Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

በዜግነት ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ አገር መከላከያ ባላቸው አገራት መፈንቅለ መንግስትማድረግ ይችላሉ -ቅቡልነት ያጣ አምባገነን ለማስወገድ።

Post by Abere » 30 Aug 2023, 10:15

በዜግነት ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ አገር መከላከያ ባላቸው አገራት መፈንቅለ መንግስትማድረግ ይችላሉ -ቅቡልነት ያጣ አምባገነን ለማስወገድ። በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዘመን በአለም ላይ አምባገነን ማስወገድ የሚያስፈልጋት ግምባር ቀደም አገር ኢትዮጵያ ነበረች። ሆኖም ግን ለአለፍቱ 32 አመታት ኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት የሌላት እና በግለሰብ ወይም የጎሳ ጠባቂ ዘበኛ የተያዘች በመሆኑ ህዝብ በጭቆና ብቻ ሳይሆን በሞት፤በስደት እና በስቃይ ይኖራል። መፈንቅለ መንግስት የሚደገፍ ድርጊት ባይሆንም ፍትህ እና ዲሞክራሲ፤ ህገ-መንግስታዊ ስርዐት በሌለባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት አይቀሬ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ሊያደርገው ይችላል። 1.5 ሚልዮን ህዝብ የጨረሰ በቀጣዩ ሌላ ሚልዮኖች እየፈጀ ያለ ዜጎችን ከቤታቸው በደረቀ ሌሊት የሚያፈናቅል እያንዳንዱን በከተማ የሚገኝ ትምህርቤት እና ዛኒጋብ እስር ቤት ያደረገ ጭራቅ መፈንቅለ መንግስት ሲያንሰው እንጅ አይበዛበትም። የኢትዮጵያው መፈንቅለ መንግስት ቤተ-መንግስት ያለውን ብቻ ሳይሆን የጎሳ ጠባቂ የሆነውን የጀኖሳይድ ተዋናይ የሆነውን ይጨምራል። ኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት ያስፈልጋታል።