Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"አፈጉባኤያችን ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች።" በድብቅ ተቀርጾ የወጣው የአቶ ዮሀንስ ቧያለው በአማራ ክልል ም/ቤት ያደረጉት ሙሉ ንግግር

Post by Wedi » 22 Jul 2023, 04:07

"አፈጉባኤያችን ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች።" በድብቅ ተቀርጾ የወጣው የአቶ ዮሀንስ ቧያለው በአማራ ክልል ም/ቤት ያደረጉት ሙሉ ንግግር

በድብቅ ተቀርጾ የወጣው የአቶ ዮሀንስ ቧያለው በአማራ ክልል ም/ቤት ያደረጉት ሙሉ ንግግር July 20 2023

"በራሳችን አፈጉባኤ ታፍነናል። ወይ አፈጉባኤያችን ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች። ከእኛ ባልሆነች።" - አቶ ዮሐንስ ቧያለው

"አለመታደል ሆኖ የአማራን ችግር እንዳንመክር፣ በአማራ ምክር ቤት አፈጉባኤ ተከልክለናል። ወይ አፈጉባኤዋ ጭራሽኑ ከአድዋ፣ ወይ ከበሻሻ በሆነች። ከእኛ ባልሆነች። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ሁላችንንም ይገድሉናል። ለስልጣናችን፣ ለህልውናችን የተዋደቀውን ልዩ ሀይል አፈረሳችሁት። ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን፣ አማራን እናዋርዳለን ያሉት ጀነራሎች በነፃነት በሚንፈላሰሱባት ሀገር፣ እያነከሰ ያዋጋው ጀነራል ህክምና ተከለከለ። ለአማራ የቆሙ አመራሮች ተገደሉ፣ ተባረሩ። ምን ቀረን?"

"ጠላቶቻችን በአንድነት ዘምተውብናል። ክልሉን ልክ እናስገባዋለን በማለት ተነስተዋል። መከላከያ ያለ ክልሉ ፍቃድ፣ አማራን እያተራመሰ ነው። እኛስ?"

"አሁኑኑ መፍትሔ እናስቀምጥ። በዚህ ምክር ቤት በአማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር እና መፍትሔ የሚያጠና ቡድን ይዋቀር።"

አቶ ዮሐንስ ቧያለው


ሙሉውን ከዝህ ላይ አዳምጡት