በነገራችን ላይ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከቤተክህነት በማንነታቸው ምክንያት ከመቶ በላይ ተጋሩ የሀይማኖት አባቶች ከስራ ታግደው .. ተባረዋል።
የሚገርመው የዋልድባ ገዳም መነኩሴ አባቶችም ይህ በደልና ግፍ ደርሶባቸዋል። ዛሬ በማንነታቸው የሚታሰሩ ሰዎች እንዳሳሰባቸው በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ፋኖኤል መንግስትን አስጠንቅቀዋል።
በማንነታቸው ለተባረሩ ለዛውም በሀይማኖት ተቋም ውስጥ በራሳቸው ፊርማና ማህተም የተባረሩ እያሉ .. መንግስት በማንነት ምክንያት እያሰረ ነው ብሎ መጠየቅ በየትኛውም ሞራል ይሁን ??
ሌላው ይቅር ኦሮሞና ተጋሩ በእነዚህ አመታት ውስጥ በማንነታቸው ተይተው ሲታሰሩ ... በማጎሪያ ሲከማቹ .. የዛሬው መግለጫ ሰጪዎች አንዲት መግለጫ አውጥተው ያውቃሉ ወይ ? ጭራሽ ተባባሪ ነበሩ እኮ ..
ዛሬ በየትኛው አግባብ ነው የፍትህ ጥያቄ በስሜት በታጀበ ቃላት የሚሰጠው ... ወይስ ሰማያዊ መርህን ጠብቀው ሁሉንም በእኩልነት በፍትህ ማገልገል የሚጠበቅባቸው የሀይማኖት አባቶች ተቆርቋሪነታቸው ደምና ዘር እየለዩ ለተመሳሰላቸው ወገን ብቻ ነው ???
Please wait, video is loading...