1ኛ ለህሊናቸው፣
2ኛ ለመረጣቸው ህዝብ
3ኛ። አሁን ለሚሰራው ህገ መንግስት ።
ከተናገሯቸው በርካታ ሃቆች በጥቂቱ “ብልጽግና እና የአማራ ህዝብ ላይገናኙ ተለያይተዋል” “የምወክለው የእማራ ህዝብ ነው። የአማራ ህዝብ እንቅስቃሴ ግፍና በደል የወለደው ነው” “የብልጽግና መንግስት በራሱ ክፋትና አቅመ ቢስነት ያጣውን ቅቡልነት ለማስመለስ መሞከር የጥፋት መንገድ ነው” “በየቦታው በተደጋጋሚ ሲጨፈጨፍ፣ ሲታሰር፣ ሲፈናቅል ፣ ሀብትና ንብረቱ እንዲያጣ ተደርጎ ለጉስቁልና ለመከራ ሲዳረግ የአማራ ህዝብ ሰብአዊ ክብሩ ኣንዲጠበቅለት በሰላማዊ ሁኔታ ደጋግሞና አጥብቆ መንግስትን ጠይቆአል” የአቶ ገዱ እንዳርጋቸው ቆራጥነት፣ ሞራልና ህሊና አስደማሚ ነው። በዚህ ቀውጢ ሰአት ፣ በአማራ ህዝብ ላይ የሚወርድ ግፍና መከራ ወቅት ከአማራ ህዝብ ጎን ወግነው ተገኝተዋል።
በአንጻሩ ደግሞ አብላጫው የተወካዮች ም/ቤት አባላት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሽፋን፣ የመንግስታዊ ሽብር በአማራ ህዝብ ላይ እንዲቀጥል ድምጽ ሰጥተዋል። በደብረ ብርሃን፣ በፍኖተ ሰላም ፣ በማክሰኚት ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ በሰላማዊ ዜጎች እይተኬ ህይወታቸውን አጥተዋል። በፋሽስቱ በሽተና አብይና የብርሃኑ ጁላ የሚታዘዘው የመከላከያ ስራዊት ድሮን፣ ከባድ መሳሪዎችን በመጠቀም ህዝብን መጨፍጨፍና የጦር ወንጀሎችን መፈጸም እንዲቀጥል ፈቅደዋል ማለት ነው። እነዚህ የህ/ተ ም/ቤት አባላት በተለይም ለፋሽስታዊ አዋጁ ድምጽ የሰጡት የአማራ ክልል ተወላጆች በመረጣቸው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የጦር ወንጀልና የግፍ ግፍ እንዳላየ፣ ይህ የግፍ ግፍ እንዲቀጥል አዋጁን በማጽደቅ የተቀመጡበትና ህዝብ መርጦቸው የተቀመጡበት ወንበርና ጥቅማ ጥቅሞቻቸውን በልጦባቸው የይሁኝታ ድምጽ ሰጥተዋል። በአማራ ህዝብ ላይ የእልቂት ሰይፍ እንዲመዘዝ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህ በመረጣችው ህዝብ ላይ የተፈጸመ ታሪካዊ ክህደት ነው።