በአካባቢው ቋንቋዎች ሌላ ትርጉም ካለው አካፍሉን ።
አሰብ በጉራጌኛ ጨው ማለት ነው፤ ቃሉ አሰቦ ይባላል ። አሰብ ወይም አሰቦ ቅጽል ሲሆን ጨዋማ እንደ ማለት ነው ።
ጨው የሚለው አማርኛ ቃል ጥንት ከም ከሚባል የትንታዊት ግብጽ ቃል በድምጽ ልውውጥ የወረደ ነው ።
በጉራጌኛ ጨው የሚለው ቃል ጨም ስንለው እሱም ጣፋጭ ማለት ነው ። ጨም (ጨው) ጣፋጭ ፣ የተወደደ፣ ወድ ማለት ነው ።
ጨው ወይም ከም ዛሬ ቅመም፣ ጣም፣ ጣዕም፣ ጥኡም ፣ ቅምሻ፣ ለሚሉና ሌሎች ብዙ ብዙ ቃላት መሰረት ነው ። ትልቁ ቃል ቅመም ነው ። ጨው የቅመኖች ሁሉ ንጉስ ነው ።
በጥንታዊት ግብጽ (ግብጾች ኢትዮጵያዊያን ነበሩ) ከም የነበረው ትርጉም ቀይ አፈር የሚል ነበር ። አውሮፓዊያን ተሳስተው ጥቁር አፈር ብለው ተርጉመውታል። ነገር ግ ን ቀይ አፈር የሚለው ትርጉም እንዴት ከነጭ ጨው ጋር እንደ ተያያዘ ጥቁር (ብላክ) የሚለው ቃል ነጭ ማለት እንደ ሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ። ድሮ ብላክ ማለት ነጭ ማለት ነበር ። ዛሬም ቢሆን በእስፓኝ ቋንቋ ብላንክ ነጭ ማለት ነው ።
ትክክለኛ ከም (ጨም) ቀይ አፈር ማለት ነበር ። ማናልባትም ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ አፈሳ ወይም ቦሌ የምንለው ከቀይ አፈር ጋራ የተደባለቀው ጨው ሊሆን ይችላል ።
ለማንኛውም አሰብ ማለት አሰቦ ጨዋማ ፣ ጣፋጭ ማለት ነው ።
ሆረስ ኃይለ ብርሃን