Re: Man’s World - እዮሃ ሜዲያ ፣ ፍርደ ገምድል ባለሙያ - ስለ ሚስትዮዋ መሰደብና መደብደብ አንዲት ቃል አላላም!
መሰረታዊ ማስተዋል የጠፋበት ዘመን ማለት ይህ ነው። ልጆቹ የኔ መሆናቸው ከተረጋገጠ፣ ሰላም እሰጣታለሁ ለሚስቴ አለ። ገና ለገና፣ የሱ ወላጆች ስለወሰለቱ ብቻ፣ በምን ሂሳብ ነው ሚስቱን መጠርጠሩ፣ ማጎሳቆሉና መደብደቡ? የቅናት በሽታ አናቱን ስላዞረው ነው እንደዚህ የሚበጠብጠው፣ እንጂ ሌላው ምክንያት ሁሉ ማደናበሪያ ነው። ወንድ ልጅ እጁን ሴት ልጅ ላይ ካሳረፈ በተለይም እናት ላይ፣ ከርቸሌ መማቀቅ አለበት።