ ነው። ሰላምና ብልጽግና በጥገኛነት ያስተሳሰረው ያው የሰው ሃሳብ ነው ። ይህን ልማዳዊ እምነት የሚያፈርስ አዲስ ፓራዳይም ወይም ቅድመ መርህ፣ ሌላ ስልት አለ።

ይህም አንቲ ፍራጂሊቲ ወይም ጸረ ተሰባሪነት ይባላል። ጸረ ተሰባሪ ነገር በቀውስ፣ በችግር፣ በሁከት የሚጠነክር፣ የሚበለጽግ፣ የሚፋፋ ማለት ነው።ይህም ማለት ጦርነት እንደ አንድ የእድገት መሳሪያ፣ የህብረት፣ የብልጽኛ፣ የትብብር እና የትጋት ዘዴ ነው ። ይህን ነገር በጥልቀት እና ክሪኤቲቭ ሆነን መመርመር አለብን።

ይህን የድሮ ያረጀ ፓራዶግማ ይዘው ኢትዮጵያን ለረጅም ግዜ በጦርነት ከወጠርናት ካሰበቸው እድገትና ሃላልነት እናደናቅፋታለን የሚለው ያሜርካና ያውሮፓ እስትራተጂ ከስሩ የምናከሽፈው አሁን ያለውን የምዕራብ የብልጽግና ንድፈ ሃሳብን የሚሽር አዲስ ፓራዳይም በመጠቀም ነው ። ለዚህም አንዱ አዲስ ፍልስፍና ጦርነት የኢኮኖሚ እና የሶሺያል እድገት መተግበሪያ ዘዴ ማድረግ ነው ።

ጦርነት የህዝብ ዲሲፕሊን የሚፈጥር ገፊ ሃይል ነው፤
ጦርነት ህዝብን አንድ ያደርጋል፤
ጦርነት ህዝብ እንዲተባበር ያደርጋል፤
ጦርነት ህዝብ በትጋት ጠንክሮ እንዲሰራ ያደርጋል፣
ጦርነት ህዝብ ፈጣሪ፣ ፈልሣፊ እንዲሆን ይገፋል ።
ጦርነት ህዝብ ቆጣቢ እንዲሆን ይገፋል፤
ጦርነት የህዝብ ንቃተ ህሊና ያሳድጋል ፤
ጦርነት ህዝብን ችግር መፍታት ያስተምራል፣
ጦርነት ህዝብ ሁሉ እንደ ወታደር እንዲያስብና እንደ ወታደር እንዲታገል የሚረዳ አዎንታዊ ሃይል ነው !
ይህ ነው አዲሱ ፍልስፍና፣ አዲሱ ፓራድይም !!!

በአ ሆረስ

Horus
Senior Member+
Posts: 42630
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢትዮጵያ፡ ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም!

Post by Horus » 04 Dec 2023, 23:48

sarcasm wrote:
04 Dec 2023, 17:42
The secrete of Ethiopian progress by ሆረስ ልበ ብርሃን

ጦርነት ለእድገትና ብልጽግና ያለው ከፍተኛ ጥቅም? If this is not the epic war sermon, what is?
Horus wrote:
24 Dec 2021, 14:13
ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ ድረስ ሳይፈተሽ በጥሬው የተዋጠውን እምነት በማፍረስ ላይ ነች ። ይህ ጥሬ እምነት ሰላም ከሌለ እድገት ብልጽግና የለም የሚለው ልማድ ነው ። ይህ ልማድ ነው። ሰላምና ብልጽግና በጥገኛነት ያስተሳሰረው ያው የሰው ሃሳብ ነው ። ይህን ልማዳዊ እምነት የሚያፈርስ አዲስ ፓራዳይም ወይም ቅድመ መርህ፣ ሌላ ስልት አለ።

ይህም አንቲ ፍራጂሊቲ ወይም ጸረ ተሰባሪነት ይባላል። ጸረ ተሰባሪ ነገር በቀውስ፣ በችግር፣ በሁከት የሚጠነክር፣ የሚበለጽግ፣ የሚፋፋ ማለት ነው።ይህም ማለት ጦርነት እንደ አንድ የእድገት መሳሪያ፣ የህብረት፣ የብልጽኛ፣ የትብብር እና የትጋት ዘዴ ነው ። ይህን ነገር በጥልቀት እና ክሪኤቲቭ ሆነን መመርመር አለብን።

ይህን የድሮ ያረጀ ፓራዶግማ ይዘው ኢትዮጵያን ለረጅም ግዜ በጦርነት ከወጠርናት ካሰበቸው እድገትና ሃላልነት እናደናቅፋታለን የሚለው ያሜርካና ያውሮፓ እስትራተጂ ከስሩ የምናከሽፈው አሁን ያለውን የምዕራብ የብልጽግና ንድፈ ሃሳብን የሚሽር አዲስ ፓራዳይም በመጠቀም ነው ። ለዚህም አንዱ አዲስ ፍልስፍና ጦርነት የኢኮኖሚ እና የሶሺያል እድገት መተግበሪያ ዘዴ ማድረግ ነው ።

ጦርነት የህዝብ ዲሲፕሊን የሚፈጥር ገፊ ሃይል ነው፤
ጦርነት ህዝብን አንድ ያደርጋል፤
ጦርነት ህዝብ እንዲተባበር ያደርጋል፤
ጦርነት ህዝብ በትጋት ጠንክሮ እንዲሰራ ያደርጋል፣
ጦርነት ህዝብ ፈጣሪ፣ ፈልሣፊ እንዲሆን ይገፋል ።
ጦርነት ህዝብ ቆጣቢ እንዲሆን ይገፋል፤
ጦርነት የህዝብ ንቃተ ህሊና ያሳድጋል ፤
ጦርነት ህዝብን ችግር መፍታት ያስተምራል፣
ጦርነት ህዝብ ሁሉ እንደ ወታደር እንዲያስብና እንደ ወታደር እንዲታገል የሚረዳ አዎንታዊ ሃይል ነው !
ይህ ነው አዲሱ ፍልስፍና፣ አዲሱ ፓራድይም !!!

በአ ሆረስ

Read Nassim N. Taleb, Antifragile: things that gain from disorder. (2012)

Post Reply