እኩልነት (ፍትህ) v. ሰላም
አንድ የፖለቲካ ስርዓት ትክክለኛ ነው ወይስ አይደለም? ሞራላዊ ነው ወይስ አይደለም?
አንድ አገዛዝ ኢፌክቲቭ፣ ፋይዳዊ፣ ምርታማ፣ ታዳጊ ፣ ስኬታማ፣ ህዝባማ (ህዝባዊ) ነው ወይስ አይደለም?
አንድ አገዛዝን እንደግፈው ወይስ እንቃወመው የሚባሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ሁሉ መቆሚያ መሰረታቸው ሰላም ሳይሆን እኩልነት (ወይም ፍትህ) ነው።
ሰላምና አመጽ አንድን የፖለቲካ ሂደት ወይም ተግባር መፈጸሚያ መንገድ እንጂ እራሱ የፖለቲካ ይዘት (ዘ ኮንቴንት ኦፍ ፖለቲክስ) አይደሉም ።
ስለዚህ በአመጽ ስልጣን መያዝ በፍጹም አይቻል የሚሉ ስልጣን ላይ ያሉ ዲክታተሮች እና ስለ ፖለቲካ ምንነት ላይ የጠራ ሃሳብ ያልያዙ ሰዎች ናቸው።
ዜጋ v. ጎሳ
ጎሳ በሰው ልጆች አለም ውስጥ በፍጹም የፖለቲካ ማደራጃ ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ዘዴ ወይም ተግባር አይደለም፤ በፍጹም መሆን የለበትም፣ መሆን አይኖርበትም ። ለምን?
ሁለት ወይም ሶስት ወይም 88 ጎሳዎች በፍጹም፣ እስከ አለም ፍጻሜ እኩል ሊሆኑ አይችሉም ። በሰው ቁጥር እኩል የሆኑ ጎሳዎች ባለም መፈጠር አይችሉም ። እናቶች ሁሉ ለክተው እኩል ልጆች ስለማይወልዱ ። ጎሳዎች ለዘላለም በሕዝብ ቁጥር ብዛት የተለያዩ፣ አንድ ብዙ አንዱ ያነሰ ሆነው ይኖራሉ ።
በዚህ አለም ላይ ፣ በግጥረት ሁሉ እኩል ፍጥረቶች ዜጋዎች ናቸው ። ሁልግዜ አንድ ሰው ከሌላ ሰው እኩል ሆኖ የሚኖረው ሁልውቱም አንድ ግለሰብ ሆነው ስለተፈጠሩና እነዚህ የተፈጥሮ ግለሰቦች በሕገ መንግስት፣ በሕገ ብሄር (ፍትሃ ብሄር) እና በህገ ቅጫ (ቅጣት/ወንጀለኛ ሕግ) ህጋዊ ሰውንነት ተደንግጎላቸው ነው ትክክለኛው የሰው ልጆች መተድደሪያ መንግስት የቆመው ።
አንድ መንግስትም ሆነ ስልጣን በሕዝብ ምርጫ ስልጣን የተሰጠው ነውና በሕዝብ ምርጫ ብቻ ነው ከስልጣን መነሳት ያለበት የሚባለው ይህን በመሰለ በግለሰብ ዜጋ ሙሉ መብት፣ ነጻነት እና እኩልነት ላይ የቆመ አገዛዝ ሲሆን ብቻ ነው ።
በኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የዘጋ ፖለቲካ አገዛዝ ስለሌለ ምርጫ የሚባል ነገር ባዶና ዉሸት ስለሆነ በሕዝብ ፈቃድ ስልጣን የተሰጠው መሪ የለም ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው በጎሳ ምርጫ እና በጎሳዎች (ዜጋዎች) ሳይሆን ፈቃድ ወይም መገደ ላይ የቆመ የኦሮሞ ጎሳ አገዛዝ እንጂ የኢትዮጵያ ዜጋዎች ፖለቲካ ስርዓት ወይም መንግስት አይደለም ።
በመሆኑም በጎሳ ሲስተም ውስጥ በፍጹም በድምጽ መስጠትም ሆነ ድምጽ ብልጫ ላይ የቆመ የስልጣን ሽግግር ሊኖር በፍጹም አይችልም። ስልጣን ላይ ያለው ጎሳም የሚወገደው በሌላ የጎሳ ኃይልና ወይም ጎሳዎች ስብስብ ነው ።
የጎሳ ፖለቲካ ሲስተም በፍጹም ለዘላለም ሰላማዊ አይሆንም ምክንያቱም በሰላም ስልጣን መቀባበያ ዘዴ ስለሌለው፣ በዜጋዎች እኩልነት ላይ የቆመ ሲስተም ስላልሆነ ። ሰላም ያለው በግለሰብ ሙሉ ነጻነት፣ ፍትህ እኩልነትና አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚገዛ ሲስተም ሲኖር ብቻ ነው ።
ፖለቲካና v. ሚሊታሪ
በመጨረሻም ስልጣን ላይ ያሉ ገዢዎች ስልጣን አልለቅም (የዛሬ አቢይ አይነት) የሚሉት የሚሊታሪው ድጋፍ ስለሚይዙ ነው ። በጎሳ ፖለቲካ እና ዜጋ ፖለቲካ መሰል ሆኖ ግ ን በከረረ ጎሳ ክፍፍል የተወጠረ ሕብረተሰብ ውስጥ ሚሊታሪው አገር ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ገዢ ጠባቂ ስለሆነ ሚሊታሪ የፖለቲካ ስልጣን መያዣና ስልጣን ላለምልቀቅ መከላከያ ኃይል ነው
ማለትም እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር ስልጣን የሚፈልቀው ከጠመንጃ አፈሙዝ ነው ። ይህን በመሰለ ሕብረተሰብ ወስጥ ህልውናና መብታቸው የተገፈፉ ሕዝብ (ለምሳሌ የዛሬው አማራ) ሕይወታቸውና መብታቸውን ለማስከበር ፣ በአገራቸው መንግስት ውስጥ ፍትሃዊ ድምጽ ለማግኘት ያላቸው ብቸኛ አማራጭ አመጽና የጦር ኃይል ነው ። ይህ ደሞ ተፈጥሮአዊ መብታቸው ነው ።
ዛሬ ላይ የአማራ ሕዝብን አመጽ ፍትሃዊነትና ትክክለኛነት የማይቀበሉ አንድም ፖለቲካ ምን እንደ ሆነ የማያውቁ (የማወቅ ሃላፊነ አለባቸው) ወይም የጎሳ ፖለቲካ ትክክል ነው፣ አንድ በቁጥር የላቀ ጎሳ ያነሱትን ለዘላለም የመግዛት መብት አለው ፤ የአንድ አገር ባለቤት በ% 25 ቢሆንም ከ88 ግለ ጎሳዎች በቁጥር ስለሚበልጥ ለዘላለም ያገሪቱ ባለቤት ፣ መሬቱም፣ ሃብቱም ፣ ባንኩም ታንኩም የሱ መሆን አለበት የሚሉ የዚያ ጎሳ ወዳጆች መሆን አለባቸው !
ዛሬ የኦሮሞ ባለስልጣኖች እያሉን ያለው ያ ነው! መላ ኢትዮጵያ እንደ ንብ ተቆጥቶ ይህን የወረሙማ እብደት አደብ ለማስገዛት ከአማራ ጋራ የቆመው ለዚህ ነው ።
የአማራ አመጽን የወለደው የትግሬና ኦሮሞ ጎሳ አገዛዝ ግፍ ነው!
ማኛም ለኬር አክራሚ አሰላንህም! እንኳን ለቅዱስ እንቁጣጣሽ አደረሳችሁ!
ሆረስ ኃይለ ብርሃን