Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42655
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የተጠላና የተናቀ ዲክታተር እንደ ወደቀ ይቆጠራ

Post by Horus » 27 Oct 2023, 01:24

ትላንት ከታች ያለው ግምት ሳቀርብ አንድ ያላነሳሁት ነገር ነበር። አቢይ አህመድ መፈራት ቢሞክርም ሕዝብና ለነጻነት ታጋዮች አይፈሩትም ፣ ለዚህ ችግር መፍትሄ የለውም ብዬ ነበር ። ነገር ግን የመናቅን መዘዝ ሳላነሳ ቀረሁ ። በዚያ ትላንት ብዙ ቆርቆርና ብረታብረት በተርታ በመደርድር ሌላ ሳይሆን አዲስ አበቤን ለማስፈራራት ቢሞክርም ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲያስል ያድራል እንዲሉ የሚዲያ ትኩረት ከፋኖ ለመንጠቅ የለፈለፈው ገንፎ ማስፈራሪያ በራሱ ላይ ባርቆበት ታንክ እያሰለፍ እኔ ልዋጋ አላልኩም ብሎ ተሽኮረመመ!

ቁም ነገሩ ይህ ነው! አለመፈራት መናቅ ይባላል ። አቢይና የኦሮሙማ ድንፋታ የተናቀ ገንፎ ነው ። ያን ማለት ደሞ ዲክታተሩ መጀምሪያ ከተጠላ ቀጥሎ ከተናቀ እንደ ሞተ ቁጠሩት! ኧልፍ አእላፍ የብረታ ብረት ክምርና ጋጋታ የሕዝብን ፍቅርና ክብር ሊገዛ አይችልም ። አቢይ አህመድ የተጠላና የተናቀ የኦሮሙማ አባገዳ ነው!


ትላንት ...
በእኔ ግምት አቢይ አህመድ የዲክታተሩ የመጨረሻ መፍትሄ አልባ ችግር ላይ ይመስለኛል ።

ኒኮሎ ማኪያቬሊ የሜዲችን መስፍን ሲያማክር (ያቢይ አማካሪ ሌንጮ ማለት ነው) መስፍኑ የጠየቀው ነገር ትዝ አለኝ ። መስፍኑ ይጠይቃል፤ ' ኒኮሎ ግዛቴ እንዲሳካልኝ ብወደድ ነው የሚሻለው ወይስ ብፈራ?' ይለዋል ። ኒኮሎ ይመልሳል፤ 'መስፍን ሆይ ቢቻል ፣ ቢቻል ብትወደድ፣ ያ ካልሆነ መፈራት አለብህ' አለው።

የዛሬው አቢይ አህመድን ያስጨነቀው ይህ ጥያቄ ነው ። ሰውዬው እንኳንስ በሕዝቡ በራሱ ታዛዥ አሽከሮች አይወደድም፣ በፍጹም። ያ ካልሆነ ደሞ በሕዝቡም ሆነ በአሽከሮቹ መፈራት አለበት ። ዛሬ ላይ የአማራ ሕዝብ ባስነሳው አቢይን አለመፍራት አገር አቀፍ መንፈስ ሳቢያ አቢይ በህዝቡ አይፈራም ለማለት ይቻላል። አሁን የቀሩት የራሱ ተቀጣሪ አሽከሮች ናቸው ።

ጥታቄ፤ ስንቶቹ የብልጽግና አሽከሮቹ ሰውዬውን ይፈሩታል (ማለትም ፈርተው ትዕዛዝ ይፈጽማሉ?) አቢይን እንዲህ እንደ ህጻን የሚያነጫንጨውና እንደ ዱርዬ አሽከሮቹን በስድብ የሚያዋርዳቸው የማይፈሩት አሽከሮች ቁጥር ስለበረከተ ነው ። ይህ ቁልፍ ሁኔታ ነው ።

ከዚህ በኋላ አንድም አሽከር በሙሉ ልብ ትዕዛዝ አይፈጽምም ። ሁሉም በመባረር ፣ በመዋረድ ፣ ወይም በመቀጣት ፍርሃት ውስጥ ስላሉ ማለት ነው። ዲክታተሩ በራሱ አሽከሮች አለመፈራትን በገንዘብ ኃይል በጉቦና ማማለል ሊፈታው አይችልም ። ገንዘብ የሚሰጠው ለመወደድ ነው፣ አሽከሮቹ የሚፈሩት ሲቀጣቸው ነው።

በአንድ ቃል ዲክታተሩ ሊፈታው የማይችለው ችግር ላይ ደርሷል ። አሁን እየገዛ ያለው በማስፈራራት ነው ። እስከ መቼ?

ነገና ከነገ ወዲያ ሰዉ ተገድዶ ሰልፍ እንዲወጣ ይደረጋል፤ በዚያ ሰልፍ ውስጥ የምናየው የሕዝቡ ስሜት ሃቁን ይነግረናል ።


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የተጠላና የተናቀ ዲክታተር እንደ ወደቀ ይቆጠራ

Post by Za-Ilmaknun » 27 Oct 2023, 11:28

What is becoming clear is the Julla PP militia is on its final gasp. One huge blow from FANO, then all the cannibals with their Orommuma aspirations will be shatterted. It is coming ..it is coming :mrgreen: :lol:


Post Reply