ማሞ ቅሎ ያ ማሞ ቅሎ
እንዲህ ብሎ ስጠሩህ ሁሉም ተንቀልቅሎ
አሁን ምን ላይ ደረሱ እንዲሁ ተንጠልጥሎ
ወደ ጉድጓዳቸዉ ተመልሶዋል፤ እዚያዉ ያልቃሉ ተቀቅሎ
አረ ማሞ ቅሎ ያ ማሞ ቅሎ፤ አይ ማሞ ቅሎ!
እንዴት ሰዉ ወጠዉ እንደዚህ ተክሎ
ሁሉንም ወደ ታች ኣያቸዉ በትንሽነታቸዉ አቅሎ፤
ታዲያ ማን ይሁን አሁን ያ ማሞ ቅሎ?
ማሞ ቅሎ ያ ማሞ ቅሎ፤ አይ ማሞ ቅሎ!
አገርን አሳደገ በብላት ታክሎ
ምድሯን አደረጋት አረንጓዴ፤ ችግኝ ተክሎ
ኢትዮጵያን ወሰዳት ወደፊት፤ በእዉቅት ታክሎ
የአደጉ አገሮች ጎራም ወሰዳት፤ በብርክስ ዉስጥ ቀላቅሎ
ጋና ጉድ ያሳየናል ይህ ሰዉ በእዉቀት ጎዳና ላይ ጉዞዉን ቀጥሎ
አይ ማሞ ቅሎ: ያ ማሞ ቅሎ
ቆሞ ይጠብቁህ እንዲሁ ተጃጅሎ እንዘህ ምድረ ጅሎ።