Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በተራ

Post by sarcasm » 08 Aug 2023, 18:15







መልካሙ ተበጀ(በተራ በተራ)



በሳቅ በጨዋታ በደስታ በሀዘን
ባለፉት አመታት ስንቱን አሳለፍን
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
ደቂቃ አልፎ ሰአት ሲተኩ ቀናቶች
አለፉ ተረሱ እነዚያ ጊዜያቶች
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
እንደጥሩ ታሪክ እንደጥሩ ዝና
ልናወራዉ በቃን ያ ሁሉ አለፈና
መከራና ስቃይ ካደረ አይቆጭ ምነዉ
በኖርነዉ ጊዜያችን ስንቱን አሳለፍነዉ
በሳቅ በጨዋታ በደስታ በሀዘን
ባለፉት አመታት ስንቱን አሳለፍን
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
ሰዉ ሁሉ ሲስማማ ሲፋቀር ሲዋደድ
ማታለል ሳይበዛ መዋሸት በገሀድ
በአፍ ቢለዋነት ሳይኖር ሰዉን ማረድ
ያ ደጉ ቀን ጠፋ እኛ ሳንወድ በግድ
የልጅነት ወራት የአበባዉ ጊዜአችን
ያ ለዛ ጨዋታ የዋህነታችን
ጎልማሳነት አልፎ እርጅና መጣና
ልናወራዉ በቃን ያ ሁሉ አለፈና
ያሳለፍነዉ ጊዜ ጥሩም ነዉ መጥፎም ነዉ
ግን ለተረት ያህል ስንቱን አሳለፍነዉ
የምትፈልጉትን የዘፈን ግጥም በኮሜንት ንገሩን👇👇👇
በየጊዜዉ የዘፈን ግጥሞች እንዲደርሳችሁ ፔጁን #like_እና_share አርጉ