በውሸት እና ድንቁርና ላይ ቆሞ እዚህ የደረሰው የኦሮሞ ብሄር ጥያቄ ላይ መፈንጠቅ ያለበት የእውቀት ብርሃን ! እኔ ሃተታ አላበዛም ።
ሳፋራ ጥንታዊ የሴም እና አረበኛ ቃል ሲሆን ባዶ ቦታ፣ ባዶ መሬት ማለት ነው። ሳፋራ በአንድ በኩል ጠፈር ወይም ባዶ ቦታ የሚለው ቃል አባት ሲሆን ዛሬ ሰፈር (ቪሌጅ) የሚባለው ቃል ነው።
ሳፋራ የሚባለው ቃል በአረብኛም በጉራጌኛም ገፈረ (የተተወ፣ ባዶ) ፣ ጀፎረ (ባዶ ቦታ)፣ ጋፋራ ( ባዶ ቦታ) ማለት ነው።
ስለዚህ ሰፋሪ የሚባሉት ሕዝቦች በአንድ ባዶ ማንም በማይኖርበት ቦታ ሰፍነው ሰፈር የቆረቆሩ ቀዳሚ ኦሪጂናል የመጀምሪያ ነዋሪዎች ናቸው ።
ሰፋሪ ማንም ባልያዘው ባዶ ቦታ ሰፍኖ ሰፈርና አገር የሚቆረቁር ሕዝብ ነው ።
ወረራ ጦርነት ማለት ሲሆን በጦርነት በሃይል የተያዘ መሬት ማለት ነው። ጦርነት ወይም ወረራ ትግል፣ ጊጂላ፣ ግድያ፣ ገድል ፣ መጋደል ማለት ሲሆን የቃሉ ስር ኃይል ወይም ጎራዴ ማለት ነው ።
ስለዚህ ሰፋሪዎች በባዶ መሬት የሰፈኑ ሕዝብ ሲሆን ፣ ወራሪዎች በጦርነት በኃይል ነባር ሕዝቦችን ነቅለው መሬቱን የያዙ ማለት ነው ።
አሁን እንግዲህ ማነው ሰፋሪ? ማነው ወራሪ መለየት ትችላላችሁ !!!
ሆረስ ዐይነ ብርሃን
ሴፕቴምበር 1 2023