Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13066
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Two brave Eritreans to receive the Medal of Valor from Biden

Post by Thomas H » 13 Sep 2023, 08:25

የናይዝጊ እና ፍረዝጊ አስገራሚ ገጠመኝ

ናይዝጊ እና ፍረዝጊን የማውቃቸው የሀባሻ ቤተክርስቲያን ስለሚመጡ እና እኔ ስለማስተረጉምላቸው ነው::ለምን እንደሆነ አላውቅም ወደ ኤርትራውያን ቤተክርስቲያን አይሄዱም:: ሁለቱም ከኬንያ ስደተኞች ካምፕ ነው የመጡት::
እና ስደተኛ እያሉ 1 ዥንጉርጉር ሙሉ ልብስ ለሁለት ተካፍለውት ነበር:: ማለት ዥንጉርጉር ሱሪ ለናይዝጊ ዥንጉርጉር ኮት ለፍረዝጊ ተካፈሉት እና በቃ የሚዘንጡበት ልብስ ሆነ::ችግሩ ግን ይሄን ልብስ ያገኙት ኬንያ ስደተኛ ካምፕ ውስጥ እያሉ ነው:: ልብሱ የተሰጣቸው ከኬንያ ሆስፒታል ከሞቱ ሰዎች ላይ ነው:: ናይዝጊም ፍረዝጊም ሟቹን የልብስ ባለቤት አይተውት አያውቁም ነበር ነገር ግን አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ የልብሱ ባለቤት መንፈሱ ይመጣባቸዋል በህልም ይመጣባቸው እና ልብሴን መልሱልኝ ይላቸዋል.....ወዘተ እና በጣም ተረብሸዋል:: እኔ እንደመፍትሄ ያቀረብኩት ይሄን ዥንጉርጉር ልብስ መልበስ እንዲያቆሙ ነበር እነሱ ግን ቶማስ ምን ማለትህ ነው ይሄ እኮ የክት ልብሳችን ነው የምንዘንጥበት ልብስ ስለሆነ መልበስ አናቆምም አሉኝ ስለዚህ የቀረው መፍትሄ ለናይዝጊ እና ፍረዝጊ ፀሎት መፀለይ ስለሆነ እባካችሁን ናይዝጊ እና ፍረዝጊን በፀሎታችሁ አስቧቸው::


አክባሪያችሁ ቶማስ