ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል --- ያልታደለች የአፍሪካ ቀንድ በችግር፤በግጭት ቀንዶ ይወልቃል። በሰገጤ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ ድብድብ ሁልጊዜ።
ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል --- ያልታደለች የአፍሪካ ቀንድ በችግር፤በግጭት ቀንዶ ይወልቃል። በሰገጤ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ ድብድብ ሁልጊዜ።በደርግ ጊዜ አንድ የመሰረተ ትምህርት መፈክር "መሀይምነት የጨለማ ጉዞ ነው" የሚል አስታወሰኝ። የእምበር ተገዳላይ፤ኬኛ ነጻ አውጭ ግንባር ዳንኪራ ሚልዮኖችን በጠበጠ። መሬት እና ውሃ ተሸክሞ ወደ መንግስተ ሰማያት የሚሄድ የለ። ይኸው ድፍን 50 አመታት አለፉ - የአንድ ሽማግሌ ዕድሜ ተጨረሰ ሌላ 50 ሽማግሌ ዕድሜ ደግሞ ያልፋል - መሬት እና ውሃ ዐይኑ እንዳየ በግጭት አፉ ተለጎሞ ወደ ፈጣሪው ይሄዳል። የነጻ አውጭ ዳንኪራ የዱር አውሬ ሁከት።